የህወሐት/ኢህአዴግ ፌዝ #በሬድዋን አንደበት!!
አቶ ሬድዋን ትላንት መግለጫ ሰጥተው ነበር በመግለጫቸውም መንግስታቸው 23ኛውን ግንቦት-20 ከግንቦት 01 - 30 "ሩቅ አስባ ሩቅ ለማደር የምትተጋ ሀገር" የሚል ሞቶን በማንገብ ለማክበር መዘጋጀቱን ገልፀዋል።የተጠየቁትን የተለያዩ ጥያቄዎች ሲመለሱ አቶ ሬድዋን እንዲህም አሉ "ከግንቦት-20 ድል በኋላ ኢትዮጵያ ትልቅ ለውጥ ውስጥ ገብታለች በከፍተኛ ሁኔታም እያደግች ነው፤የተወሰኑ የአፈፃፀምና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ቢኖሩብንም ዲሞክራሲያችን እያደገና እየጎለበተ ነው፤ኢትዮጵያን አኮብኩቦ ከመሬት መነሳት እነደጀመረ አውሮፕላን ውሰዷት አውሮፕላኑ የተስተካከለ ከፍታ እስኪደርስ ትንሽ መንገጫገጭ እንደሚገጥመው ሁሉ አሁን እኛ ያሉብን ትናንሽ ችግሮችንም ወደ አሰብነው ለውጥ ስንገሰግስ እንደሚገጥሙን መንገጫገጮች ውሰዷቸው"።የሩቅ የሩቁን እንኳን ብንተወው ትላንት በአምቦና በተለያዩ ቦታዎች ጥያቄያቸውን በሰላማዊ መንገድ ያቀረቡ ወጣቶችን የገደለው፣ያቆሰለውና ያሰረው ፤ትላንት ስለ ፍትህና ነፃነት በቅን ልቦና የፃፉ ጋዜጠኞችንና ጦማሪያንን እስር ቤት ወርውሮ ሌት ከቀን በግርፋት የሚያሰቃየው ፤በእምነት ተቋሞች ገብቶ መጅሊሱንም ሲኖዶሱንም የተቆጣጠረው ህወሐት/ኢህአዴግ ነው እነግዲህ የሩቅ አሳቢያችን ይህ ሁሉ በደልና ግፍ ነው ትንሹ መነገጫገጭ።ጅብ የማያውቁት ሀገርን አልተርትም ህወሐት/ኢህአዴግ የምናውቀው የቀን ጅብ ነውና ኢትዮጵያ አይደለም የሩቁን ልታልም ቀርቶ ዛሬዋን አጨልሞ ነገዋን እንዳታይና እንዳታስብ ያደረገ ስርዓት ስለ ሩቅ አላሚነት ሲደሰኩር መስማት በቆሰልነው ቁስላችን ላይ የማላገጥንና የእብሪትን እንጨት መስደድ ነው።አቶ ሬድዋን ግዴለም ኢትዮጵያን አኮብኩቦ ከመሬት መነሳት እነደጀመረ 80 ሚሊዮን መንገደኞች እነደጫነ አውሮፕላን እንወሰዳት ህወሐቶችን/ኢህአዴጎችንስ? በግንቦት-20 ቀን የጦር መሳሪያ ታጥቀው አውሮፕላኑን በጉልበት ጠልፈው መንገደኞቸን በማነገላታትና በመገደል እነደተጠመዱ አውሮፕላኑን ከነ 80 ሚሊዮን መንገደኞቹ የመከስከስ አደጋ እነዲጋረጥበት እነዳደረጉ አሸባሪዎች??
#ሀናመታሰቢያ 02/09/06
No comments:
Post a Comment