ኦሮሚያ ክልል አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች በተፈጠረ ግርግር ሆነ ተብለው በተሰራጩ አሳሳች አሉባልታዎችና ሃሜታዎች የተደናገሩ የተወሰኑ ተማሪዎች በፈጠሩት ሁከት በክልሉ በሚገኙ የተወሰኑ ዩንቨርስቲዎች በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል ብሏል፡፡ ማን ? የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት
በአምቦ ዩኒቨርስቲ የተቀሰቀሰው ሁከት ወደ ከተማ በመዝለቁ እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት በአምቦ ከተማ ቢዝነስና ኮንስትራክሽን ባንክ ላይ በተደረገው የዘረፋ ሙከራና ሌሎችም ህገ ወጥ የነውጥ እነቅስቃሴዎች በአምቦና ቶኬኩታዮ ከተሞች የሰባት ሰዎች ህይወት እንዳለፈና ባንኩን ጨምሮ በበርካታ የመንግስትና የሀዝብ ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተመልክቷል፡፡ (ባንክ ሊዘርፉ ሲሉ ነው የተገደሉት ማለታቸው ነው :: ወያኔ ያደረገውን ግድያ ለማስተባበል እየሞከረ መሆኑን ያሳያል )
የእግር ኳስ ሲመለከቱ የነበሩ ሰዎች ላይ ፈንጂ ተወርውሩ ወደ 70 ሰው መቁሰሉና ሌሎችም ተዘግበዋል:: ይህ የወያኔ ማስተባበያ እና ሰውን ለማስፈራራት የተዘገበ ነው በነገራችን ላይ ከ30 በላይ ወጣቶች መገደላቸውን ሰምተናል ነገር ግን እነዚህን ወታቶች ፌደራል ለመግደሉ አልተዘገበም ::
ይሄ አገዛዝ ያሰራል ከዛ ወንጀል ይፈልጋል እንጂ ወንጀሉን ተከታትሎ አስሮ አያውቅም ሁሌም ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ ግዜ ይሰጠኝ በማለት ጥያቄ ያቀርባል ግዜው ይሰጠዋል ከዛ ወንጀሉን እራሱ ፈጽሞ እራሱ ይከሳል ታዲያ ይሄን እያያችሁ መንግስት እና ህግ አለን ትላላችሁ ????
source-Mitmita
No comments:
Post a Comment