Wednesday, May 14, 2014

አንበጣዊ ሃረካት - አዲስ ዶሜንተሪ በኢቲቪ

አንበጣዊ ሃረካት - አዲስ ዶሜንተሪ በኢቲቪ
**************************************
ተመልካቾቻችን <አንበጣዊ ሃረካት> የሚል አዲስ ዶክሜንተሪ ከነገ ጀምሮ በተከታታይ ስለምናቀርብ እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።
ዶሜንተሪውን ለመከታተል እንዲይመቻቹ እነሆ ለቅምሻ ያህል
"አንበጦቹ ከሱማሌ ላንድ ተነስተው አዲስ አበባ የገቡት ለሽብር ተግባር እንደሆነ በቂ መረጃ ... እደግመዋለሁ ከበቂ በላይ መረጃ አለን ... ማስረጃ ግን የለንም አራት ነጥብ"
.......... (ታላቁ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከሰማይ ቤት በእስካይፕ)
"አንበጦቹ ከሱማሌ ላንድ ተነስተው ለሽብር ተግባር አዲስ አበባ እንደገቡ መረጃ አለን .. ማስረጃ ግን የለንም።
... (ታናሹ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ (ቃል በቃል ኮፒ ፔስት ከአራት ነጥቡ ውጪ))
"Successful meeting with the guest Anibetoch ... I am so happy."
.... Dr. Tedros Adhanom Ghebreyesus (የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር)
"አራት ኪሎ ቤተመንግስት በአንበጣ ተወሯል አሉ። ወይ አራት ኪሎ ለስንት አንበጣ ትችያለሽ?"
...... Abraha Desta ከመቀሌ (ይሄን የጻፈው ሌላ ሰው ቢሆን ኖሮ በዘረኝነት ተፈርጆ ነበር) (አብርሽ እኮ ቀልዶ ስለማያውቅ መጀመሪያ ሳየው አካውንቱ ሃክ የተደረገ መስሎኝ ነበር። It is so!!! የሚለውን ፊርማ ሳይ ተረጋጋሁ ... ይልመድብህ እስኪ አንበሳው)
"አንበጦቹ ወደ አዲስ አበባ የመጡት የኦሮሚያን ልዩ ዞን መሬት ለመቀራመት እና ሃብታችንን ለመቦጥበጥ ስለሆነ በሜንጫ አንገታቸውን"
...... (ጃ ነፍሴ ከኒውዮርክ እና ሚኒሶታ)
"አዲስ አበባ ከ23 አመት በኋላ በድጋሚ በአንበጣ ቁጥጥር ስር ወደቀች"
..... Semir Ali ኢሳትን ጠቅሶ
"በተያያዘ ዜና እነዚህ አንበጦች የአንድ ክልል ተወላጆች ሲሆኑ ከመስቀል አድባባይ እስከ መገናኛ ያሉት ሕንጻዎች በሙሉ የእነሱ ንብረት እንደሆነ የአይን ምስክሮች ለኢሳት አረጋግጠዋል"
.... (ኢሳት ሬድዮ እና ቴሌቭዢን)
"አንበጦቹ ከግንቦት ሰባት፤ ከግብጽ፤ ከኤርትራ እና ከፈረንጆች ገንዘብ ተቀብለው አዲስ አበባን እንደወረሩ ከፖሊስ መረጃ አግኝተናል"
.... (ሚሚ ስብሃቱ ከሶስት መአዘን ጠረጴዛ) ... (እርስዎ ከፈረንጅ የተቀበሉት ገንዘብስ የጦጣ ፍራንክ ነው?)
"የኒዎሊብራል ሃይሎች የቀለም አብዮት ለማካሄድ ከሚጠቀሙበት ዋነኛ መንገድ አንዱ አንበጣን በገንዘብ መደገፍ እና ወደ ሌሎች አገሮች ማሰማራት ነው"
..... Merkeb Negash ከጅማ ዩኒቨርሲቲ (ደግሞ ዲግሪዬን ገዝቼው አይደለም) ... lol)
"አንበጦቹ የመጡት አገራችን ካስመዘገበችው እድገት ትምህርት ሊቀስሙ ነው። ካላመናቹኝ ልማልላችሁ ... ብርኒህጎ ይሙት!!!"
..... Sabawi Desalegn ከፌስ ቡክ)
"እነዚህ አንበጦች ከግብጽ ተልከው እንደሚመጡ ከሶስት ወር በፊት አንድ የፈረንጅ ዲፕሎማትን ጠቅሼ ጽፌ ነበር። በዚህም ምክኒያት ዳንኤል ለምን አይታሰርም እያሉ ያወሩት ሰዎች ዛሬ አንበጦቹ መምጣታቸው ሲረጋገጥ ምን ይዋጣቸው? ... ካለ እኔ ሌላ ብሎገር አላዩም እንዴ?"
...... Daniel Berhane ከሆርን አፌርስ
"<እንደምችመለከቹች> አንበጮቹ በዳያፖሯ መሽገው ኢትዮጵያን ለማተራመሽ እንደመጡ እኔ እራሼ ዋሽንግተን ሽኖር አረጋግጫለሁ።
--- ቤን ነኝ ከኢትዮጵያ ፈርስት ("ቤን" ብሎ ኢትዮጵያ?")
"እነዚህ አንበጦች በዋናነት ከሶስት ብሄሮች የተውጣጡ ናቸው። ከአማራ ክልል የመጡት አንበጦች የበላይ ነን ማለት እስካልተው፤ ከትግራይ ክልል የመጡት አንበጦች እኛ ብቻ ማለት እስካልተው፤ የኦሮሚያ ክልል አንበጦችም ኩርፊያቸውን እስካልተው ድረስ ተባብረው ሊኖሩ ስልማይችሉ ወደ ሱማሌ ላንድ ሊመለሱ ይችላሉ"
..... ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና (የመድረክ ሊቀመንበር)
"መክሸፍ እንደ አንበጦች"
..... ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም
በመጨረሻም
"ሁሉም ትክክል ነው ግን በእግዚያብሔር ዞን-ዘጠኞችን Zone9 ፍቱልን"
..... እኔ እራሴ ...ከማርስ ፕላኔት (ደግሞ በሽብርተኝነት ሆ)

No comments:

Post a Comment