እንደሰሞኑ የኢትዬጵያን ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ወቅት የለም ማለት ይቻላል ። ዘርኝነት የመጨረሻው ምእራፍ ላይ በከፍተኛ ፍጥነት እዬተምዘገዘገ ነው። በኦሮሞ ተማሪዎች የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም በሚል ሽፋን እልም ያለ የዘረኝነት ምግባር ታይቷል። የፈረደባቸው የአማራ ተወላጆች ዛሬም ሂዎታቸው ተቀጥፏል። ንብረታቸው ወድሟል ። አማራ ስለሆኑ ብቻ!! ህወሓት እያራመደችው ያለውን ዘረኝነት ግብ በማስመታት ደረጃ ተማርኩ የሚለውን የኦሮሞ ወጣት የሚደርስበት ጠፍቷል።
የአማራ ህዝብ ምን ያህል በችግር እዬተጠበሰ …በዲሞክራሲ እጦት እዬተሰቃዬ… እንደሆን ፅንፈፆቹ የኦሮሞ ወጣቶች ሊረዱለት አልቻሉም። ሆዱን በጠፍር እያሰረ ያሰተማራቸው ልጆቹ ከዛሬ ነገ ዩንቨርስቲ ተመርቀው ወጥተው ራህቤን ያስታግሱልኛል ሲል በዘረኝነት በአበዱ ፅንፈኞ እዬተቀጠፉነው።ለኦሮሞ ህዝብ ነፃነት ስንታገል የአማራን ህዝብ ነፃነት እዬጨፈለቅን ከሆነ ትልቅ ስህተት ነው።
የኦሮሞ ወጣቶች እባካችሁ አስተውሉ!! ለኦሮሞ ህዝብ ጠላቱ አማራ፣ትግሬ……አይደለም። ስርአት ነው። ያን ሥርአት ደግሞ ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ የቀመሰው ነው። በጋራ ሆነን ህወሓት የተባለ የማፍያን ስርአትን ታግለን ስንጥል ነው ነፃ ልንወጣ የምንችለው ። እንደሰሞኑ ከሆነ ግን እንጨራረሳለን እመኑኝ!! የህወሓትን ድራማ ልብ ማለት አቅቶናል።
እባካችሁ… ከአማራ ህዝብ ላይ እጃችሁን አንሱ!! የእኛ እንዲህ መሆን ከህወሓት ሰርግ እና ምላሽ ነው። አማሮች በአክራሪ ኦሮሞዎች ተገደሉ ኦሮሞዎች ደግሞ በአጋዚ ጥይት ተለቀሙ። ማን ተጎዳ ማን አተረፈ? ልብ ያለው ልብ ይበል!!!
source -
No comments:
Post a Comment