Monday, May 26, 2014

ችሎቱ- ልብ አንጠልጣዩ ቴአትር

ችሎቱ- ልብ አንጠልጣዩ ቴአትር
ደረጀ ሀብተወልድ( ኢሳት)
እንደወትሮው ሁሉ ዛሬም ከቃሊቲ ወህኒ ቤት እስከ ጊዜያዊው ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ድረስ ባለው አስፋልት ዳርና ዳር
እስካፍንጫቸው የታጠቁ ወታደሮች በተጠንቀቅ ቆመዋል።መንገድች ለእግረኞችም ሆነ ለሌሎች ተሽከርካሪዎች ዝግ ናቸው። ወደ
130 የምንጠጋ እስረኞች በአራት ኮስተር መኪናዎች ተጭነን ወይም እንደወቅቱ ቀልዳችን እንደ አቶ መለስ ታጅበን ወድ ችሎቱ
እያመራን ነው። በየመኪናዎቹ ውስጥ ያሉትን ታጣቂዎች ሳይጨምር መትረየስ የደገኑ ሶስት ፒክ አፖች ከፊት፤ ሶስት ፒክ አፖች
ከሁዋላ አጅበውናል።አቶ መለስ በአንድ ወቅት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፦‛ስልጣን እስር ቤት ነው‛ሲለ ምን ማለታቸው እንደሆነ
በደንብ ገብቶኛል። በእርግጥም በህዝብ መካከል በነፃነት መራመድ ልማይችልና ዘመኑን ሁለ በጥቁር መስተዋትና በታጣቂ ተከብቦ
ለሚኖር እንደ እርሳቸው ላለ ሰው- ስልጣን የከፋ እስር ቤት ለመሆኑ ምርምር የሚጠይቅ አይደለም። ለዚህም ይመስለኛል
በግንቦት 97 ምርጫ ውድድር ወቅት አርቲስት ደበበ እሸቱ፦‛ቅንጅት ስልጣን ሲይዝ የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን አቶ መለስም
ጭምር ነፃ ይወጣሉ፤ የፈለጉበት ሱቅ ገብተው ሲጃራቸውን ይገዛሉ፤ በህዝብ መካከል ያለ ስጋት ይራመዳሉ‛ በማለት በተደጋጋሚ
ሲናገር የነበረው።
እናም... ታጅበን ወደ ችሎቱ ስናመራ ... ወደ ቤታቸው እንዲከተቱ የተደረጉት የአካባቢው ነዋሪዎች አንገቶቻቸውን በመስኮት
በማውጣት፣ በየቤታቸው በር ሊይ በቆሙት ቅልብ ታጣቂዎች ጀርባ በማንጋጠጥና በሁለት ጣቶቻቸው የቅንጅትን አርማ
በማውለብለብ ያስለመዱንን ‚የአለንላችሁ በርቱ!‛ አሸኛኘት ዛሬም አሊጓደሉብንም። ልክ ከጧቱ 3፡00 ሲሆን የቅንጅት መሪዎችን
በጊዜያዊነት እንዲያስችል ወደተዘጋጀው ሰፊ አዳራሽ ደረስን።የስድስት ኪሎው ቋሚ ችሎት ወደዚህ እንዲቀየር የተደረገው፤ፍርድ ቤት
በቀረብን ቁጥር “መሪዎቻችን ይፈቱ!” የሚለው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የተፈሪ መኮንን ተማሪዎች አመፅ፤በስፍራው እንደ አሸን
በሚፈሱት ደረት አልሞ ተኳሾች ጥይት ሊቆም ባለመቻሉ ነው።
*** ***** ****
ችሎቱን ለመከታተል አስቀድመው በመመዝገብ መግቢያ ካርድ ያገኙ የታሳሪ ቤተሰቦችና የወቅቱ ጭፍን እርምጃ የሳታቸው
አንዳንዴ የአገር ውስጥ ጋዜጠኞች ፤እየተፈተሹ፣መታወቂያቸውን እያሳዩና በፌዴራል ፖሊሶች እየተመዘገቡ ወደ አዳራሹ ከተቱ።
ዘወትር እንደሚደረገው ሁሉ የእነሱ መግባት እንደተጠናቀቀ በከፍተኛ አጀባና ጥበቃ ከመኪናዎቹ ወርደን በሁለት መስመር በመሰለፍ
ወደ አዳራሹ ገባን። ታዲሚዎች ከመቀመጫቸው በመነሳት እጃቸውን አወዛወዙ፤እኛም እጃችንን በማወዛወዝ የአፀፋ ሰላምታ ሰጥተን ተቀመጥን።ያ ሰፊ አዳራሽ ከአፍ እስከ ገደፉ ሞላ።
ሁሉም የቴአትሩን መጀመር በጉጉት እየተጠባበቀ ነው።ጥቁር ካባ የደረቡት ሶስት ዳኞች በአዳራሹ ጓሮ በር በመግባት መድረኩ ላይ
የተዘጋጀላቸውን ስፍራ ያዙ፦ የቀኝ ዳኛ ልኡል ገብረማርያም፣ የግራ ዳኛ አህመድ ኢብራሂም ሳኒ እና የመሀል ዳኛው አዲል።
አቃብያነ -ህጎቹ በትንሹ ለ30 ደቂቃ መዘግየት ልምዳቸው ነበርና ዛሬም ወንበራቸው ክፍት ሆኖ ይታያል። እንደምንም
ተንጠባጥበው መሟላታቸውን ተከትሎ፦
“እባካችሁ አቃቤ ህጎች በሰዓቱ ተገኙልን፤ እናንተ ቀድማችሁ መገኘት ሲገባችሁ እንዴት ታረፍዳላችሁ? ሁለተኛ እንዲይደገም!”
የተለመደው የመሀል ዳኛው ማሣሰቢያ ዛሬም ተሰማ።እነሱ ግን አልበረዳቸውም፤ አልሞቃቸውም። እነዚህ አቃብያነ-
ህጎች ከዳኞች በላይ አርፋጆችና ፈራጆች ሲሆኑ፤ ተከሳሾች ሊይ አፋቸውን ያሊቅቁ ዘንድ ረዥም የስድብ አፍ የተሰጣቸው
ይመስላሉ። ተከሳሾች “የንጉስ ሌጆች” የሚሌ ቅፅል ስም የሰጡዋቸው እነዚህ አቃበያነ ህጎች፦ አብርሀም ተጠምቀ፣ ሽመልስ ከማልና
ሚካኤሌ አብርሀ ይባሊሉ።
ጊዜያዊው ችሎት ለመጀመሪያ ቀን በቀረብን ዕለት አንደኛው አቃቤ ህግ 1ኛ ተከሳሽ የሆኑትን
ኢንጅነር ሀይሉ ሻውልን “አንተ!” እያለ ሲዘልፋቸው፤ ድንገት ብድግ በማለት ቁጣ ባዘለ ቃል፦‛ በእድሜ አባትህ ይሆናሉ፤ደግሞም
ሊቀ-መንበራችን ናቸው፤ አንተ ብለህ ልትጠራቸው መብት የለህም!” በማለቱ፤ ችሎት በመድፈር እዚያው ተከሶ በፖሊሶች እየተዳፋ
እንዲወጣ የተደረገው ማን ነበር? አዎ !ያችው መከረኛ ብርቱካን ሚዴቅሳ ነበረች።
ኩት! የማይባሉትን የሹም ዶሮዎች ዯደፍራለቻ! የንጉስ ልጆችን ገላምጣለቻ!
እሷ ለመብቷ በራሷ ቆመች፤ እነሱም በአለቃቸው ተመክተው አቅራሩ።
እነሱ፣
በጌታቸው እያመኑ- ባ’ለቃቸው እየፎከሩ፣
ላታቸውን ውጪ አሳደሩ።
እኛም፣
ቀንዳቸንን አውጥተን-ቀያችን እንዳይጠቃ፣
ፀንተን ቆመናል በጥበቃ።
……. እናም ከሳሾች (አቃብያነ-ህጎች) ምስክራቸውን ያሰሙ ዘንድ መሀል ዳኛው ጠየቁ ። መጋረጃው ተገለጠ፤ የእለቱ ድራማ ተጀመረ።
የዛሬውን ድራማ ከወትሮው በተለየ መልኩ አጓጊ ያደረገው፤ የአቃቤ ህግ ምስክር ሆነው የቀረቡት ግለሰብ ከሶስት ቀናት
በፊት አቃቤ ህግ ባቀረባቸው ሌላ ምስክር አንዴ “ሞተዋል”‚ አንድ ጊዜ “ተድብድበው ሞት አፋፍ ላይ ሆነው እያጣጣሩ ነው፤
እንደውም እስካሁን ህይወታቸው ሊቆይ አይችልም፤ አብቅተዋል” የተባሉ ሰው መሆናቸው ነው።ነገሩን በተከሳሽነትነት ለሚከታተል ብቻ ሳይሆን ለታዳሚዎች ሁሉ ሁኔታው እንቆቅልሽ ነው።በተለይ፦
“አማን በ አማን፣
ተንስአ እምነ ሙታን‛ እያለ እንደኔ ሲዘምር ላደገ ሰው፤‛ ኑር ሁሴን ከሞት ተነስቶ በቅንጅት ተከሳሾች ላይ ሊመሰክር ሲመጣ ማየት -እንዴት ግራ ያጋባል መሰላችሁ?
*** ***** ****
ድራማ ክፍል 1
ከጓደኞቹ እንደተረዳሁት፤ ኑር ሁሴን በምርጫ 97 ወቅት የንቧን ቲሸርት ለብሶ፦‛ኢህአዴግን ምረጡ!‛ እያለ በሳር ቤት አካባቢ
ሲቀሰቅስ የነበረ አነስተኛ ገቢ ያለው ግለሰብ ነው።ሆኖም የአዲስ አበባ ነዋሪ፦ “ምርጫችን ቅንጅት ነው” በማለቱ ሳይከፋው
አልቀረም። ቢያንስ በሰፈሩ ኢህአዴግ እንዲያሸንፍ ለማድረግ የነደፈው እቅድ እንደማይሳካ ሲረድ፤የምርጫውን መድረስ ተከትሎ
ከኢህአዴግ እየተሰፈረችለት ያለችው ስንቅ የምትቀርበት መሰለው። የሚይዘውን የሚጨብጠውን አጣ። በዚህ ሳይበቃው
“የቅንጅት ቀንደኛ ደጋፊዎች ሆነው ኢህአዴግ እንዲይመረጥ እንቅፋት እየፈጠሩ ያሉት እነ እገሌ ናቸው” ብሎ ከሚገምታቸው
ሰዎች ጋር በተድጋጋሚ ፀብ ይፈጥር ጀመር። የኑር ሁሴን አዲስ አመል የሰፈሩ መነጋገሪያ እስከመሆን ደረሰ።በዚህ መሀከል
ባልታወቁ ሰዎች በምሽት ተደብድቦ መንገድ ሊይ መውደቁ ተሰማ። የድራማው መቼት እዚህ ላይ በደንብ ተሰራ። እናም ኑር
ሁሴንን ማን መታው?? ማን ደበደበው?እነ መላኩ? ወይስ እነ መላኩን በህግ ቁጥጥር ስር ለማስገባት ሴራ የጠነሰሱ የደህንነት
ሀይሎች??የሚል ጥያቄ አንጠጥሎ ክፍል አንድ ቀጠለ....
አቃቤ ህግ ከቅንጅት መሪዎች ጋር በዘር ማጥፋት ወንጀል የከሰሳቸውን አምስት የአካባቢው ወጣቶች በኑር ሁሴን ድብደባ
ተጠያቂ አድርጓቸዋል።መላኩና ጓደኞቹ በቅንጅት ደጋፊነት መታሰራቸው እየታወቀ ለዚህ ነገር ተጠያቂ እንዱሆኑ የተፈለገው ፤
በክሱ ሂደት ሉቀርብባቸው የሚችል ማስረጃ ስላልተገኘ ነው።ምክንያቱም ወጣቶቹ ከደጋፊነት በዘለለ በቅንጅት ውስጥ
እዚህ ግባ የሚባል ሀላፊነት አልነበራቸውም። እናም ከሶስት ቀን በፊት የቀረበው የአቃቤ ህግ ምስክር፤ ኑር ሁሴን በነመላኩ
ድብደባ መሞቱን ለፍርድ ቤቱ ተናገረ፤ ወይም መሰከረ። የአምስቱንም ወጣቶች ማንነት በጣቱ በመጠቆም ጭምር አመሊከተ።
“ደብዳቢ እና ገዳይ” የተባለተ ወጣቶችም እየተባለ ያለው ነገር ፈፅሞ ስህተት እንደሆነ ለማስረዳት ቢሞክሩም ፤ለጊዜው ሰሚ አልተገኘም።
ዳኛው የምስክሩን ቃል መዝግበው አሰናበቱት።
ድራማ ክፍል 2
ይህ በሆነ በሶስተኛው ቀን ነው ዛሬ ኑር ሁሴን እንደ ኢየሱስ ተነስቶ የተገለጠልን። የንጉስ ልጆችም(አቃብያነ ህጎች)፦ የደረሰበትን ከፍተኛ ድብደባና ሰቆቃ በራሱ አንደበት ይገልፅ ዘንድ ኑር ሁሴንን ታሞ ከሚያጣጥርበት አልጋ ላይ እንዳመጡት ተናግረው ተቀመጡ። ተከሳሾችና ታዲሚዎች ብቻ ሳንሆን ችሎቱን የሚመሩት የመሀል ዳኛ ጭምር ግር ተሰኙ። ከቀናት በፊት በአሁኑ መስካሪ(ተጠቂ) ላይ - ሌላ ሰው የሰጠውን የ”ሞቷል” ምስክር አስታወሱ መሰል‛ ምንድነው ነገሩ?‛ በሚመስል ሁኔታ አንዴ ወደ መዝገባቸው፤ አንዴ ወደ አቃቤ ህጎቹ በማየት ነገሩን እንደገና ግልፅ ያድርጉላቸው ዘንድ ጠየቁ።
ልኡላኑም “ሞቷል..” ማስባላቸው ትዝ አላቸውና ፦
“ተከሳሾቹ ሞቷል እስኪባል ድረስ ክፉኛ እንደደበደቡት እና በህይወትና በሞት መካከል ጥለውት እንደሄዱ፣ ሆኖም ‘ኮማ’ ውስጥ ገብቶ ሞቷል ከተባለ በሁዋላ መትረፉን አሻሽለው በማብራራት፤ በህይወት ከተረፈ አይቀር የደረሰበትን አደጋ በራሱ አንደበት ይናገር ዘንድ እንዳመጡት እየተወለካከፉ ምላሽ ሰጡ። አዳራሹ ውስጥ ሳቅ ተሰማ። ዳኛው ታዳሚውንና ተከሳሾችን ስለመሳቃቸው ከተቆጡና ዳግም እንዲይለምዳቸው ካስጠነቀቁ በሁዋላ ከሞት የተነሳው ኑር ሁሴን ምስክርነቱን ይቀጥል ዘንድ ፈቀደ። ድራማው እየጦዘና አጓጊነቱ ይበልጥ እየጨመረ መጣ ።”ስክሪፕቱ” አሰልችና በቀሽም ደራሲ የተፃፈ ቢሆንም፤ ዋናው ገፀ-ባህሪ አሪፍ ስለነበር ተውኔቱን ህይወት ሊሰጠው ችሎአል። “የቲአትር ድርሰት ደረቅ አፅም ነው ፤ስጋና ደም አልብሰው ህይወት የሚሰጡት ጎበዝ ተዋንያን ናቸው” ‚ይባል የለ?አዎ! ኑር ሁሴን አሪፍ(genuine) ገፀ-ባህሪ ነበር።
እነሆ የገጸ- ባህርይው በቃት የታየበት ተከታይ ክፍል፦
የመሀል ዳኛው የደረሰበትን በአጭሩ ለፍርድ ቤቱ ይናገር ዘንድ ባቀረቡለት ጥያቄ መሰረት ኑርሁሴን የተፈፀመበትን ድብደባ ሆድ
እየባሰውና እያለቀሰ ብዙዎቻችንን ባሳዘነን ሁኔታ ተናገረ።
አዎ! ኑር ሁሴን ክፉኛ ተደብድቧል። ይህን ማስተባበል ከእውነት ጋር መጣላት ይሆናል።እንደውም ከሁኔታው ለመገመት
እንደሚቻለው ጠንከር ያለ በትር ሳያርፍበት አልቀረም።ይህ በማንም ዘንድ ተቀባይነት የሌለው ፀያፍ ድርጊት እስከሆነ ድረስ፤የኑር ሁሴን ደብዳቢዎች በህግ መጠየቅ የለባቸውም የሚል የለም። አብዩ ነጥብ፦ ”ደብዲቢዎቹ እነማን ናቸው? የሚለው ወሳኝ ጥያቄ መመለሱ ላይ ነው። እናም ዳኛው ቀጠሉ፦‛የመቱዎት እነማን እንደሆኑ ያውቃሉ?‛
“እ…እ…መላኩ፣ ..እእእ...ፈቃደ፣እእእ....ቻይና....‛ እያለ የጓደኞቹን(የአምስቱን ወጣቶች) ስም እየተንቀጠቀጠ ተናገረ። “ሞቷል” የተባለው
ኑር ሁሴን በአካል ሊመሰክር ሲመጣ ፊታቸው በደስታ የበራውና ነፃ እንደሚወጡ በሙሉ መተማመን እያንሾከሾኩ ሲነጋገሩ
የነበሩት አምስቱ ወጣቶች ፤ በራሱ ከኑር ሁሴን አንደበት “ደብዲቢ” ተብለው ሲመሰከርባቸው በድንጋጤ እጃቸውን አፋቸው ላይ
አኖሩ።‛ እንዴ ምነካው?‛ የሚል ድምፅም ንዴቱን መቆጣጠር ከተሳነው ከአንድኛው ወጣት ተሰማ። አቃቤ ህጎቹ የስነ
ስርአት ጥያቄ አስከተሉ፤ ዳኛው ተናጋሪውን ወጣት ገሰፁ፤ ድራማው ቀጠለ...
አሁን ኑር ሁሴን በአካል ተነስቶ “ደበደቡኝ” ያላቸውን ጓደኞቹን በጣቱ እየጠቆመ የሚያሳይበት ክፍል ነው።”ደብዳቢ” በተባሉት
ወጣቶች መደድ የተቀመጥን ተከሳሾች በሙሉ ከመቀመጫችን እንድንነሳ ዳኛው ጠየቁ፤ሁላችንም ተነሳን።ከተነሳነው ውስጥ እነ መሊኩን፣እነ ፈቃደን፣አነ ቻይናን እየጠቆመ እንዲያሳይ ኑሩ ሁሴን ተጠየቀ። ኑር ሁሴን በስግታ እየተራመደ ወደ እኛ መጣ፤ ነገሩ ሳያስጨንቀው አልቀረም። “ደበደቡኝ” ብሎ ወደመሰከረባቸው ጓደኞቹ ሲደርስ ከውስጡ ጋር የሚሟገት ይመስል ነበር። ለመጠቆም በጣም ዘገየ። መሀል ዳኛው “ልትለያቸው አልቻልክም ማለት ነው?” እስኪጠይቁት ድረስ አጠገባቸው ደርሶ በዝምታ ቆመ። መጨነቁን የተመለከቱት ተከሳሽ ጓደኞቹም ያለ ምንም ፍርሀት፦‛ኑር ሁሴን፤ እዚህ ነን‛ ብለው እንደ ወትሮው በፍቅር ጠሩት።እሱም ተከትሎ እየሳቀ ፦‛እኚሁት‛አለ።እየጠቆማቸው እርስ በርስ ተሳሳቁ። ሁላችንም እስክንስቅ ድረስ ነገረ-ስራቸው ግራ አጋባን። ዳኛው የተለመደ ቁጣቸውን ካሰሙ በሁዋላ ኑር ሁሴን ቦታውን እንዱይዝ አዘዙ ።አስከትለውም ተከሳሾቹ መስቀለኛ
ጥያቄ ካላቸው ኑርሁሴንን መጠየቅ እንደሚችሉ አሳወቁ፤ድራማው ውበቱን እየጨመረ ወደ መጠናቀቂያው ደረሰ...
የመጨረሻው ክፍል(መስቀለኛ ጥያቄ)
ተከሳሽ ፈቃዱ፦”ኑር ሁሴን እኔ አንተን መትቼሀለሁ?”
ኑር ሁሴን፦”ፈቃደ ጓደኛዬ ፤ ገንዘብ አበዳሪዬ፤ የልብ ምስጢረኛዬ ...በፍፁም አልመታኸኝም” አዲራሹ በከፍተኛ ሳቅ ተናጋ።
የአቃቤ ህጎቹ አይን ከመቅፅበት ደም መሰለ።ዳኞቹ ግራ ተጋቡ።ፈቃዱ ፦‛ይኸው ይመዝገብልኝ፤ጥያቄየን ጨርሻለሁ”ብሎ
ተቀመጠ። ተከሳሽ መላኩ በተራው ተነሳ፦
“ኑር ሁሴን እኔ አንተን መትቼሀሇሁ?”
ኑር ሁሴን፦”መሊኩ ጓደኛዬ፤ ፀጉሬን አስተካካዬ፤ወንዴሜ ፣መካሪዬ....‛ የብዙዎቻችን ሳቅ የአዲራሹን ጣራ ሰንጥቆ ወጣ።አቃቤ
ህጎቹ በመሀከል ገብተው ለመናገር ቢፈልጉም ጊዜው የመስቀለኛ ጥያቄ ነበርና አልተፈቀደላቸውም። መላኩም፦“ይኸው ይመዝገብልኝ፤
ጥያቄየን ጨርሻለሁ” ብሎ ተቀመጠ።ቻይና እና ሌሎቹም ለጊዜው ስማቸውን የዘነጋሁዋቸው ሁለት ወጣቶች እንደዚሁ
ተመሳሳይ ጥያቄ በማቅርብ ንፅህናቸውን አረጋገጡ።በሁኔታው በጣም ግራ የተጋቡት ዳኛም፦” አቶ ኑር ሁሴን ቅዴም ማነው የደበደበዎት ተብለው ሲጠየቁ፤ እነ መላኩ፣ እነ ፈቃዱ፣እነ ቻይና....ናቸው እያሉ መስክረው ሲያበቁ፤ አሁን በመስቀለኛ ጥያቄ ላይ እንዴት አልደበደቡኝም ይላሉ? ነገሩን ግልፅ ሉያደርጉልን ይገባል! እነ መላኩ ደብድበዎታል?ወይስ አልደበድቡዎትም?”
ኑር ሁሴን፦‛አልደበደቡኝም!‛
ዳኛ፦‛ቅድም ለምን ደብድበውኛል አሉ?’
ኑር ሁሴን፦‛ጧት እቤቴ መጥተው እንደሱ በል ብለውኝ ነው‛
ዳኛ፦‛ማናቸው እንደሱ በሉ ያለዎት?‛
ኑርሁሴን፦‛መንግስት፣የመንግስት ፖሉሶች‛ ........የአቃቤ ህጉቹ የማያባራ ‚ስነ ስርአት !ስነ-ስርአት!‚ያልገደበው የማያባራ
ሳቅ................ሳቅ.......................
.የእለቱ ድራማ በዚሁ ተጠናቀቀ።
***********************************
ኑር ሁሴን ከህሊናው ጋር ታረቀ።ከአቃቤ ህጎቹ ቁጣና ማባበል የጓደኞቼ እውነት ይበልጥብኛል አለ።የአምላክ ነፍስ በብርቱ
ከምትፀየፋቸው ነገሮች ዋነኛው፦‛በወንድማማቾች መካከል ፀብ የሚዘራን‛ እንደሆነ ታላቁ መፅሀፍ ይነግረናል።በኑር ሁሴንና በነ
መላኩ መካከል ፀብ የዘሩት ወገኖች እንደ ሀገርም ያቆየነውን የመዋደድ፣ የመከባበርና አብሮ የመኖር እሴት ፤በሀይማኖትና በዘር እሳት
ለመሸርሸር እንቅልፍ አጥተው መራወጥ ከያዙ ጥቂት የማይባሉ ዓመታት አለፉ። በጓደኛሞቹ በኑር ሁሴንና -በነመላኩ ላይ
የተሞከረው ነገር ፤የትልቁ “በታትነው ‚ፖሲሲ” ነፀብራቅ ነው።ግን አልተሳካም።በወቅቱ ፈቃዱ እንደነገረኝ ከሆነ ከእስር ሲፈታ የልብ ጓደኛ ከሚያደርጋቸው ሰዎች መካከል አንዱ- ኑር ሁሴን ነው።
ድራማው በዚህ መልክ ቢጠናቀቅም ችሎቱ በሌሎች ቀናት ቀጠለ...ቀጠለ...በእነዚህና በሌሎች መሰል አስቂኝ ማስረጃዎች ፍርድ ቤቱ በእነኢንጅነር ሀይለ ፋይሌ በተከሰሱ የቅንጅት መሪዎች፣የሲቪሌና የሙያ ማብበራት መሪዎችና ጋዜጠኞች ላይ የዕድሜ ልክ እስራት ፈረደ።
ምክንያት?
ይኽ የግንቦት 20 ፍርድ ቤት ነው።

No comments:

Post a Comment