Thursday, May 8, 2014

ያልተጣራ ክስ ፦ "ኬንያ እና ስዊዲን ሄደው የሽብርተኝነት የሃገር መበጥበጥ እና ተያያዥ ጉዳዮች ኮርስ ወስደዋል"

ያልተጣራ ክስ ፦ "ኬንያ እና ስዊዲን ሄደው የሽብርተኝነት የሃገር መበጥበጥ እና ተያያዥ ጉዳዮች ኮርስ ወስደዋል" ... ወይ ወያኔ ፈጠራ አያጣም እኮ .. እነዚህ ሃገራት የሽብር ኮርስ ይሰጡ ጀመር እንዴ..፡ ? ከኢርትራ ነው ከወያኔ ፕሮፖዛሉን የገዙት? WE ARE ALL ZONE 9!!! የዞን 9 አባላት የፍርድ ቤት ውሎ :
ሦስቱ የዞን 9 አባላትና ሶስቱ ሌሎች ጋዜጠኞች ዛሬ ሚያዝያ 29 2004 አም ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ የዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ በዝግ ችሎት የቀረቡ ሲሆን ፓሊስ ለምርመራ 10 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል፡፡ በዚህም የተሰጠው ምክንያት
1. ተጨማሪ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ እንዳንችል ሊሸሹ ይችላሉ
2. ከውጪ ገንዘብ በማስገባት የተገዙ ቁሳቁሶችን ለመያዝ ጊዜ ያስፈልገናል
3. የሰነድ ትርጉምና የባለሞያ ድጋፍ ለምርመራው አንፈልጋለን
4. ምስክሮችን ለማዘጋት ጊዜ ያስፈልገናል
ሲሆን ጠበቃቸው ከላይ የተጠቀሱት ምክንያቶች ዋስትና ለማስከልከል በቂ አይደሉም ሲል ተከራክሮአል፡፡ ፍርድ ቤቱ አስር ተጨማሪ ቀን የጊዜ ቀጠሮ የፈቀደ ሲሆን ግንቦት 9 ቀን ተመልሰው ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፡፡ በተጨማሪም ተከሳሾች በቤተሰብና በህግ አማካሪ መጎብኘት አለመፈቀዱ አግባብ አለመሆኑን ፍርድ ቤቱ ጠቅሶ ከነገ ጀምሮ ቤተሰብ እና የህግ ባለሞያ እነዲያያቸው እንዲፈቀድ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡ ይህ በእነደህ እንዳለ የመጀመሪያ የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው ቀን የተጠረጠሩበት የተባለው ወንጀል ላይ ቀላል የማይባል ለውጥ የተደረገ ሲሆን የመጀመሪያው ክስ ላይ የነበረው |” ራሱን የሰብአዊ መብት ድርጅት እያለ ከሚጠራ ድርጅት ጋር በሃሳብና በፋይናንስ መተባበር በማህበረሰብ ሚዲያ ብጥብጥ ለማነሳሳት ” የሚለው ወደ “በህቡህ በመደራጀት በሽብርተኛነት ተግባር ከተፈረጀ ድርጅት ጋር በመገናኘት ገንዘብ በመቀበልና አገር እና ህዝብን ለማሸበር ሲንቀሳቀሱ” በሚል ለውጥ እነደተደረገበት የጠበቃው ንግግር ያመላክታል
በመጀመሪያውም ሆነ ሁለተኛው ክስ ላይ የተጠቀሱትን ወንጀሎች የዞን ዘጠኝ አባላት እንዳልፈጸሙት ማንኛውም የሽብር ተግባር ከተጠረጠረ ድርጅት ጋርም ፈጽሞ ግንኘነት እነደሌላቸው ና ምንም አይነት የገንዘብ ድጋፍ ተቀብለው እነደማያውቁ እየገለጽን የተጠረጠሩበትን ወንጀል በየቀጠሮው መቀያየሩ ያለምንም ተጨባጭ ማስረጃ እንደዞን 9 በሚያደርጉት እነቅስቃሴ ብቻ መታሰራቸውንና ጉዳዩ የፓለቲካ ክስ መሆኑን እንደሚያሳይ እንደምናምን ደግመን ለመናገር እንወዳለን፡፡ የዞን 9 ነዋሪያን ዛሬ ፍርድ ቤት በመገኘት ላሳዩትን አጋርነት ምስጋናውን እያቀረበ ነገ በተመሳሳይ ሰአት በፍቃዱ ማህሌትና አቤል ስለሚቀርቡ አጋርነታችሁን ማሳየት እንድትቀጥሉ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

No comments:

Post a Comment