Monday, June 2, 2014

በደብረብርሃን ወያኔ ሞባይል ፍተሻ ላይ ተሰማርቷል

በደብረብርሃን ወያኔ ሞባይል ፍተሻ ላይ ተሰማርቷል። ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎DebreBirhan‬
"መጀመሪያ የሚፈተሸው የተጠቀምከው ድህረገጽ ነው።" ነዋሪዎች 
በሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን የወያኔ የደህንነት ሃይሎች የነዋሪዎችን ሞባይል በመፈተሽ እንዲሁም የሞባይል ጠጋኞችን በማስገደድ ሊሰሩ የመጡ ሞባይሎችን ከተጠገኑ በኋላ ባለቤቶቻቸው እጅ ሳይደርሱ ከነሚሞሪው በመፈተሽ እና እንዲሁም የሞባይል ኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን በመለየት በቀጥታ በየጊዜው የሚፈትሹት የተጠቀሟቸውን ድህረገጾች እና የማህበራዊ ሚዲያ እንቅስቃሴዎቻቸውን መሆኑ ታውቋል።
የሞባይል ጠጋኞቹ እንደሚሉት ንብረቶቻቸው እና ሙዚቃ የሚጭኑባቸው ኮምፒዩተሮች ሳይቀሩ የተወሰዱ መሆን በመናገር ለጸጥታ ሃይሎች ለመተባበር ፍቃደኛ ካልሆኑ ንብረቶቻቸው እንደማይመለሱ እና እንዲሁም ከዛሬ ነገ እንታሰርለን በሚል ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንዲገቡ የደህንነት ሃይሎቹ ሽብር እየፈጠሩ መሆኑን ከስፍራው የመጣ መረጃ ያመለክታል።
የገንዘብ ጥማት ያለባቸውን ፖሊሶች በማስከተል ከግንቦት የመጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ አፈሳ ፍተሻ እና ወከባ የሚያካሂዱት የደህንነት ሃይሎች የሞባይል ጥጋኞችን እና ሙዚቃ በመጫን የሚተዳደሩትን ኮምፒዩተሮቻቸውን በመውሰድ ....ኮምፒዩተሩ ባዶ ሆኖ ቢገኝ እንኳን በሪከቨሪ ሶፍትዌር በባለሙያዎች ተደጋጋሚ ምርመራ እየተደረገ ዜጎችን በማንገላታት በማሰር ፍርድ ቤት ድረስ በማቅረብ 2000 ብር ዋስሰንDኢጠሩ ያስደረጉ ቢሆንም ፍርድ ቤት የሚሰሩት ስራ ህጋዊ ስለሆነ አያስከሥም በማለት በነጻ ቢያሰናብትም የደህንነት ሃይሎቹ እያሰሩ በመፍታት ከህግ በላይ እያሰቃይዋቸው መሆኑን አክለው ገልጸዋል።

ማዕከላዊ ማጎሪያ ሄጀ ነበር፡፡

ትላንት በነበፍቄ የፍርድ ሂደት ሊታደም ሄዶ መታወቂያው ተውሰዶ ሰኞ ማእከላዊ ቅረብ የተባለው ጋዜጠኛ በላይ ማናየ ዛሬ ሄዶ የገጠመውን ያወጋናል
ልታሸብሩኝ አትሞክሩ!
ማዕከላዊ ማጎሪያ ሄጀ ነበር፡፡
ዕሁድ በአራዳ ምድብ ችሎት የዞን 9 ጦማሪዎችን የፍርድ ውሎ ለመከታተል በቦታው ነበርኩ፡፡ ችሎቱ በዝግ ታዬ፤ ምንም አላልንም፡፡ ከውጭ ጠብቀን የፍርድ ውሳኔውን ለመስማት ስንጓጓ ምንም ሳንሰማ የፍርድ ቤቱን ግቢ ለቅቀን እንድንወጣ ታዘዝንለ፡፡ ወጣን፡፡ በዚህ ሳያበቃ ደግሞ ከግቢው ውጭም እንድንርቅ አዘዙ፡፡ ይህኔ ወደፍርድ ቤቱ የሄድነው የፍርዱን ውሳኔ ለመስማትና ወዳጆቻችንን ለማየት እንደሆነ ገልጬ ‹ለምን እንወጣለን?› ብዬ በመጠየቄ ከሰው ለይተው አገቱኝ፡፡
እገታው ለአጭር ጊዜ የቆየ ቢሆንም በጣም ዘግናኝ ስድቦችንና ጥያቄዎችን ሰንዝረውብኛል፡፡ መጠየቄ ወንጀል ሆኖባቸው ያለ የሌለ ማስፈራሪያና ዛቻ አውርደውብኛል፡፡ በዚህም ሳያበቁ መታወቂያየንና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የያዘ ካርዴን ነጥቀውኛል፡፡ ለምን ብዬ ስጠይቅ ምላሽ አልነበራቸውም፡፡ ከዚያ ይልቅ ዛሬ ሰኞ ማዕከላዊ ማጎሪያ ድረስ እንድቀርብ ትዕዛዝ አወረዱ፡፡
እናም ዛሬ ማዕከላዊ ሄጄ ነበር፡፡ በቅጡ የሚናገርም የሚያዳምጥም የለም፡፡ መታወቂያየን እንዲመልሱልኝ ለመጠየቅ እንኳ እድሉን ላገኝ አልቻልኩም፡፡ በር ላይ ያለው ሰው አድራጊ ፈጣሪ ሆኖ ቀረበ፡፡ አብሮኝ የነበረው ጓደኛዬ ብርሃኑ በጥሞና ሊያስረዳው ሞከረ፤ መስሚያም የለው!
ከግቢው ዞር እንድንል አዘዘ፡፡ አሁንም ግን ልናስረዳው ሞከርን፡፡
‹‹መታወቂያህን አልወሰድንም….ማን ነው የወሰደብህ…..የወሰዱብህን ሰዎች ስም ጥራ›› አለኝ፡፡
ስማቸውን እንዴት ላውቅ እችላለሁ? ማንስ እንድጠይቅ ፋታ ሰጠኝ?
‹‹ነገ መጥተህ ሪፖርት አድርግ፤ መታወቂያህ ከእኛ ጋር ይቆያል›› ነበር ያሉት ትናንት መታወቂያየን ሲነጥቁኝ፡፡
‹‹የት…ማን ብዬ ልጠይቅ?››
‹‹ቦቃ ማዕከላዊ ዙም ብለህ ና አልኩህ፤ ምን ቾገር ትፈጥራለህ!›› ሲቪል የለበሰ ኮሳሳ ሰውዬ አንቧረቀብኝ፡፡
እና አሁንም እያደነጋገሩ ሊያሸብሩ ነው የሚሞክሩት፡፡ ስርዓቱን አውቀዋለሁና አዲስ ነገር አልሆነብኝም፡፡ ደስ ባላቸው ጊዜ ይጠራሉ፤ ያስራሉ፤ ይገድላሉ…እነሱ ብቻ አዋቂ፣ እነሱ ብቻ ተናጋሪ ናቸው፡፡
ደግሞ እኮ ብዙ ጊዜ እንደ ለማዳ ውሻ ከኃላ ከኋላዬ የሚከተሉኝ ሰዎቻችሁንም ተላምጃቸዋለሁ፡፡ ስለእኔ መረጃ ለመሰብሰብ እንዳልሆነ ይገባኛል፡፡ እናንተ የምትከተሉኝ ከማን ከማን ጋር እንደምገናኝ ለማወቅ ነው፡፡ የመረጃ ምንጮቼን ለማስፈራራት ነው፡፡ ይህን ደግሞ ራሳችሁም ነግራችሁኛል፡፡
እናንት የማዕከላዊ ሰዎች…መታወቂያየን ብትመልሱልኝ ደስ ይለኛል፤ ልማጸናችሁ ግን አልፈልግም፡፡ እናንተ እንደሆን ህግን አትፈሩም፤ አታከብሩም! ግን ግን ልታሸብሩኝ አትሞክሩ፤ ስራዬን ጠንቅቄ አውቃለሁና አልሸበርም! እኔ ሰላማዊ ሰው ነኝ፡፡
እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው፣ መቼም ቢሆን ከምወደው ስራዬ ፈቅ እንደማልል ነው!
ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም!

Sunday, June 1, 2014

በትግራይ አለመረጋጋት አለ! ወያኔ ደንግጧል!!!

በትግራይ አለመረጋጋት አለ! ወያኔ ደንግጧል!!!
====================
አብረሃ ደስታ
ጓዶች ህወሓቶች በጣም ደንግጠዋል። ባሁኑ ሰዓት በብዙ የሑመራ አከባቢዎች፣ ማይጨው (ሽኮማዮ)፣ ዓዲጎሹ (ተከዘ)፣ ሐውዜንና አፅቢ ህዝቡን ለመቆጣጠር ፖሊሶችና ምልሻዎች ተሰማርተዋል። ትናንት ማታ (ቅዳሜ ማታ) አቶ መሰለ ገብረሚካኤል (የዓረና ስራ አስፈፃሚ አባልና የምዕራባዊ ዞን የዓረና አስተባባሪ) ፊታቸው በሸፈኑ ታጣቂዎች ወደ ፖሊስ ጣብያ ተወስደው ምርመራ ተደርጎባቸዋል። ትናንት ቅዳሜ በእንዳ አብርሃ ወ አፅብሃ የዓረና ልሳን ለህዝብ ሲያድሉ የነበሩ የዓረና አመራር አባላት አቶ ዓምዶም ገብረስላሴ፣ አቶ ቴዎድሮስ ሞገስ ፣ አቶ ኃይለኪሮስ ታፈረና መምህር ይልማ ኩኖም በህወሓት አስተዳዳሪዎች ክፉኛ ተደብድበው ሆስፒታል ገብተዋል። አቶ ቴዎድሮስ ሞገስ ተደብድቦ በፖሊስ ታስረዋል። አቶ ገረችአል ግደይ (አባ ሐዊ) የተባለ ያከባቢው አስተዳዳሪ አቶ ቴዎድሮስን እንዲታሰር ስለወሰነ በሚል ምክንያት በዉቅሮ ከተማ ታስሮ ይገኛል። አሁን የእንዳ አብርሃ ወ አፅብሃ አከባቢ በፖሊሶች እየተጠበቀ ነው።
ሁለትና ከሁለት በላይ ሁኖ መንቀሳቀስ ተከልክሏል። ከምሽቱ ሁለት ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ አይፈቀድም። በአፅቢ ወንበርታ ላለው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለመግታት የተቃውሞው መሓንዲስ የተባለውን አቶ ሕድሮም ሀይለስላሴን በሰበብ አስባቡ ለማሳሰር ዝግጅት መጀመሩ ከህወሓት ፅሕፈትቤት መረጃ ደርሶኛል። በሐውዜን ከተማ ዓረና ተብሎ የተጠረጠረ ሁሉ ድብደባ ተፈፅሞበታል። ከሐውዜን እንዲወጣም እየተደረገ ነው። አሁን እሁድ ግንቦት 24, 2006 ዓም ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ በእግሪሓሪባ መንደር ብዙ ቁጥር ያላቸው ፖሊሶች ተሰማርተዋል። አቶ ሙኡዝ ፀጋይ የተባለ ያከባቢው የዓረና አስተባባሪ ቤት ተከቧል። መንቀሳቀስ አይችልም። በያንዳንዱ የእግሪሓሪባ መኖርያቤት በር ሦስት ፖሊሶች ይገኛሉ። ዛሬ በህዝቡና አስተዳዳሪዎች አለመግባባት ተፈጥሮ ነበረ። ባጠቃላይ ባሁኑ ሰዓት በትግራይ አለመረጋጋት አለ። ይህን ሁሉ ችግር እየፈጠረ ያለ ግን ህወሓት ራሱ ነው። ከሰለማዊ ተቃውሞ ዉጭ ምንም ዓይነት ዓምፅ በሌለበት ህዝቡ ሊያምፅ ይችላል በሚል ስጋት ብቻ የፀጥታ ሃይሎች እያሰማራ ነው። ህዝቡም ተደናግጧል። እኛ ግን ብዕር እንጂ ጠመንጃ አልያዝንም።
በትግራይ አስቸኳይ መፍት ሄ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ተባራክተዋል። መነጋገር ይኖርብናል።

ሶስቱ የዞን 9 ጦማርያን "የፍርድ ቤት" ቆይታ

የሶስቱ የዞን 9 ጦማርያን "የፍርድ ቤት" ቆይታ
ለዛሬ ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ተጠይቆባቸው የነበረው ሶስቱ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን ማህሌት ፋንታሁን በፍቃዱ ሃይሉ እና አቤል ዋበላ ላይ ተጨማሪ 28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተሰጠ፡፡ ፓሊስ የጠየቀው 28 ቀን የተፈቀደለት ሲሆን ማንም የቤተሰብ አባል ችሎቱ ውስጥ ያልተገኘበት ዝግ ችሎት ነበር፡፡
ጦማርያኖቹ ለደቂቃዎች ችሎቱ ውስጥ ቆይተው ከመውጣታቸው በፌት ጊቢ ውስጥ ያሉ ቤተሰብ ጓደኞች ዲፕሎማቶች እና ሌሎች ሊከታተሉ የመጡ ሰዎችን ከግቢው አንዲወጡ ፓሊስ አስገድዷል፡፡ በዚህም የተነሳ ወደ "ፍርድ ቤት" ጊቢው ሲገቡ አንጂ ሲወጡ ቤተሰብና ወዳጅ ሊያያቸው አልቻለም፡፡ በዛሬው ችሎት ቤተሰብ አባላት ላይ ከፍተኛ ወከባና እንግልት የደረሰ ሲሆን ብዙ የቤተሰብ አባላትና የቅርብ ጓደኞች ሲያለቅሱ ታይተዋል፡፡
ማህሌት አቤልና በፍቃዱ በጠንካራ መንፈስ ላይ ሆነው የታዩ ሲሆን 28 ቀን መፈቀዱም ክሳቸው በጸረ ሽብር ህጉ እንደሚታይ ያመለክታል፡፡
የዞን9 ጦማሪያን ጓደኞቻችን ምንም አይነት የወንጀል ተግባር ላይ ተሰማርተው እንደማያቁ እና ክሳቸው ፓለቲካዊ እንደሆነ እያስታወስን በፍርድ ቤት ተገኝተው አጋርነታቸው ላሳዩ ከ120 በላይ ለሆኑ የዞን ዘጠኝ ወዳጆች ልባዊ ምስጋናችንን በታሰሩ ጓደኞቻችን ስም እናቀርባለን!

‹‹ጥያቄ አለኝ››

‹‹ጥያቄ አለኝ››
ጥያቄውም የዜግነት መብት እንዲከበር ነው፤
አያምጣውና እንዳንል መጣብን እንጂ፡፡ ርሃብ፣ ችጋር፣ ጉስቁለናና፣ ጦርነት፣ ግፍ፣ ኢ-ፍትሃዊነት፣ አድሎዎና መድሎዎ ስጠሪረን፣ እንደ መዥገር የሙጥኝ/አልላቀቅ ሲል ‹‹እሪሪ›› ማለት በየትኛውም ዓለም አከባቢ የተለመደ ነው፡፡ ከእኛ ከኢት/ያዊያን ይህ ‹እሪታ ተለይቶብን አያውቅም ብል ማጋነን አይሆንብንም፡፡ ታዲያ በዚህን ወቅት እሪታው ቢያንሰን ነው እንጂ በፍጹም የሚበዛብን አይሆንም ባይ ነኝ፡፡ ለእሪታ ያበቃን ጉዳይ በኢህአዴግዊያን ዘንድ የዕቃ ዕቃ ጨዋታ ልመስላቸው ይችላል፡፡ ልማታዊ ጋዜጠኛ ከበደ ካሣ እንዳለው ማለቴ ነው፡፡ ሰብሰብ ሳደርገው በአንድ ሀገር ከሁለት በላይ ዜጎች ሆን ተብሎ እንዲፈጠሩ ሲደረግ፤ በኑሮ ተከፍተውና ቀኑ ሲጨልምባቸው፣ ገምሱ ጠግቦ ሲያገሣ፣ በተቃራኒው ያለው አጥቶ ሲያዛጋ፤ . . . ምንም እንኳ ይህ ሰው ሰራሹ የምድራዊው ውጣ ውረዱ የኢህአዴግ,ን ቤተሰቦች ይነካል ብለን ለመሞገት ቢናስብ፤ አሁንም የዕቃ ዕቃ ጨዋታ ቢመስለኝም …፤
ነገሯን በወጉ የታዘበው ‹‹አንድነት ለዴሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ (አንድነት)›› ሕዝቡ አለን! የሚለውን ችግር ይዞ ወደ አደባባይ በመውጣት ድምጹን ያሰማ ዘንድ አጀንዳ ቀርጾ ቀን ቆርጦ፣ ቦታ (እንደተወለድኩበት አከባቢ አጠራር ‹‹ዱቡሻ››) ጠቁሞ፣ በጡሩንባ አስነግሮ ነበር፡፡ ይሄንን ለመከወን ግን ፓርቲዩን የገጠመው ውጣ ውረድ መተረክ ለቀባሪዩ . . . እንደማለት ስለሆነ ማንንም ሳላስፈቅድ ትቼው፡-
‹‹ቀኑ “የእሪታ ቀን” ነበር፡፡ በ2006 ዓ.ም ዕለተ ዕሁድ ሚያዝያ 26ቀን፡፡ ከሕዝብ ቁጥር አንጻር ከምርጫ-97 ወዲህ ትልቁ የተባለለትና በአደባባይ ሕዝብ የጮኸበት ዕለት፡፡ እኔና ጓዳኞቼ ከያለንበት ተጠራርተን፣ አንቀርም ተባብለን ተሳትፈናል፡፡ አዎን! አሁንም …ምላሹን በክብር እስካገኝ ድረስ እጠይቃለሁ! እጮሃለሁ! በእምባዬ እታጠባለሁ! ገና እሰለፋለሁ! ከዚህ ሌላ ሞት የለምና፡፡ አዎን! አሁን እየጠየቅን ያለነው ጥያቄ ስለ ዜግነት መብት ጥያቄ ሳይሆን ‹‹ዜግነቴ ዕውቂና ያግኝ›› ነውና በፈጣሪና በዓለም ሕዝብ ፊት መቆመን እቀጥላለሁ!!
‹‹ጥያቄ አለኝ! እንዲያስረዱኝም እንዲመልሱልኝም እፈልጋለሁ፡፡ …ይቀጥላል! በዚህ ተሳትፎ ብቻም ሳልገታ እንደ አባቶቼ፣ እንደ ታላላቆቼ፣ እንደ . . .፤ እኔም እንደ አቅሚቲ ትግሉን ለማገዝ ቆርጫለሁ፡፡ በጉልበት፣ በሀሳብ፣ በገንዘብ . . . አቅም በፈቀደው፣ ፈጣሪዬ በሬዳኝ መጠን ሁሉ …፡፡ ለዚህም አንዱ መገለጫዬ በፎቶዬ ላይ እንደሚታዩት የአንድነት ፓርቲ (UDJ) ያዘጋጀውን የገንዘብ ዋጋ ያለውን ባለ100ብር ኩፖን ባለቤት መሆኔ፤ ሲጤራ አቤት?! ሲልኩት ወደት?? ቀጠሯችን አክብሬ መገኘቴ ወ.ዘ.ተ ነው፡፡ ይህም ‹‹ለሀገሬ ጥቅም፣ ለፍትህና ለህልናዬ ዳኝነት›› የምሰጠው ወቅታዊ ምላሽ ነው፤ ለ‹‹እውነት››የምከፍለው ዋጋ ነው፡፡ እርሶዎስ ምን ያስባሉ?? …?? ከወደዱ ላይክ/ሸር (Like/Share) ይበሉ/ያደርጉ…፤ ቸር ያሰማን፡
Like ·  · 

ሶስቱ የዞን 9 ጦማርያን "የፍርድ ቤት" ቆይታ

ሶስቱ የዞን 9 ጦማርያን "የፍርድ ቤት" ቆይታ
ለዛሬ ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ተጠይቆባቸው የነበረው ሶስቱ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን ማህሌት ፋንታሁን በፍቃዱ ሃይሉ እና አቤል ዋበላ ላይ ተጨማሪ 28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተሰጠ፡፡ ፓሊስ የጠየቀው 28 ቀን የተፈቀደለት ሲሆን ማንም የቤተሰብ አባል ችሎቱ ውስጥ ያልተገኘበት ዝግ ችሎት ነበር፡፡
ጦማርያኖቹ ለደቂቃዎች ችሎቱ ውስጥ ቆይተው ከመውጣታቸው በፌት ጊቢ ውስጥ ያሉ ቤተሰብ ጓደኞች ዲፕሎማቶች እና ሌሎች ሊከታተሉ የመጡ ሰዎችን ከግቢው አንዲወጡ ፓሊስ አስገድዷል፡፡ በዚህም የተነሳ ወደ "ፍርድ ቤት" ጊቢው ሲገቡ አንጂ ሲወጡ ቤተሰብና ወዳጅ ሊያያቸው አልቻለም፡፡ በዛሬው ችሎት ቤተሰብ አባላት ላይ ከፍተኛ ወከባና እንግልት የደረሰ ሲሆን ብዙ የቤተሰብ አባላትና የቅርብ ጓደኞች ሲያለቅሱ ታይተዋል፡፡
ማህሌት አቤልና በፍቃዱ በጠንካራ መንፈስ ላይ ሆነው የታዩ ሲሆን 28 ቀን መፈቀዱም ክሳቸው በጸረ ሽብር ህጉ እንደሚታይ ያመለክታል፡፡
የዞን9 ጦማሪያን ጓደኞቻችን ምንም አይነት የወንጀል ተግባር ላይ ተሰማርተው እንደማያቁ እና ክሳቸው ፓለቲካዊ እንደሆነ እያስታወስን በፍርድ ቤት ተገኝተው አጋርነታቸው ላሳዩ ከ120 በላይ ለሆኑ የዞን ዘጠኝ ወዳጆች ልባዊ ምስጋናችንን በታሰሩ ጓደኞቻችን ስም እናቀርባለን!