ፖሊስ ሊመሰረት ያሰበው የሽብርተኝነት ክስ በፍርድ ቤቱ ውድቅ ተደረገ
(By Bisrat Woldemichael)
ዛሬ እሁድ ግንቦት 10 ቀን 2006 ዓ.ም. አራዳ በሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት በፍቃዱ ኃይሉ፣ አቤል ዋበላ እና ማህሌት ፋንታሁን ከረፋዱ 4፡20 ቀርበው ነበር፡፡ ይዟቸው የመጣውና እስካሁንም መደበኛ ክስ ያልመሰረተው የማዕከላዊ ፖሊስ ምርመራዬን አልጨረስኩም፣ ጉዳዩ ከሽብር ጋር ስለሚያያዝ ተጨማሪ የ 28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ ሲል ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል፡፡
ፍርድ ቤቱም ከዚህ በፉት ለ24 ቀናት አስራችሁ ያቀረባችሁት ከሽብር ጋር የተያያዘ ባለመሆኑ እና ሌላ አዲስ ሂደት ስለሌለ ከዚህ በፊት ያላቀረባችሁትን ከሽብር ጋር የተያያዘ የሚለውን ጭብጥ አልቀበልም፣ ተጨማሪ የ28 ቀናት የምርራ ጊዜ የተጠየቀውም ተገቢ አይደለም ካለ በኋላ የ14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ በመስጠት ለእሁድ ግንቦት 24 ቀን 2006 ዓ.ም. ጠዋት ተለዋጭ ቀነ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ፍርድ ቤቱም ፖሊስ ያቀረበውን ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ የሚውን ውድቅ አድርጎታል፡፡
ትናንት ግንቦት 9 ቀን 2006 ዓ.ም. የነበረው የ 6ቱ ጋዜጠኞች እና ብሎገሮች ፖሊስ ጉዳዩን ከሽብር ጋር አያይዞ ተጨማሪ የ28 ቀናት የጠየቀው ተፈቅዶለት ለሰኔ 7 ቀን 2006 ዓ.ም. ጠዋት ተለዋጭ ቀነ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል፡፡ ትናንት የነበረው የ6 ቱን ጉዳይ የተመለከተው ዳኛ ወንድ ሲሆን የዛሬውን ጉዳይ የተመለከተችው ዳኛ ሴት መሆኗ ተጠቁሟል፡፡
No comments:
Post a Comment