Saturday, May 31, 2014

አረብሳት ከኢትዮጵያ የሞገድ አፈና እየተደረገብኝ ነው አለ

አረብሳት ከኢትዮጵያ የሞገድ አፈና እየተደረገብኝ ነው አለ
31 May, 2014 Written by addis admassnews
ካቻምናም ታፍኛለሁ፣ ዘንድሮ ግን በህግ እጠይቃለሁ ብሏል
ተቀማጭነቱን በሳዑዲ አረቢያ ያደረገውና በርካታ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚያሰራጨው የአረብ ሳተላይት ኮሙኒኬሽን ተቋም (አረብሳት) ካለፈው ሳምንት ጀምሮ እየተፈጸመበት ያለው ዓለማቀፍ የሳተላይት ሞገድ አፈና (Jamming) ምንጩ ከኢትዮጵያ መሆኑን እንዳረጋገጠ ገለጸ፡፡
ሳትኒውስ የተባለው የአገሪቱ የዜና ምንጭ ከትናንት በስቲያ እንደዘገበው፣ አረብሳት በሚያስተላልፋቸው በርካታ የቴሌቪዝን ጣቢያዎቹ ላይ መታየት የጀመረውን የስርጭት መስተጓጎል መነሻ ለማወቅ ባደረገው በረቂቅ ቴክኖሎጂ የታገዘ ጥናት፣ ከኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የሚነሳና ሆን ተብሎ የሚፈጸም የሳተላይት ሞገድ አፈና (Jamming) እየተደረገበት መሆኑን ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡ ይህን መሰሉ ህገወጥ ድርጊት መፈፀሙ መሆኑ እጅግ እንዳሳዘነው ያስታወቀው አረብሳት፤ ከኢትዮጵያም ሆነ ከኤርትራ የሚተላለፍ ምንም አይነት ስርጭት ሳይኖረው፣ የሳተላይት ሞገድ አፈና መደረጉ እንቆቅልሽ እንደሆነበት ገልጿል፡፡
የሳተላይት ሞገድ አፈናው፣ ምናልባትም ከሁለቱ አገራት የአንዱ ተቀናቃኝ የሆኑና ከአረብሳት ሳተላይቶች አቅራቢያ በሚገኙ ሳተላይቶች አማካይነት የሚሰራጩ የቴሌቪዝን ጣቢያዎችን ለማፈን የታለመ ሊሆን እንደሚችል ያለውን ግምትም ሰጥቷል፡፡
እየተፈጸመበት ያለውን ህገወጥ ተግባር ለመመከት በብሄራዊና በአለማቀፍ ደረጃ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የገለጸው አረብሳት፣ ጉዳዩን ለዓለማቀፉ የቴሌኮምኒኬሽን ህብረት እና ለአረብ ሊግ ማሳወቁንም ጠቅሷል፡፡አረብሳት ጉዳዩን በቀጣይ ከመረመረ በኋላ፣ ከአለማቀፍ የህግ ተቋማትና የአገሪቱ የህግ አካላት ጋር በመቀናጀት ወደ ህግ እንደሚያመራና እየተቃጣበት ባለው የሳተላይት ሞገድ አፈና ለደረሰበትም ሆነ ለሚደርስበት ጉዳት ካሳ እንደሚጠይቅ ማቀዱን ተናግሯል፡፡ከሁለት አመታት በፊት ከኢትዮጵያ ተመሳሳይ የሳተላይት ሞገድ አፈና እንደተፈጸመበትም አስታውሷል።

Breaking News

he Swiss government granted asylum to Co-pilot Hailemedhin Abera
(EMF) — The Switzerland government has granted asylum to the Ethiopian co-pilot who seized control of the Boeing 767-300 on 17 February 2014 and flew it to Geneva, according Ethiopian attorney who closely following the case.
The Ethiopian government has pushed the Swiss government to extradite the Co-pilot Hailemedhin Aberaby labeling him as a “traitor”. The regime has also opened file to try him in absentia, sources said.
The Swiss Federal Office of Justice has confirmed that it has refused the extradition request by the Ethiopian government.
Hailemedhin Abera can freely move now and defend his case out of confinement.
The pro-democracy Ethiopian Diaspora and, attorneys, like Shakespeare Feyissa, are trying to defend the rights of the co-pilot.
The airliner’s second-in-command, Hailemedhin Abera Tegegn, 31, took control of the plane when the pilot left the cockpit to use the toilet. He then sent a coded signal announcing he had hijacked his own aircraft. The plane landed safely, and none of the 202 passengers and crew members on Flight ET-702, which originated in Addis Ababa, the Ethiopian capital, were injured.
The Co-pilot has exposed the gross human rights violations in Ethiopia at a global scale.
Diaspora Ethiopians took the streets of American and European cities in Support of the Co-pilot Hailemedhin Abera.

Thursday, May 29, 2014

Breaking News -ባልታወቁ ኃይሎች ታፈነ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 1ኛ ዓመት ተማሪ ከዩኒቨርስቲ ግቢ ባልታወቁ ኃይሎች ታፈነ
------------------------------------------------------------------------
በጎንደር ምዕራብ አርማጨሆ ነዋሪ የሆነውና በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 6ኪሎ የአካውንቲግ 1ኛ ዓመት ተማሪ የሆነው እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአንድነት መዋቅር ስራ አስፈጻሚ አባል ወጣት መልካሙ አምባቸው ሰኞ ግንቦት 18 ቀን 2006 ዓ.ም ማታ ራት ከበላ በኋላ ከዩኒቨርስቲ ግቢ ባልታወቁ ኃይሎች ታፍኖ ተወስዷል፡፡ ወጣት መልካሙ በጎንደር የሚደረገውን የድንበር ማካለል የአካባቢው ነዋሪ እንደመሆኑ መጠን የሚያውቀውን መረጃ በመስጠቱ ክትትል አንዳንዴም ማስፈራሪያ ይደረግበት እንደነበር ለፍኖተ ነፃነት ዘጋቢ ይገልጽ ነበር፣ አሁንም የተያዘው ከድንበር ማካለሉ ጋር በሰጠው መረጃ እንደሆነ በቦታው የነበሩ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ፓርቲው ወጣት መልካሙ ያለበትን ሁኔታ ለማጣራት በዩኒቨርስቲው አካባቢ ያሉ ፖሊስ ጣቢያዎች ቢሞከርም እስካሁን ድረስ ያለበት አልታወቀም፡፡

Monday, May 26, 2014

ችሎቱ- ልብ አንጠልጣዩ ቴአትር

ችሎቱ- ልብ አንጠልጣዩ ቴአትር
ደረጀ ሀብተወልድ( ኢሳት)
እንደወትሮው ሁሉ ዛሬም ከቃሊቲ ወህኒ ቤት እስከ ጊዜያዊው ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ድረስ ባለው አስፋልት ዳርና ዳር
እስካፍንጫቸው የታጠቁ ወታደሮች በተጠንቀቅ ቆመዋል።መንገድች ለእግረኞችም ሆነ ለሌሎች ተሽከርካሪዎች ዝግ ናቸው። ወደ
130 የምንጠጋ እስረኞች በአራት ኮስተር መኪናዎች ተጭነን ወይም እንደወቅቱ ቀልዳችን እንደ አቶ መለስ ታጅበን ወድ ችሎቱ
እያመራን ነው። በየመኪናዎቹ ውስጥ ያሉትን ታጣቂዎች ሳይጨምር መትረየስ የደገኑ ሶስት ፒክ አፖች ከፊት፤ ሶስት ፒክ አፖች
ከሁዋላ አጅበውናል።አቶ መለስ በአንድ ወቅት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፦‛ስልጣን እስር ቤት ነው‛ሲለ ምን ማለታቸው እንደሆነ
በደንብ ገብቶኛል። በእርግጥም በህዝብ መካከል በነፃነት መራመድ ልማይችልና ዘመኑን ሁለ በጥቁር መስተዋትና በታጣቂ ተከብቦ
ለሚኖር እንደ እርሳቸው ላለ ሰው- ስልጣን የከፋ እስር ቤት ለመሆኑ ምርምር የሚጠይቅ አይደለም። ለዚህም ይመስለኛል
በግንቦት 97 ምርጫ ውድድር ወቅት አርቲስት ደበበ እሸቱ፦‛ቅንጅት ስልጣን ሲይዝ የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን አቶ መለስም
ጭምር ነፃ ይወጣሉ፤ የፈለጉበት ሱቅ ገብተው ሲጃራቸውን ይገዛሉ፤ በህዝብ መካከል ያለ ስጋት ይራመዳሉ‛ በማለት በተደጋጋሚ
ሲናገር የነበረው።
እናም... ታጅበን ወደ ችሎቱ ስናመራ ... ወደ ቤታቸው እንዲከተቱ የተደረጉት የአካባቢው ነዋሪዎች አንገቶቻቸውን በመስኮት
በማውጣት፣ በየቤታቸው በር ሊይ በቆሙት ቅልብ ታጣቂዎች ጀርባ በማንጋጠጥና በሁለት ጣቶቻቸው የቅንጅትን አርማ
በማውለብለብ ያስለመዱንን ‚የአለንላችሁ በርቱ!‛ አሸኛኘት ዛሬም አሊጓደሉብንም። ልክ ከጧቱ 3፡00 ሲሆን የቅንጅት መሪዎችን
በጊዜያዊነት እንዲያስችል ወደተዘጋጀው ሰፊ አዳራሽ ደረስን።የስድስት ኪሎው ቋሚ ችሎት ወደዚህ እንዲቀየር የተደረገው፤ፍርድ ቤት
በቀረብን ቁጥር “መሪዎቻችን ይፈቱ!” የሚለው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የተፈሪ መኮንን ተማሪዎች አመፅ፤በስፍራው እንደ አሸን
በሚፈሱት ደረት አልሞ ተኳሾች ጥይት ሊቆም ባለመቻሉ ነው።
*** ***** ****
ችሎቱን ለመከታተል አስቀድመው በመመዝገብ መግቢያ ካርድ ያገኙ የታሳሪ ቤተሰቦችና የወቅቱ ጭፍን እርምጃ የሳታቸው
አንዳንዴ የአገር ውስጥ ጋዜጠኞች ፤እየተፈተሹ፣መታወቂያቸውን እያሳዩና በፌዴራል ፖሊሶች እየተመዘገቡ ወደ አዳራሹ ከተቱ።
ዘወትር እንደሚደረገው ሁሉ የእነሱ መግባት እንደተጠናቀቀ በከፍተኛ አጀባና ጥበቃ ከመኪናዎቹ ወርደን በሁለት መስመር በመሰለፍ
ወደ አዳራሹ ገባን። ታዲሚዎች ከመቀመጫቸው በመነሳት እጃቸውን አወዛወዙ፤እኛም እጃችንን በማወዛወዝ የአፀፋ ሰላምታ ሰጥተን ተቀመጥን።ያ ሰፊ አዳራሽ ከአፍ እስከ ገደፉ ሞላ።
ሁሉም የቴአትሩን መጀመር በጉጉት እየተጠባበቀ ነው።ጥቁር ካባ የደረቡት ሶስት ዳኞች በአዳራሹ ጓሮ በር በመግባት መድረኩ ላይ
የተዘጋጀላቸውን ስፍራ ያዙ፦ የቀኝ ዳኛ ልኡል ገብረማርያም፣ የግራ ዳኛ አህመድ ኢብራሂም ሳኒ እና የመሀል ዳኛው አዲል።
አቃብያነ -ህጎቹ በትንሹ ለ30 ደቂቃ መዘግየት ልምዳቸው ነበርና ዛሬም ወንበራቸው ክፍት ሆኖ ይታያል። እንደምንም
ተንጠባጥበው መሟላታቸውን ተከትሎ፦
“እባካችሁ አቃቤ ህጎች በሰዓቱ ተገኙልን፤ እናንተ ቀድማችሁ መገኘት ሲገባችሁ እንዴት ታረፍዳላችሁ? ሁለተኛ እንዲይደገም!”
የተለመደው የመሀል ዳኛው ማሣሰቢያ ዛሬም ተሰማ።እነሱ ግን አልበረዳቸውም፤ አልሞቃቸውም። እነዚህ አቃብያነ-
ህጎች ከዳኞች በላይ አርፋጆችና ፈራጆች ሲሆኑ፤ ተከሳሾች ሊይ አፋቸውን ያሊቅቁ ዘንድ ረዥም የስድብ አፍ የተሰጣቸው
ይመስላሉ። ተከሳሾች “የንጉስ ሌጆች” የሚሌ ቅፅል ስም የሰጡዋቸው እነዚህ አቃበያነ ህጎች፦ አብርሀም ተጠምቀ፣ ሽመልስ ከማልና
ሚካኤሌ አብርሀ ይባሊሉ።
ጊዜያዊው ችሎት ለመጀመሪያ ቀን በቀረብን ዕለት አንደኛው አቃቤ ህግ 1ኛ ተከሳሽ የሆኑትን
ኢንጅነር ሀይሉ ሻውልን “አንተ!” እያለ ሲዘልፋቸው፤ ድንገት ብድግ በማለት ቁጣ ባዘለ ቃል፦‛ በእድሜ አባትህ ይሆናሉ፤ደግሞም
ሊቀ-መንበራችን ናቸው፤ አንተ ብለህ ልትጠራቸው መብት የለህም!” በማለቱ፤ ችሎት በመድፈር እዚያው ተከሶ በፖሊሶች እየተዳፋ
እንዲወጣ የተደረገው ማን ነበር? አዎ !ያችው መከረኛ ብርቱካን ሚዴቅሳ ነበረች።
ኩት! የማይባሉትን የሹም ዶሮዎች ዯደፍራለቻ! የንጉስ ልጆችን ገላምጣለቻ!
እሷ ለመብቷ በራሷ ቆመች፤ እነሱም በአለቃቸው ተመክተው አቅራሩ።
እነሱ፣
በጌታቸው እያመኑ- ባ’ለቃቸው እየፎከሩ፣
ላታቸውን ውጪ አሳደሩ።
እኛም፣
ቀንዳቸንን አውጥተን-ቀያችን እንዳይጠቃ፣
ፀንተን ቆመናል በጥበቃ።
……. እናም ከሳሾች (አቃብያነ-ህጎች) ምስክራቸውን ያሰሙ ዘንድ መሀል ዳኛው ጠየቁ ። መጋረጃው ተገለጠ፤ የእለቱ ድራማ ተጀመረ።
የዛሬውን ድራማ ከወትሮው በተለየ መልኩ አጓጊ ያደረገው፤ የአቃቤ ህግ ምስክር ሆነው የቀረቡት ግለሰብ ከሶስት ቀናት
በፊት አቃቤ ህግ ባቀረባቸው ሌላ ምስክር አንዴ “ሞተዋል”‚ አንድ ጊዜ “ተድብድበው ሞት አፋፍ ላይ ሆነው እያጣጣሩ ነው፤
እንደውም እስካሁን ህይወታቸው ሊቆይ አይችልም፤ አብቅተዋል” የተባሉ ሰው መሆናቸው ነው።ነገሩን በተከሳሽነትነት ለሚከታተል ብቻ ሳይሆን ለታዳሚዎች ሁሉ ሁኔታው እንቆቅልሽ ነው።በተለይ፦
“አማን በ አማን፣
ተንስአ እምነ ሙታን‛ እያለ እንደኔ ሲዘምር ላደገ ሰው፤‛ ኑር ሁሴን ከሞት ተነስቶ በቅንጅት ተከሳሾች ላይ ሊመሰክር ሲመጣ ማየት -እንዴት ግራ ያጋባል መሰላችሁ?
*** ***** ****
ድራማ ክፍል 1
ከጓደኞቹ እንደተረዳሁት፤ ኑር ሁሴን በምርጫ 97 ወቅት የንቧን ቲሸርት ለብሶ፦‛ኢህአዴግን ምረጡ!‛ እያለ በሳር ቤት አካባቢ
ሲቀሰቅስ የነበረ አነስተኛ ገቢ ያለው ግለሰብ ነው።ሆኖም የአዲስ አበባ ነዋሪ፦ “ምርጫችን ቅንጅት ነው” በማለቱ ሳይከፋው
አልቀረም። ቢያንስ በሰፈሩ ኢህአዴግ እንዲያሸንፍ ለማድረግ የነደፈው እቅድ እንደማይሳካ ሲረድ፤የምርጫውን መድረስ ተከትሎ
ከኢህአዴግ እየተሰፈረችለት ያለችው ስንቅ የምትቀርበት መሰለው። የሚይዘውን የሚጨብጠውን አጣ። በዚህ ሳይበቃው
“የቅንጅት ቀንደኛ ደጋፊዎች ሆነው ኢህአዴግ እንዲይመረጥ እንቅፋት እየፈጠሩ ያሉት እነ እገሌ ናቸው” ብሎ ከሚገምታቸው
ሰዎች ጋር በተድጋጋሚ ፀብ ይፈጥር ጀመር። የኑር ሁሴን አዲስ አመል የሰፈሩ መነጋገሪያ እስከመሆን ደረሰ።በዚህ መሀከል
ባልታወቁ ሰዎች በምሽት ተደብድቦ መንገድ ሊይ መውደቁ ተሰማ። የድራማው መቼት እዚህ ላይ በደንብ ተሰራ። እናም ኑር
ሁሴንን ማን መታው?? ማን ደበደበው?እነ መላኩ? ወይስ እነ መላኩን በህግ ቁጥጥር ስር ለማስገባት ሴራ የጠነሰሱ የደህንነት
ሀይሎች??የሚል ጥያቄ አንጠጥሎ ክፍል አንድ ቀጠለ....
አቃቤ ህግ ከቅንጅት መሪዎች ጋር በዘር ማጥፋት ወንጀል የከሰሳቸውን አምስት የአካባቢው ወጣቶች በኑር ሁሴን ድብደባ
ተጠያቂ አድርጓቸዋል።መላኩና ጓደኞቹ በቅንጅት ደጋፊነት መታሰራቸው እየታወቀ ለዚህ ነገር ተጠያቂ እንዱሆኑ የተፈለገው ፤
በክሱ ሂደት ሉቀርብባቸው የሚችል ማስረጃ ስላልተገኘ ነው።ምክንያቱም ወጣቶቹ ከደጋፊነት በዘለለ በቅንጅት ውስጥ
እዚህ ግባ የሚባል ሀላፊነት አልነበራቸውም። እናም ከሶስት ቀን በፊት የቀረበው የአቃቤ ህግ ምስክር፤ ኑር ሁሴን በነመላኩ
ድብደባ መሞቱን ለፍርድ ቤቱ ተናገረ፤ ወይም መሰከረ። የአምስቱንም ወጣቶች ማንነት በጣቱ በመጠቆም ጭምር አመሊከተ።
“ደብዳቢ እና ገዳይ” የተባለተ ወጣቶችም እየተባለ ያለው ነገር ፈፅሞ ስህተት እንደሆነ ለማስረዳት ቢሞክሩም ፤ለጊዜው ሰሚ አልተገኘም።
ዳኛው የምስክሩን ቃል መዝግበው አሰናበቱት።
ድራማ ክፍል 2
ይህ በሆነ በሶስተኛው ቀን ነው ዛሬ ኑር ሁሴን እንደ ኢየሱስ ተነስቶ የተገለጠልን። የንጉስ ልጆችም(አቃብያነ ህጎች)፦ የደረሰበትን ከፍተኛ ድብደባና ሰቆቃ በራሱ አንደበት ይገልፅ ዘንድ ኑር ሁሴንን ታሞ ከሚያጣጥርበት አልጋ ላይ እንዳመጡት ተናግረው ተቀመጡ። ተከሳሾችና ታዲሚዎች ብቻ ሳንሆን ችሎቱን የሚመሩት የመሀል ዳኛ ጭምር ግር ተሰኙ። ከቀናት በፊት በአሁኑ መስካሪ(ተጠቂ) ላይ - ሌላ ሰው የሰጠውን የ”ሞቷል” ምስክር አስታወሱ መሰል‛ ምንድነው ነገሩ?‛ በሚመስል ሁኔታ አንዴ ወደ መዝገባቸው፤ አንዴ ወደ አቃቤ ህጎቹ በማየት ነገሩን እንደገና ግልፅ ያድርጉላቸው ዘንድ ጠየቁ።
ልኡላኑም “ሞቷል..” ማስባላቸው ትዝ አላቸውና ፦
“ተከሳሾቹ ሞቷል እስኪባል ድረስ ክፉኛ እንደደበደቡት እና በህይወትና በሞት መካከል ጥለውት እንደሄዱ፣ ሆኖም ‘ኮማ’ ውስጥ ገብቶ ሞቷል ከተባለ በሁዋላ መትረፉን አሻሽለው በማብራራት፤ በህይወት ከተረፈ አይቀር የደረሰበትን አደጋ በራሱ አንደበት ይናገር ዘንድ እንዳመጡት እየተወለካከፉ ምላሽ ሰጡ። አዳራሹ ውስጥ ሳቅ ተሰማ። ዳኛው ታዳሚውንና ተከሳሾችን ስለመሳቃቸው ከተቆጡና ዳግም እንዲይለምዳቸው ካስጠነቀቁ በሁዋላ ከሞት የተነሳው ኑር ሁሴን ምስክርነቱን ይቀጥል ዘንድ ፈቀደ። ድራማው እየጦዘና አጓጊነቱ ይበልጥ እየጨመረ መጣ ።”ስክሪፕቱ” አሰልችና በቀሽም ደራሲ የተፃፈ ቢሆንም፤ ዋናው ገፀ-ባህሪ አሪፍ ስለነበር ተውኔቱን ህይወት ሊሰጠው ችሎአል። “የቲአትር ድርሰት ደረቅ አፅም ነው ፤ስጋና ደም አልብሰው ህይወት የሚሰጡት ጎበዝ ተዋንያን ናቸው” ‚ይባል የለ?አዎ! ኑር ሁሴን አሪፍ(genuine) ገፀ-ባህሪ ነበር።
እነሆ የገጸ- ባህርይው በቃት የታየበት ተከታይ ክፍል፦
የመሀል ዳኛው የደረሰበትን በአጭሩ ለፍርድ ቤቱ ይናገር ዘንድ ባቀረቡለት ጥያቄ መሰረት ኑርሁሴን የተፈፀመበትን ድብደባ ሆድ
እየባሰውና እያለቀሰ ብዙዎቻችንን ባሳዘነን ሁኔታ ተናገረ።
አዎ! ኑር ሁሴን ክፉኛ ተደብድቧል። ይህን ማስተባበል ከእውነት ጋር መጣላት ይሆናል።እንደውም ከሁኔታው ለመገመት
እንደሚቻለው ጠንከር ያለ በትር ሳያርፍበት አልቀረም።ይህ በማንም ዘንድ ተቀባይነት የሌለው ፀያፍ ድርጊት እስከሆነ ድረስ፤የኑር ሁሴን ደብዳቢዎች በህግ መጠየቅ የለባቸውም የሚል የለም። አብዩ ነጥብ፦ ”ደብዲቢዎቹ እነማን ናቸው? የሚለው ወሳኝ ጥያቄ መመለሱ ላይ ነው። እናም ዳኛው ቀጠሉ፦‛የመቱዎት እነማን እንደሆኑ ያውቃሉ?‛
“እ…እ…መላኩ፣ ..እእእ...ፈቃደ፣እእእ....ቻይና....‛ እያለ የጓደኞቹን(የአምስቱን ወጣቶች) ስም እየተንቀጠቀጠ ተናገረ። “ሞቷል” የተባለው
ኑር ሁሴን በአካል ሊመሰክር ሲመጣ ፊታቸው በደስታ የበራውና ነፃ እንደሚወጡ በሙሉ መተማመን እያንሾከሾኩ ሲነጋገሩ
የነበሩት አምስቱ ወጣቶች ፤ በራሱ ከኑር ሁሴን አንደበት “ደብዲቢ” ተብለው ሲመሰከርባቸው በድንጋጤ እጃቸውን አፋቸው ላይ
አኖሩ።‛ እንዴ ምነካው?‛ የሚል ድምፅም ንዴቱን መቆጣጠር ከተሳነው ከአንድኛው ወጣት ተሰማ። አቃቤ ህጎቹ የስነ
ስርአት ጥያቄ አስከተሉ፤ ዳኛው ተናጋሪውን ወጣት ገሰፁ፤ ድራማው ቀጠለ...
አሁን ኑር ሁሴን በአካል ተነስቶ “ደበደቡኝ” ያላቸውን ጓደኞቹን በጣቱ እየጠቆመ የሚያሳይበት ክፍል ነው።”ደብዳቢ” በተባሉት
ወጣቶች መደድ የተቀመጥን ተከሳሾች በሙሉ ከመቀመጫችን እንድንነሳ ዳኛው ጠየቁ፤ሁላችንም ተነሳን።ከተነሳነው ውስጥ እነ መሊኩን፣እነ ፈቃደን፣አነ ቻይናን እየጠቆመ እንዲያሳይ ኑሩ ሁሴን ተጠየቀ። ኑር ሁሴን በስግታ እየተራመደ ወደ እኛ መጣ፤ ነገሩ ሳያስጨንቀው አልቀረም። “ደበደቡኝ” ብሎ ወደመሰከረባቸው ጓደኞቹ ሲደርስ ከውስጡ ጋር የሚሟገት ይመስል ነበር። ለመጠቆም በጣም ዘገየ። መሀል ዳኛው “ልትለያቸው አልቻልክም ማለት ነው?” እስኪጠይቁት ድረስ አጠገባቸው ደርሶ በዝምታ ቆመ። መጨነቁን የተመለከቱት ተከሳሽ ጓደኞቹም ያለ ምንም ፍርሀት፦‛ኑር ሁሴን፤ እዚህ ነን‛ ብለው እንደ ወትሮው በፍቅር ጠሩት።እሱም ተከትሎ እየሳቀ ፦‛እኚሁት‛አለ።እየጠቆማቸው እርስ በርስ ተሳሳቁ። ሁላችንም እስክንስቅ ድረስ ነገረ-ስራቸው ግራ አጋባን። ዳኛው የተለመደ ቁጣቸውን ካሰሙ በሁዋላ ኑር ሁሴን ቦታውን እንዱይዝ አዘዙ ።አስከትለውም ተከሳሾቹ መስቀለኛ
ጥያቄ ካላቸው ኑርሁሴንን መጠየቅ እንደሚችሉ አሳወቁ፤ድራማው ውበቱን እየጨመረ ወደ መጠናቀቂያው ደረሰ...
የመጨረሻው ክፍል(መስቀለኛ ጥያቄ)
ተከሳሽ ፈቃዱ፦”ኑር ሁሴን እኔ አንተን መትቼሀለሁ?”
ኑር ሁሴን፦”ፈቃደ ጓደኛዬ ፤ ገንዘብ አበዳሪዬ፤ የልብ ምስጢረኛዬ ...በፍፁም አልመታኸኝም” አዲራሹ በከፍተኛ ሳቅ ተናጋ።
የአቃቤ ህጎቹ አይን ከመቅፅበት ደም መሰለ።ዳኞቹ ግራ ተጋቡ።ፈቃዱ ፦‛ይኸው ይመዝገብልኝ፤ጥያቄየን ጨርሻለሁ”ብሎ
ተቀመጠ። ተከሳሽ መላኩ በተራው ተነሳ፦
“ኑር ሁሴን እኔ አንተን መትቼሀሇሁ?”
ኑር ሁሴን፦”መሊኩ ጓደኛዬ፤ ፀጉሬን አስተካካዬ፤ወንዴሜ ፣መካሪዬ....‛ የብዙዎቻችን ሳቅ የአዲራሹን ጣራ ሰንጥቆ ወጣ።አቃቤ
ህጎቹ በመሀከል ገብተው ለመናገር ቢፈልጉም ጊዜው የመስቀለኛ ጥያቄ ነበርና አልተፈቀደላቸውም። መላኩም፦“ይኸው ይመዝገብልኝ፤
ጥያቄየን ጨርሻለሁ” ብሎ ተቀመጠ።ቻይና እና ሌሎቹም ለጊዜው ስማቸውን የዘነጋሁዋቸው ሁለት ወጣቶች እንደዚሁ
ተመሳሳይ ጥያቄ በማቅርብ ንፅህናቸውን አረጋገጡ።በሁኔታው በጣም ግራ የተጋቡት ዳኛም፦” አቶ ኑር ሁሴን ቅዴም ማነው የደበደበዎት ተብለው ሲጠየቁ፤ እነ መላኩ፣ እነ ፈቃዱ፣እነ ቻይና....ናቸው እያሉ መስክረው ሲያበቁ፤ አሁን በመስቀለኛ ጥያቄ ላይ እንዴት አልደበደቡኝም ይላሉ? ነገሩን ግልፅ ሉያደርጉልን ይገባል! እነ መላኩ ደብድበዎታል?ወይስ አልደበድቡዎትም?”
ኑር ሁሴን፦‛አልደበደቡኝም!‛
ዳኛ፦‛ቅድም ለምን ደብድበውኛል አሉ?’
ኑር ሁሴን፦‛ጧት እቤቴ መጥተው እንደሱ በል ብለውኝ ነው‛
ዳኛ፦‛ማናቸው እንደሱ በሉ ያለዎት?‛
ኑርሁሴን፦‛መንግስት፣የመንግስት ፖሉሶች‛ ........የአቃቤ ህጉቹ የማያባራ ‚ስነ ስርአት !ስነ-ስርአት!‚ያልገደበው የማያባራ
ሳቅ................ሳቅ.......................
.የእለቱ ድራማ በዚሁ ተጠናቀቀ።
***********************************
ኑር ሁሴን ከህሊናው ጋር ታረቀ።ከአቃቤ ህጎቹ ቁጣና ማባበል የጓደኞቼ እውነት ይበልጥብኛል አለ።የአምላክ ነፍስ በብርቱ
ከምትፀየፋቸው ነገሮች ዋነኛው፦‛በወንድማማቾች መካከል ፀብ የሚዘራን‛ እንደሆነ ታላቁ መፅሀፍ ይነግረናል።በኑር ሁሴንና በነ
መላኩ መካከል ፀብ የዘሩት ወገኖች እንደ ሀገርም ያቆየነውን የመዋደድ፣ የመከባበርና አብሮ የመኖር እሴት ፤በሀይማኖትና በዘር እሳት
ለመሸርሸር እንቅልፍ አጥተው መራወጥ ከያዙ ጥቂት የማይባሉ ዓመታት አለፉ። በጓደኛሞቹ በኑር ሁሴንና -በነመላኩ ላይ
የተሞከረው ነገር ፤የትልቁ “በታትነው ‚ፖሲሲ” ነፀብራቅ ነው።ግን አልተሳካም።በወቅቱ ፈቃዱ እንደነገረኝ ከሆነ ከእስር ሲፈታ የልብ ጓደኛ ከሚያደርጋቸው ሰዎች መካከል አንዱ- ኑር ሁሴን ነው።
ድራማው በዚህ መልክ ቢጠናቀቅም ችሎቱ በሌሎች ቀናት ቀጠለ...ቀጠለ...በእነዚህና በሌሎች መሰል አስቂኝ ማስረጃዎች ፍርድ ቤቱ በእነኢንጅነር ሀይለ ፋይሌ በተከሰሱ የቅንጅት መሪዎች፣የሲቪሌና የሙያ ማብበራት መሪዎችና ጋዜጠኞች ላይ የዕድሜ ልክ እስራት ፈረደ።
ምክንያት?
ይኽ የግንቦት 20 ፍርድ ቤት ነው።

Saturday, May 24, 2014

-----------ሰበር ዜና-----------

----------------------------ሰበር ዜና-----------------------------------
ያለ በቂ ማስረጃ በሕገ ወጥ መንገድ ከአራት ሳምንት በፌት ከተያዙት ስድስቱ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን በተጨማሪ በአንድ ጦማሪ አባል መኖሪያ ቤት ላይ ፖሊስ ለ7 ሰአት የቆየ ብርበራ አካሄደ፡፡
በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 12 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ በዞን ዘጠኝ ጦማሪና መስራች ሶልያና ሽመልስ ቤተሰብ መኖሪያ ቤት ፖሊስ ብርበራ ያካሄደ ሲሆን የጸረ-ሽብር ሕጉ ይፈቅድልናል የሚል ምክንያት ሰጥተው ያለ ፍርድ ቤት የብረበራ ማዘዣ ከካሜራ ቀራጭ ጋር የተገኙት ሰባት ፖሊሶች በጦማሪዋ ክፍል እና ሌሎች አስፈላጊ ነው ባሉዋቸው ክፍሎች ሲያካሂዱ ነበረውን ብርበራ ጨርሰው ይጠቅመናል ያሉትን የዶ/ር መረራ ጉዲና የመጨረሻ መጽሀፍ እና ሌሎች ወረቀቶች ወስደው ቤት ውስጥ የነበሩትን የጦማሪዋን ወላጅ እናት አስፈርመው ከጠዋቱ 4 ሰአት አካባቢ ቤቱን ለቀው ወጥተው ነበር፡፡ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ተመልሰው በመምጣት ተጨማሪ ፍተሻ በዋናው መኖሪያ ቤት መካሄድ እንፈልጋለን ብለው ሁለተኛ ዙር ብርበራ በምግብ ማብሰያ ክፍል ውስጥ እናካሂዳከን በሚል ሰበብ ትንሹ ክፍል ውስጥ የጦማሪዋን እናት እነዲወጡ በማግለል ከማቀዝቀዛውን አንቀሳቅሰው አፍታም ሳይቆዩ 19 ገጽ የግንቦት ሰባት ፕሮግራም አግኝቻለሁ ሲል አንዱ ፈታሽ ተናግሯል፡።
የጦማሪዋን ወላጅ እናት እነዲፈርሙ ያግባቡ ቢሆንም ወላጅ እናትዋ ከክፍሏ እና ሌላም ቦታ በመፈተሽ ስታገኙ ያየሁት ወረቀት ላይ ፈርሜያለሁ ይህ ግን ምግብ ማብሰያ ክፍል ውስጥ ያልነበረ እና እዚህ ያልተገኘ ሌላ ወረቀት ነው ሲገኝም አላየሁም በማለት አልፈርምም ብለዋቸዋል፡፡ በመሆኑም ፈታሾች ተጨማሪ የሰው ሃይል ደውለው በማስጠራት ለማግባባት ቢሞክሩም ስላልተሳካላቸው ይዘዋቸው የመጡትን የራሳቸውን ሁለት ምስክሮች ብቻ አስፈርመው ባለቤትዋ ለመፈረም ፍቃደኛ አይደሉም ብለው ቤቱን ለቀው ሄደዋል፡፡ ከፓሊስ ጋር የመጡት ምስክሮች አንደኛው አድራሻቸው በብርበራ ምስክርነት ዶክመንቱ ላይ ያልተጻፈ መሆኑንም ለመረዳት ችለናል ፡፡
በብርበራው ወቅት በነበራቸው የ7 ሰአት ቆይታ የጦማሪዋን መጸሃፍት የጉዞ ትኬቶች የስልጠና ማንዋል እና የመሳሰሉትን ጥቃቅን ወረቀቶች የወሰዱ ሲሆን ማብሰያ ክፍል ከፍሪጅ ጀርባ አገኘነው ካሉት ወረቀት ግን ቤት ውስጥ ያልነበረና ፓሊሶች ራሳቸው ያመጡት በመሆኑ እናትዋ ተናግረዋል፡፡
የዞን ዘጠኝ ጦማሪ አባላት ከየትኛውም በፓርላማ በአሸባሪነት ከተፈረጀ የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆኑና ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸው እነዲሁም አነዚህ ድርጅቶች ላይ በተለያየ አጋጣሚ ትችቶቻቸውን ሲያቀርቡና ሲቃወሙ የሚታወቁ ቢሆንም ሲሆን በተያዙት አባሎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው አስገድዶ ለሃሰተኛ መረጃ እንዲፈርሙ የማድረግ ተግባር ሳያንስ ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ለማያያዝ ማስረጃን እንደተገኘ አድርጎ የማቅረቡ ተግባር መንግሰት ይታማበት የነበረውን የፓለቲካ ውንጀላን በሽብር የመቀየር ክስ በተግባር እንድናይ ያስቻለን ነው ፡።
በመሆኑም አሁንም ቢሆነ ጦማሪ ጓደኞቻችን ሃሳባቸውን በነጻነት ከመግለጻቸው ውጪ ምንም አይነት የወንጀልም ሆነ ሽብር ከተፈረጁ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት እንደሌላቸው እያስታወስን መንግስት ያሰራቸውን ጦማርያን እና ጋዜጠኞች አንዲፈታ አሁንም አንጠይቃለን፡፡

Sunday, May 18, 2014

ፖሊስ ሊመሰረት ያሰበው የሽብርተኝነት ክስ በፍርድ ቤቱ ውድቅ ተደረገ

ፖሊስ ሊመሰረት ያሰበው የሽብርተኝነት ክስ በፍርድ ቤቱ ውድቅ ተደረገ
(By Bisrat Woldemichael)
ዛሬ እሁድ ግንቦት 10 ቀን 2006 ዓ.ም. አራዳ በሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት በፍቃዱ ኃይሉ፣ አቤል ዋበላ እና ማህሌት ፋንታሁን ከረፋዱ 4፡20 ቀርበው ነበር፡፡ ይዟቸው የመጣውና እስካሁንም መደበኛ ክስ ያልመሰረተው የማዕከላዊ ፖሊስ ምርመራዬን አልጨረስኩም፣ ጉዳዩ ከሽብር ጋር ስለሚያያዝ ተጨማሪ የ 28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ ሲል ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል፡፡
ፍርድ ቤቱም ከዚህ በፉት ለ24 ቀናት አስራችሁ ያቀረባችሁት ከሽብር ጋር የተያያዘ ባለመሆኑ እና ሌላ አዲስ ሂደት ስለሌለ ከዚህ በፊት ያላቀረባችሁትን ከሽብር ጋር የተያያዘ የሚለውን ጭብጥ አልቀበልም፣ ተጨማሪ የ28 ቀናት የምርራ ጊዜ የተጠየቀውም ተገቢ አይደለም ካለ በኋላ የ14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ በመስጠት ለእሁድ ግንቦት 24 ቀን 2006 ዓ.ም. ጠዋት ተለዋጭ ቀነ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ፍርድ ቤቱም ፖሊስ ያቀረበውን ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ የሚውን ውድቅ አድርጎታል፡፡
ትናንት ግንቦት 9 ቀን 2006 ዓ.ም. የነበረው የ 6ቱ ጋዜጠኞች እና ብሎገሮች ፖሊስ ጉዳዩን ከሽብር ጋር አያይዞ ተጨማሪ የ28 ቀናት የጠየቀው ተፈቅዶለት ለሰኔ 7 ቀን 2006 ዓ.ም. ጠዋት ተለዋጭ ቀነ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል፡፡ ትናንት የነበረው የ6 ቱን ጉዳይ የተመለከተው ዳኛ ወንድ ሲሆን የዛሬውን ጉዳይ የተመለከተችው ዳኛ ሴት መሆኗ ተጠቁሟል፡፡

ጋዜጠኞቹ እና ብሎገሮቹ የፍርድ ቤት ውሎ

የጋዜጠኞቹ እና ብሎገሮቹ የፍርድ ቤት ውሎ
“የሥነልቡና ጫና ደርሶብኛል”
ጋዜጠኛ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ
“ከሌሊቱ 8 ሰዓት እየተወሰድኩ ድብደባ፣ ማስፈራራት እና ወከባ ተፈጽሞብኛል”
አጥናፍ ብርሃኔ
“ለምርመራ የምጠቀምበት አንድ ኮምፒውተር ነው ያለኝ፤ ጊዜ ይሰጠኝ”
ፖሊስ
ቅዳሜ ግንቦት 9፣ 2006 በቀጠሯቸው መሠረት አራዳ ምድብ ችሎት የቀረቡት 3 ጋዜጠኞች እና 3 ብሎገሮች ነበሩ፡፡ ፖሊስ የተጠርጣሪዎቹን ጉዳዩ ከወንጀል ወደ ሽብር በማሻሻሉ እና ምርመራዬን አላጠናቀቀኩም በማለቱ የ28 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቆ ተፈቅዶለታል፡፡ ሦስት ሰዓት ይሰማል የተባለው ችሎት 4፡30 አካባቢ የተጀመረ ሲሆን በመዝገብ ቁጥር 118721 የተከሰሱት ሦስት ተጠርጣሪዎች ኤዶም ካሣዬ፣ አጥናፍ ብርሃኔ እና ናትናኤል ፈለቀ በመጀመሪያ ቀርበዋል፡፡ በዛሬው ችሎት ከእየአንዳንዱ ታሳሪ ሦስት የቤተሰብ አባላት ወደ ችሎት ገብተው እንዲታደሙ ተፈቅዶ ነበር፡፡ ፖሊስ ክሱን ከወንጀል ወደ ሽብር ከፍ አድርጎ ቀርቧል፡፡ ምርመራዬን ስላላጠናቀቅኩ የተጨማሪ የ28 ቀናት ጊዜ ይሰጠኝ ብሎም ለችሎቱ ጥያቄ አቅርቧል፡፡ የተከሳሽ ጠበቆች ግን ከዚህ ቀደም በተሰጠው ሁለት ቀጠሮዎች ውስጥ አጣራቸዋለሁ ያላቸው 6 ጉዳዮች አሁንም አልተሰሩም፤ ድርጊቱ ደንበኞቻችንን በቀጠሮ ማጉላላት ነው፣ ማስረጃ ባልተሰበሰበበት ሁኔታ ከወንጀል ወደ ሽብር የተቀየረበት መንገድም ተገቢ አይደለም ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ ፖሊስ መተርጎም ያለባቸው ሰነዶች ወደ ትርጉም ቤት ተልከዋል፣ ግብረአበሮቻቸው አድራሻ እየለዋወጡ ሊያዙልኝ አልቻሉም፣ አቀርባለሁ ያልኳቸውን ምስክሮችም እያስፈራሩብኝ ለማቅረብ አልተቻለኝም ሲል መልሷል፡፡ ፍርድ ቤቱም የተጠየቀውን የ28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ፈቅዷል፡፡ በዚህም መሠረት ጋዜጠኞቹ እና ብሎገሮቹ ቅዳሜ ሰኔ 7፣ 2006 ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት እንዲቀርቡ አዟል፡፡ አጥናፍ ብርሃኔ ከሌሊቱ በስምንት ሰዓት ወደ ምርመራ ክፍሎች እየተወሰደ በመርማሪዎች ወከባ፣ ድብደባ እና ማስፈራሪያ እንደደረሰበት ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ ባለፈው ቀጠሮ ሚያዚያ 30 ቀርበው የነበሩት በፍቃዱ ኃይሉ እና አቤል ዋበላ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ለፍርድ ቤቱ ማስረዳታቸው ይታወሳል፡፡ ቀጥሎ በታየው መዝገብ 118722 ተጠርጥረው የቀረቡት አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ፣ ተስፋዓለም ወልደየስ እና ዘላለም ክብረት ክሳቸው ወደ ሽብር ተለውጦ በመቅረቡ እነሱም ሰኔ 7 ቀን 2006 እንዲቀርቡ ታዟል፡፡ ለችሎቱ የመናገር እድል እንዲሰጠው ጠይቆ የተፈቀደለት ጋዜጠኛ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ “መርማሪው የዞን 9 አባል አለመሆኔን ቢያምንም በተደጋጋሚ ጊዜ እየተጠራሁ አንድ ዓይነት በሆነ ጥያቄ ስለዞን 9 የምታውቀው ነገር አለና ተናገር እየተባልኩ ከፍተኛ የሥነልቡና ጫና ደርሶብኛል፡፡ ጋዜጠኛ እንደሆንኩም ያውቃሉ፡፡” በማለት ቅሬታውን እንባ እየተናነቀው አሰምቷል፡፡ የአስማማው ሁኔታ የችሎቱን ታዳሚያን እንባ አራጭቷል፡፡ ጠበቆቻቸውም ፖሊስ ከዚህ ቀደም በጠየቃቸው ቀጠሮዎች የሰራው ነገር ስለሌለ የ28 ቀን ቀጠሮ ሊሰጠው አይገባም፤ ዋስትና ይፈቀድልን፤ ዋስትና አያሰጥም እንኳን ከተባለ ፖሊስ ከዚህ በኋላ በጠየቀው ጊዜ ምን ሊሰራ እንዳሰበ ይግለጽልን ሲሉ ለችሎቱ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ መልስ የሰጡት መርማሪም በመረጃ ዴስካችን ውስጥ ያለን ኮምፒዩተር አንድ ብቻ በመሆኑ የሁሉንም ተጠርጣሪዎች ፋይል ለማጣራት ጊዜ ወስዶብናል ብለዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በሕቡዕ ተደራጅተዋል፤ ከእያንዳንዳቸው ኢ-ሜይል ለአመጽ የሚቀሰቅሱ ማስረጃዎች አግኝተናል እያንዳንዱን ለማስተርጎም ጊዜ ይወስዳል፤ በስማቸው ከውጭ የተላከ ገንዘብ እንዳለና ለሽብር ድርጊት ሊጠቀሙበት እንደሆነ ደርሰንበታል ያለ ቢሆንም ጠበቆቻቸው ግን ፖሊስ የጸረ-ሽብር ሕጉን አለአግባብ እየተጠቀመበት ነው፤ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ እና ተስፋለም ወልደየስ የዞን ዘጠኝ አባላት አይደሉም፡፡ ጋዜጠኞች ናቸው፡፡ ደንበኞቻችንን ሊያስጠረጥራቸው የሚችል ወንጀል አልተገኘባቸውም ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ የዞን 9 አባላት ከውጭ የሽብር አካላት ስልጠና አግኝተዋል የሚለው ልክ አይደለም፡፡ አርቲክል 19 እና ፍሪደም ሃውስ ሀሳብን የመግለጽ መብት እንዲከበር የሚንቀሳቀሱ ዓለም አቀፍ ተቋማት ናቸው፡፡ የትም ሀገር እና ቦታ የሽብር ተቋማት ተብለው አያውቁም፡፡ በኛም ሀገር በፓርላማ ሽብርተኛ ተብለው አልተወገዙም ሲሉ ጠበቆቻቸው ተናግረዋል፡፡ በመዝገብ ቁጥር 118720 የተካተቱት በፍቃዱ ኃይሉ፣ ማህሌት ፋንታሁን እና አቤል ዋበላ እሁድ ግንቦት 10 ቀን 2006 ዓ.ም ጠዋት ይቀርባሉ፡፡ ጋዜጠኞቹ እና ብሎገሮቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሚያዚያ 18 እና 19 ቢሆንም ጠበቆቻቸው እንዲጎበኟቸው የተፈቀደው ግን ባሳለፍነው ረቡዕ ግንቦት 6 እና አርብ ግንቦት 8፣ 2006 ነው፡፡

Friday, May 16, 2014

ጁነዲን ሰዶ አትላንታ አሜሪካ ገቡ

ጁነዲን ሰዶ አትላንታ አሜሪካ ገቡ
May 15, 2014
Junedin Sado“ይሄ ፋሽስት መንግሥት!” ማለት ጀምረዋል!
አገር ለቀው የኮበለሉትና የኦሮምያ ፕሬዚዳንትነትን ጨምሮ በተለያዩ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች በሚኒስትርነት ማዕረግ ያገለገሉት እንዲሁም የኦህዴድና የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ጁነዲን ሰዶ አሜሪካ መግባታቸውን በዋሺንግተን ዲሲ የሚታተመው ዘ-ኢትዮጵያ የተባለው የአማርኛ ጋዜጣ ይፋ አድርጓል። ኬንያ ለአንድ ዓመት ያህል በስደተኝነት ተቀምጠው የአሳይለም ወረቀታቸውን አግኝተው አትላንታ ከገቡ ሁለት ወራት እንደሆናቸውም የዘኢትዮጵያ ጋዜጣ ምንጮች ገልጸዋል።
አቶ ጁነዲን በአባ ዱላ ገመዳ እስኪተኩ ድረስ ከኦክቶበር 28/2001 እስከ ኦክቶበር 6 /2005 የኦሮምያ ክልል ፕሬዚዳንት ነበሩ። ከዚያም የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስትር በመሆን እስከ ኦክቶበር 2008 አገልግለዋል። በመቀጠልም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትርነት ከሠሩ በኋላ በመጨረሻም በ2010 የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር በመሆን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊን መንግሥት አገልግለዋል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲም የቦርድ ሊቀመንበር ነበሩ። መንግሥታቸው ብዙ ዓመት ከኖሩበት የሚኒስትሮች ካቢኔ ያሰነባታቸው የአቶ ኃይለማርያም የጠቅላይ ሚኒስትርነት ዘመን ሲጀመር ነው።የስደት ኑሯቸውን ማቃናት የያዙት አቶ ጁነዲን ከወዳጆቻቸው ጋር ሲያወጉ “ይሄ ፋሽስት መንግሥት እኮ የሚያደርገውን አያውቅም” በሚል መገረም ሲናገሩ መደመጣቸውን ምንጮቻችን ገልጸዋል። ባለቤታቸው ወ/ሮ ሀቢባ መሀመድ “በሽብር ተግባር ተጠርጥረዋል፣ ከሳዑዲ ኤምባሲ ገንዘብና መጽሐፍት ይዘው ሲወጡ ሐምሌ 9 ቀን 2004 እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል” በሚል ተዘውታሪ ሰበብ በእስር መቆየታቸው ይታወሳል። ከሥልጣናቸው በመስመጥ ላይ ለነበሩት አቶ ጁኒዲም ይህ የባለቤታቸው እስር ተጨምሮ ከአገር ለመኮብለል መንስኤ መሆኑ ሲዘገብ መሰንበቱ ይታወቃል።
ባለቤታቸውና ልጃቸው አሁንም በኢትዮጵያ የሚገኙ በመሆኑ አቶ ጁኒዲን በይፋ ምንም አስተያየት ሳይሰጡ ተቆጠበው መቀመጡን መምረጣቸው ተነግሯል። ሰሞኑን በኦሮምያ ክልል ተማሪዎች ላይ እየደረሰው ያለው ግድያና ሁከት በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የሚመለከታቸው ቢሆንም፣ እንደ ተራ ሰው “ይሄ ፋሽስት መንግሥት ምን እያደረገ ነው” ብለው መገረማቸው መልሶ ማሰገረሙን ምጮቻችን ገልጸውልናል። የኦሮምያ ክልል ፕሬዘዳንት ከነበሩት ውስጥ ሀገር ጥለው የኮበለሉ ፕሬዘዳንቶች ከአቶ ሀሰን ዓሊ ጋር አቶ ጁነዲን ሲደመሩ ሁለተኛ መሆናቸው ነው። ሁለቱም አትላንታ መሆናቸው ሲገለጽ አቶ ጁነዲን በአንድ ዩኒቨርስቲ መምርህነት ሥራ ለማግኘት ማመልከቻ ማስገባታቸውም ተነግሯል።
ምንጭ:(ዘኢትዮጵያ)

የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ክለላ ዛሬ በድብቅ ሊፈረም ነው!

የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ክለላ ዛሬ በድብቅ ሊፈረም ነው!
==========================
የኢትዮ ሱዳን ዳር ድንበር በግልፅ የተከለለ እንዳልሆነ ይታወቃል። የኢትዮጵያ አርሶአደሮች የሚጠቀሙት መሬት የኢትዮጵያ እንደሆነ ሲወሰድ ሱዳናውያን የሚገለገሉበትም የሱዳን ነው ተብሎ ይታሰባል። ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን የኢህአዴግ መንግስት ኢትዮጵያውያን አርሶአደሮችን ከቀያቸው እያፈናቀለ ለሱዳን ማስረከቡ ይታወቃል። ብዙ የኢትዮጵያ አርሶአደሮች ተፈናቅለዋል፣ የተወሰኑ ተለዋጭ መሬት ሲሰጣቸው ምንም ያላገኙም አሉ።
ድንበሩ ብዙ ዉዝግብና ተቃውሞ ያለው ሲሆን የኢህአዴግ መንግስት ከሱዳኖች ጋር በመተባበር በድብቅ ለመከለል ተስማምቷል። እንዲህ ነው የተደረገው፥ በድንበሩ አከባቢ የሚገኙ ኗሪዎች (የኢትዮጵያና የሱዳን) ድንበራቸውን አይተው ክለላውን ይፈፅማሉ፣ ይፈራረማሉ። ለሱዳን የተሰጠው መሬት ታውቋል። ሁሉም ነገር በኢህአዴግና የሱዳን መንግስት አልቋል። አሁን "የሀገር ሽማግሌዎች" እንዲፈርሙ እየተደረገ ነው። የሀገር ሽማግሌዎች እንዲፈርሙ የተፈለገበት ምክንያት የድንበር ክለላ የተከናወነው በኗሪዎች ነው እንዲባል ነው። ለሌላ ግዜም ምስክር ሁነው እንዲቀርቡ ነው።
በዚህ መሰረት በድንበሩ አከባቢ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ከተሞች ማይካድራና በረከት የተወሰኑ ሰዎች በካድሬዎች ተመርጠው "ኮሚቴ" ተሰኝተው ዛሬ ግንቦት 8, 2006 ዓም እንዲፈርሙ ወደ ሱዳን ድንበር ተጉዘዋል። እነዚህ ኮሚቴ ተብለው የተመረጡ ሰዎች ስለ ድንበሩ ይሁን አከባቢው እውቀት የሌላቸው፣ የአከባቢው ኗሪዎች ሳይሆኑ በቅርብ ግዜ ባከባቢው መሬት የተሰጣቸው ሰፈርተኞች ናቸው። ዕድሜየቸውም ከአርባ በታች ነው፣ ትምህርት የላቸውም፣ የድንበሩ ታሪክ አያውቁም፣ መሬት ስለተሰጣቸውና በካድሬዎች ስለታዘዙ ብቻ ሊፈርሙ የሚችሉ ናቸው። ስለዚህ የሀገር ሽማግሌዎች ሊባሉ አይችሉም። ምክንያቱም ሰፈርተኞች እንጂ ኗሪዎች አይደሉም፣ ወጣቶች ናቸው (ድንበሩ ላያውቁት ይችላሉ)፣ ትምህርት የላቸውም (የድንበር ጉዳይ ምን ያህል ጥንቃቄ የሚያስፈልገው እንደሆነ ላይረዱ ይችላሉ) ወዘተ። ዛሬ እንዲፈርሙ የተወሰዱት በድብቅ መሆኑ ነው።
የድንበር ጉዳይና ሌሎች የሑመራ አከባቢ ኗሪዎች በማየሉ ተቃውሞ እየተቀሰቀሰ በመሆኑ ባከባቢው ተገኝቶ መረጃ ማሰባሰብ አስቸጋሪ እየሆነ ነው። የመንግስት አካላት ኗሪዎች ለሌሎች አካላት መረጃ እንዳይሰጡ እያስፈራሩ ነው። መረጃ መሰብሰብም አይፈቀድም። በዚሁ አጋጣሚ ግርማይ ወልደግዮርግስ የተባለ የድምፂ ወያነ ሬድዮ ጋዜጠኛ ባስተዳዳሪዎች ከቀረቡለት አራት ካድሬዎች ዉጭ ሌሎች ኗሪዎችን በማነጋገሩ ምክንያት ባለስልጣናት ፖሊስ ጠርተው አስረውታል። የድምፂ ወያነ ሬድዮ ጋዜጠኛ ህዝብን ሳንፈቅድልህ አገጋግረሃል ተብሎ ነው የታሰረው።
በሑመራ አከባቢ ብዙ ተደራራቢ ችግሮች አሉ። ሕገወጥ የመሬት ሽንሸና እየተደረገ ነው። ኗሪዎችን ከቀያቸው እየተፈናቀሉ ስርዓቱ ያገለግላሉ ለተባሉ ሰዎች መሬት እየተሰጠ ይገኛል። ለምሳሌ አቶ ካሕሳይ ገብረሚካኤል የተባሉ ያከባቢው ኗሪ መሬታቸው ተወስዶ ለሌላ የህወሓት ካድሬ ዉሽማ ተሰጥቷል። ፍትሐዊ ያልሆነ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል።
በድንበሩ ጉዳይ በድብቅ እየተፈረመ ያለው ነገር ተቀባይነት የለውም። ለሱዳን የሚሰጥ መሬት መኖር የለበትም። ተግባሩ ሕገወጥ ነው። ኢህ አዴግም ለተግባሩ ይጠየቃል።
It is so!!!

Wednesday, May 14, 2014

አንበጣዊ ሃረካት - አዲስ ዶሜንተሪ በኢቲቪ

አንበጣዊ ሃረካት - አዲስ ዶሜንተሪ በኢቲቪ
**************************************
ተመልካቾቻችን <አንበጣዊ ሃረካት> የሚል አዲስ ዶክሜንተሪ ከነገ ጀምሮ በተከታታይ ስለምናቀርብ እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።
ዶሜንተሪውን ለመከታተል እንዲይመቻቹ እነሆ ለቅምሻ ያህል
"አንበጦቹ ከሱማሌ ላንድ ተነስተው አዲስ አበባ የገቡት ለሽብር ተግባር እንደሆነ በቂ መረጃ ... እደግመዋለሁ ከበቂ በላይ መረጃ አለን ... ማስረጃ ግን የለንም አራት ነጥብ"
.......... (ታላቁ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከሰማይ ቤት በእስካይፕ)
"አንበጦቹ ከሱማሌ ላንድ ተነስተው ለሽብር ተግባር አዲስ አበባ እንደገቡ መረጃ አለን .. ማስረጃ ግን የለንም።
... (ታናሹ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ (ቃል በቃል ኮፒ ፔስት ከአራት ነጥቡ ውጪ))
"Successful meeting with the guest Anibetoch ... I am so happy."
.... Dr. Tedros Adhanom Ghebreyesus (የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር)
"አራት ኪሎ ቤተመንግስት በአንበጣ ተወሯል አሉ። ወይ አራት ኪሎ ለስንት አንበጣ ትችያለሽ?"
...... Abraha Desta ከመቀሌ (ይሄን የጻፈው ሌላ ሰው ቢሆን ኖሮ በዘረኝነት ተፈርጆ ነበር) (አብርሽ እኮ ቀልዶ ስለማያውቅ መጀመሪያ ሳየው አካውንቱ ሃክ የተደረገ መስሎኝ ነበር። It is so!!! የሚለውን ፊርማ ሳይ ተረጋጋሁ ... ይልመድብህ እስኪ አንበሳው)
"አንበጦቹ ወደ አዲስ አበባ የመጡት የኦሮሚያን ልዩ ዞን መሬት ለመቀራመት እና ሃብታችንን ለመቦጥበጥ ስለሆነ በሜንጫ አንገታቸውን"
...... (ጃ ነፍሴ ከኒውዮርክ እና ሚኒሶታ)
"አዲስ አበባ ከ23 አመት በኋላ በድጋሚ በአንበጣ ቁጥጥር ስር ወደቀች"
..... Semir Ali ኢሳትን ጠቅሶ
"በተያያዘ ዜና እነዚህ አንበጦች የአንድ ክልል ተወላጆች ሲሆኑ ከመስቀል አድባባይ እስከ መገናኛ ያሉት ሕንጻዎች በሙሉ የእነሱ ንብረት እንደሆነ የአይን ምስክሮች ለኢሳት አረጋግጠዋል"
.... (ኢሳት ሬድዮ እና ቴሌቭዢን)
"አንበጦቹ ከግንቦት ሰባት፤ ከግብጽ፤ ከኤርትራ እና ከፈረንጆች ገንዘብ ተቀብለው አዲስ አበባን እንደወረሩ ከፖሊስ መረጃ አግኝተናል"
.... (ሚሚ ስብሃቱ ከሶስት መአዘን ጠረጴዛ) ... (እርስዎ ከፈረንጅ የተቀበሉት ገንዘብስ የጦጣ ፍራንክ ነው?)
"የኒዎሊብራል ሃይሎች የቀለም አብዮት ለማካሄድ ከሚጠቀሙበት ዋነኛ መንገድ አንዱ አንበጣን በገንዘብ መደገፍ እና ወደ ሌሎች አገሮች ማሰማራት ነው"
..... Merkeb Negash ከጅማ ዩኒቨርሲቲ (ደግሞ ዲግሪዬን ገዝቼው አይደለም) ... lol)
"አንበጦቹ የመጡት አገራችን ካስመዘገበችው እድገት ትምህርት ሊቀስሙ ነው። ካላመናቹኝ ልማልላችሁ ... ብርኒህጎ ይሙት!!!"
..... Sabawi Desalegn ከፌስ ቡክ)
"እነዚህ አንበጦች ከግብጽ ተልከው እንደሚመጡ ከሶስት ወር በፊት አንድ የፈረንጅ ዲፕሎማትን ጠቅሼ ጽፌ ነበር። በዚህም ምክኒያት ዳንኤል ለምን አይታሰርም እያሉ ያወሩት ሰዎች ዛሬ አንበጦቹ መምጣታቸው ሲረጋገጥ ምን ይዋጣቸው? ... ካለ እኔ ሌላ ብሎገር አላዩም እንዴ?"
...... Daniel Berhane ከሆርን አፌርስ
"<እንደምችመለከቹች> አንበጮቹ በዳያፖሯ መሽገው ኢትዮጵያን ለማተራመሽ እንደመጡ እኔ እራሼ ዋሽንግተን ሽኖር አረጋግጫለሁ።
--- ቤን ነኝ ከኢትዮጵያ ፈርስት ("ቤን" ብሎ ኢትዮጵያ?")
"እነዚህ አንበጦች በዋናነት ከሶስት ብሄሮች የተውጣጡ ናቸው። ከአማራ ክልል የመጡት አንበጦች የበላይ ነን ማለት እስካልተው፤ ከትግራይ ክልል የመጡት አንበጦች እኛ ብቻ ማለት እስካልተው፤ የኦሮሚያ ክልል አንበጦችም ኩርፊያቸውን እስካልተው ድረስ ተባብረው ሊኖሩ ስልማይችሉ ወደ ሱማሌ ላንድ ሊመለሱ ይችላሉ"
..... ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና (የመድረክ ሊቀመንበር)
"መክሸፍ እንደ አንበጦች"
..... ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም
በመጨረሻም
"ሁሉም ትክክል ነው ግን በእግዚያብሔር ዞን-ዘጠኞችን Zone9 ፍቱልን"
..... እኔ እራሴ ...ከማርስ ፕላኔት (ደግሞ በሽብርተኝነት ሆ)

Tuesday, May 13, 2014

ተስፋለም ሆይ! ስላንተ ምን ልናገር? ስለልጅነትህ?!

ተስፋለም ሆይ! ስላንተ ምን ልናገር? ስለልጅነትህ?!
ሚያዚያ 18 ቀን 2006 ዓ.ም ንጋት ላይ ትንሿ ስልኬ አንጫረረጭ፡፡ ከእንቅልፌ ብንን ብዬ ስልኬን ተመለከትኩት፡፡ የደወለው ወዳጄከዚህ ቀደም በዚህ ሰዓት ደውሎልኝ አያውቅም ነበር፡፡ ስልኩን ሳላነሳው ‹‹ምን አንዳች ነገር ተፈጥሮ ይሆን?›› ብዬ ማሰላለሌን ተያያዝኩት፡፡ ከ20 ደቂቃ በኋላ ስልኩ በድጋሚ ተደወለ፣ አነሳሁት፡፡ ከደዋዩ ወዳጄጋርም ሰላምታ ተለዋወጥን፡፡ ‹‹ጓደኞችህ ታሰሩ አይደል?›› አለኝ፡፡ ‹‹እነማን?›› በማለት በችኮላ መለስኩለት፡፡ ‹‹ተስፋለም፣ በፍቃዱ ኃይሉ፣ ዞን ዘጠኞች…›› ደንግጬ መረጃው እንደለሌለኝ ነገርኩት፡፡ …ተስፋለም ከመታሰሩ ሁለት ቀናት በፊት ደውሎ ከሥራ ጋር የተገናኘ መረጃ ጠይቆኝ ነበር፡፡
ያለ ወትሮ ስልክ ሲደወል በተቻለ አቅም እረጋ ብሎ ማሰላለሰልን ከተሞክሮ ተምሬያለሁ፡፡ የቀድሞ የአውራምባ ታይምስ ማኔጂንግ ኤዲተር ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደን ከኢትዮጵያ መሰደድ ንጋትላይ ‹‹አለቃችሁ ተሰደደ አይደል?›› ብሎ የነገረኝ፣ እስከአሁን ድረስ በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ መታሰሩ በጣም የገረመኝ፣ የማከብረው እና የምወደው የልጅነት ጓደኛዬ እና ወንድሜ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ነበር፡፡ እንደአንድ ነጻ እና ጎበዝ ጋዜጠኛ ለመረጃ ያለውን ቅርበት ተመልከቱ!
የሌሎቹም የጋዜጠኛ አስማማው ኃይለጊዮርጊስ፣ የጋዜጠኛ እና ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ (በፍቄ)፣ የጦማሪያኑ የማህሌት ፋንታሁን፣ የአጥናፍ ብርሃኔ፣ የዘላለም ክብረት፣ የናትናኤል ፈለቀ፣ የአቤል ዋበላና የኤዶም ካሳዬ መሰል እስርም እጅግ አሳዝኖኛል፡፡ ዋይ! ሀገሬ!
ከተስፋለም ወልደየስ ጋር ትውውቃችን ከለጋ አፍላ ዕድሜያችን ይጀምራል፡፡ ወላጆቹ ጦላይ ወታደራዊ ካምፕን ለቅቀው አዲስ አበባ መኖር ከጀመሩ በኋላ ማለት ነው፡፡ ዛሬ በሕይወት የሌሉት የተስፍሽ ወላጅ እናት ወ/ሮ አበበች አክስት ከወላጅ አባቴ ጋር በጣም የቅርብቤተሰባዊ ትስስር አላቸው፡፡ ወ/ሮ አበበች እና አክስታቸው ለረዥም ዓመታት ልደታ መኮንኖች ክበብ አቅራቢያ አንድ ግቢ ውስጥ ኖረዋል፡፡
ዛሬ በሕይወት የሌሉት ወላጅ አባቱ እና እናቱ እንዲሁም አሁን ላይ በቅርቡ ያለችው እህቱ ራሄል ተስፋለምን ‹‹አቡሽ/አቡሼ›› በማለት ነበር ፍቅራቸውን በመግለጽ የሚጠሩት፡፡ እኔም እስከቅርብ ዓመታት ድረስ ‹‹አቡሽ›› ነበር የምለው፡፡
ከተስፋለም ጋር አብሮ በመሆን በነበሩን አጋጣሚዎች ሁሉ በጣም ደስ የሚል ጨዋታ፣ እያወጉ ረዥም ወክ የማድረግ ተደጋጋሚ ልምድናእውቀት የመካፈልየቁም ነገር ጊዜያቶችን በልጅነታችን በደንብ አጣጥመን አሳልፈናል፡፡ …እነዚህ መቼም አይደገሙ! ትዝታ ሆነው አልፈዋል፡፡ ተስፋለም አዲስ ነገር ለማወቅ እና አዲስ ነገርን ለመንካት ያለውን ጉጉት እና ትጋት ወደር የለውም፡፡ አከባቢያዊ፣ ሀገራዊ እና ዓለማቀፋዊ መረጃዎችን ከአቅሙ በላይ ለማወቅ ይታትር ነበር፡፡ ለዕውቀት እና ለመረጃ የነበረውም የተንቀለቀ ስሜት እና ጥማትየላቀ ነው፡፡ ለዚህ ይሆን፣በብዙዎች ዘንድ በኢትዮጵያ የፕሬስ ታሪክ ትልቅ ተምሳሌት ከነበረችው የ‹‹አዲስ ነገር›› ጋዜጣ መስራቾች መካከል አንዱ የሆነው?
ተስፋለምን ልጅነት ካወኩት ጊዜ አንስቶ የንባብ ቀበኛ ነው፡፡ ገበያ ላይ ያሉ መጽሐፍትን፣ ጋዜጦችንና መጽሄቶችን ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ከሰዎች ይዋሳል፣ ያነብባል፣ ይገዛል፣ አደራጅቶ በጥንቃቄ ያስቀምጣል፡፡ ለምሳሌ፣ ሆሊውድ ጋዜጣ እና ኢንፎቴይንመንት መጽሄትለአንባቢያን ቀርበው ህትመታቸው እስከተቋረጠባቸውጊዜያት ድረስ ያሉትን ቅጾች በተስፋለም ቤት አሁንም ድረስ በክብር ተቀምጠው ያገኟቸዋል፡፡ የሬዲዮ እና የቴሌቭዥን ፕሮግራሞችንበሚያስገርምመልኩ በአንክሮ ይከታተላል፡፡ ፊልሞችንም እንደዚሁ፡፡ የተመለከታቸውን ፊልሞች መቼ እንደተመለከታቸውጠቅሶ ከነዕርሶቻቸው ማስቀመጥም ልምዱ ነበር፡፡ ዛሬ ላይ ምን እንዳደረጋቸው ባላውቅም በርካታ ግጥሞችንም ይጽፍ ነበር፡፡ ግለ-ሀሳቡንም ይጽፋል፡፡
ተስፋለም፣ የጋዜጠኝነት ሙያን መማር ጥልቅ ፍላጎቱ መሆኑንለወላጆቹ ተናግሮ ካሳመነ በኋላ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ጋር በሚገኘው በቀድሞ የማስሚዲያ ማሰልጠኛ ኤጀንሲ የጋዜጠኝነትትምህርትን ለመመዝገብ የሄደው ከእኔ ጋር ነበር፡፡ …ከዚህ መደበኛ ትምህርት ባሻገር በሂደት ሙያውን በራሱ ጥረት ለማሻሻል ጥረቱ ትልቅ ነበር፡፡ በዚህ ወቅት የፍሪላንስ ሥራን በጎን በመጀመሩ ምክንያት እና በትምህርት ጥናት የተነሳ አምሽቶ ከእኩለ ሌሊት በኋላወደቤት መግባትን ልምድ አድርጎም ነበር፡፡በዚህ ወቅት በመኖሪያ ቤቶቹ ግቢ ውስጥ በጣም አምሽቶ የሚገባው ተስፋለም ነው፡፡ ተስፋለም ‹‹ለእውነተኛ ጋዜጠኝነት የተፈጠረ›› ብል አፌን ሞልቼ ነው፡፡ ሙሉ ሕይወቱን ለጋዜጠኝት ሙያ ስለመስጠቱም ሆነ ስለጥንቃቄውእመሰክራለሁ፡፡
አሁን ላይ ቀን እና ዓመተምህረቱን ዘንግቼዋለሁ፡፡ ወላጅ አባቱ ለረዥም ወራት እያመማቸው እና እየተሸላቸው ከቆዩበኋላአመሻሽ ላይ ሕይወታቸው አለፈ፡፡ በቦታውም ነበርኩ፡፡ ተስፋለም ግን ከነፍሱ ለሚወደው ሙያ ሌሊቱን ሙሉ ሲሰራ አድሮ ንጋት ላይ ወደቤቱ ሊገባ የአጥሩንበር ሲከፍት መኖሪያ ቤታቸው በሰዎች ተከብቧል፡፡ ድንጋጤው ፊቱ ላይ በግልጽ ያስታውቅበት ነበር፡፡ ማንምም ሳያናግር ወደቤቱ ዘለቀ፡፡ በጥልቅ የሚወዳቸው እና የሚሳሱለትየወላጅ አባቱ ሞት እውነት መሆኑን ተረዳ፡፡ ፊቱ ተቀያየረ፣ ግራ ተጋባ፣ አይኖቹ በዕንባ ተሞሉ፣ የአባቱን መሪር ሀዘን …
ከደቡብ ዩኒቨርሲቲ በደን ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ከተመረኩኝ በኋላ አንድ ቀን አመሻሽ ላይ ከተስፋለም ጋር ከልደታ ተነስተን ወደቦሌ መስመር ወክ በማድረግ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይበተመስጦ እያወጋን ነበር፡፡ አስታውሳለሁ፣ ወሎ ሰፈር ጋር አንድ ጥያቄ ጠየኩት፡፡ ‹‹በተማርኩት ትምህርት ደስተኛ ብሆንም ነፍሴ ግን አልረካችም›› አልኩት፡፡ ‹‹ኤልያስ ውስጥህን በእርጋታ አዳምጠው›› በማለት ተስፋለም መለሰልኝ፡፡ እውነቱን ለመናገር ውስጥን ማዳመጥ ምን ማለት እንደሆነ እስከዚያች ቅጽበት ድረስ አላውቅም ነበር፡፡ ዛሬ ከነፍሴ በምወደው የጋዜጠኝነት ሙያ ላይ እንድገኝ ‹‹…ውስጥህን አዳምጠው›› የሚለው የተስፋለም ወንድማዊ ምክር እጅጉን እንደጠቀመኝ ዛሬ ላይ ተነፈስኩት፡፡ ተስፍሽ አስተዋይ የሆነ የትንሽ ትልቅ ነበር፡፡
ተስፍሽ፣ ድንገተኛ እስርህ አመመኝ፣ ቁጭት ፈጠረብኝ፡፡ ዛሬም ድረስ ውስጤን እያንገበገበው ይገኛል፡፡ ሆኖም እሰሩ የዜጎችን ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ ሕገ-መንግስታዊም ሆነ ዓለማቀፋዊ መብት እንዲከበር ለምወደው ሙያ ይበልጥ በጽኑ እንድቆም ጤናማ እልህ አቀጣጥሎብኛል፡፡ የእናንተ እስርም በነጻው ፕሬስ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ጋዜጠኞችን ልብ በሃዘን ነክቷል፣ ንዴታዊ ስሜት ውስጥም ከትቷል፡፡ በጋዜጠኝነት ለመስራት ‹‹ሙያው አስጠላን›› ያሉኝም አሉ - መፍትሄ ባይሆንም፡፡
በአዲስ አበባ አራዳ ፍርድ ቤት የጓደኞችህን እና የአንተን ሁለት እጅችህ በብረት ካቴና ተጠፍንገው ስመለከት ደግሞ በመንግሥታችን እጅጉን አዘንኩ፡፡ ጠረጼዛ ላይ ያሉ ጋዜጦችን፣ መጽሄቶችንና መጽሐፍቶችን እንኳን ከልጅነትህ ጀምሮ ማዝረክረክ የማትወደው ልጅ ከነፍስህ የምትወዳትን እምዬ ኢትዮጵያን ከሙያ አጋሮችህ ጋርበሽብር እና በአመጽ ለማተራምስ ተንቀሳቅሰሃል ብዬ ለሰከንድ እኩሌታ እንኳን በጭራሽ አላስብም፡፡ለምትወደው ሙያህ ዘወትር ሚዛናዊ ዘገባን ለማቅረብ መታተርህ መንግሥት ላይ ስጋት ፈጥሮ ይሆን እንዴ? …በእናንተ ላይ የሚቀርበውን ክስ ለማወቅ በጣም የጓጓሁትምለዚሁ ነው፡፡
አይደለም ከልጅነቴ ጀምሮ በደንብ የማውቀውን ተስፋለምን ቀርቶ ሌሎች የታሰሩት የሙያ አጋሮቻችንእንኳን በሚወዷት ሀገር ላይ ሽብር እና አመጽ ለማካሄድ የማሴርዓላማ እና ዕቅድ አላቸው ብዬ ለማሰብ ፍጹም እቸገራለሁ፣ይህ የግሌ እምነት ነው፡፡
…ተስፋለምን ለረዥም ዓመታት ከማውቀው አኳያ ብዙ ማለት ብችልምለዛሬ የልጅነት ሕይወቱን ብቻ ጠቅሼ ለማለፍ ወደድኩ፡፡ተስፍሽ፣ ንጽሕናህ እና ሙያዊ ጥንቃቄህ ነጻ ያወጣሃል!!! ነገር ግን፣ በጊዜው የኢሕአዴግ መንግሥት የፍትሕ ሥርዓት ላይ እምነት ካጣሁ ቆየሁ፡፡
እንደመውጫ
ስለተስፋለም በሥራው ላይ ስለላው ባህሪ እና ትጋት በቅርበት የሚያውቁት ጓደኞቹ፣ ባልደረቦቹና ወዳጆቹ በማኅበራዊ ድረ-ገጽ እና በሕትመት ሚዲያዎች ላይ ሃሳባቸውን መግለጻቸው ይታወቃል፣ አሁንም እየገለጹ ነው፡፡
ከእነዚህም መካከል ሁለትጓደኞቹለእሱ ከጻፉለት ጽሑፎች ውስጥመርጬ በድጋሚ በዚህ ጽሑፌላይ ባሰፍርለት ልቤ ወደደ፡፡ የቀድሞ አዲስ ነገር ጋዜጣ ባልደረባው ጋዜጠኛ ማስረሻ ማሞ በፌስ ቡክ ገጹ እንዲህ ብሎ ነበር፡-
‹‹ …ተስፋለም የግል ፖለቲካ አመለካከቱ ከጋዜጠኝነቱ ጋር እንዳይጋጭበት የሚጠነቀቅ ወጣት ነው፡፡ ከጋዜጠኝነት ከፍ ያለ ክብር እና ዋጋ ይሰጣል፡፡ አንዳንዴ እቀናበታለሁ፡፡ ስለሚዛናዊነቱ እቀናበታለሁ፡፡ ስለሚዛናዊነቱ፣ ስለተገቢነትና ስለእውነተኛ ዘገባ አብዝቶ ይጨነቃል፡፡ ማንኛውም ዓይነት ዘገባ ከትክክለኛው ወንዝ ተቀድቶ እንዲፈስ ይመኛል፣ ያደርጋል፣ ይጓዛል፡፡ መጀመሪያ ለሙያው ታማኝ መሆንን ያስቀድማል፡፡ ከተስፋለም ጋር ሳወራ ከታናሽ ወንድሜ ጋር የማወራ ነው የሚመስለኝ፡፡ ኢሕአዴግ እንደተስፋለም መሥመራቸውን ጠብቀው ለሚሰሩ ሰዎች የማይመለስ ይሆናል ብዬአስቤ አላውቅም፡፡ አሁንም መታሰሩን ማመን እውነት እውነት አልመስልህ ብሎኛል! የሚሰማኝ እልህ፣ ቁጭት፣ ተስፋቢስነትና ቁጣ ነው፡፡ እኔ እስከማውቀው ድረስ ተስፋለም የማንም ወገን አይደለም፡፡ ብቻውን በራሱ የቆመ ጋዜጠኛ ነው፡፡››
ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ ደግሞ ባለፈው ሳምንት ለንባብ በበቃው ‹‹ፋክት› መጽሔት ላይ ‹‹ትንሹ ተስፋለም›› በሚል ርዕስ ከጻፈችው የቀነጨብኩትን ደግሞ እንዲህ አስቀመጥኩት፡-
‹‹በአነጋገሩ ቀጥተኛና በጠባዩ ገራገር ነው፡፡ ‹ጥርስ ያሳብራል› በሚባሉ ስብሰባዎች፣ በኃይለ ቃል በተሞሉ የኢዲቶሪያል ውይይቶችና ግምገማዎች ሳይቀር ስሜቱን ውጦ በተረጋጋ መንፈስና በለዘብታ ቃል መመላለስ ጸጋው ነው፡፡ በኤዲቶሪያል ጠረጼዛዎች እና ዴስኮች ዙሪያ በሐሳብ ለመግባባት ከሚደረጉ ግብግቦች ውጭና ባሻገር ቂም እና በቃል አያውቅም፡፡ በደሙ ውስጥ ከሚዘዋወረውና ራሱን ከሰጠለት የጋዜጠኝነት ሙያውና የጋዜጠኝነት መርህ የተነሳ ሌላ ዓለም፣ ሌላ ኑሮ ያለም አይመስለው፡፡ ለእርሱ ኑሮው፣ ለእርሱ ዓለሙ፣ ተጨባጭ መረጃን ከወገናዊነት በጻዳ መልኩ ለሕዝብ ማድረስ ነው፡፡…››
…ከቀናቶች በኋላም ለተወሰኑ ወራት በዕንቁ መጽሄት ላይ አብረን በመሰራት ስለማውቀው ጋዜጠኛ እና ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ (በፍቄ) ብዕሬን አንስቼ እጽፋለሁ፡፡
በእስር ላይ የሚገኙትን፣ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት በፖሊስ እንደተፈጸመባቸው በፍርድ /ቤት የተናሩትን ጋዜጠኞችን እና ጦማሪያን እግዚአብሄር ጽናት፣ ብርታትና ጥንካሬ ይስጣቸው፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

የዞን ዘጠኝ ብሎግ ጸህፊያን የታሰሩበት ምክንያት፤ እኔ እንደደረስኩበት...

የዞን ዘጠኝ ብሎግ ጸህፊያን የታሰሩበት ምክንያት፤ እኔ እንደደረስኩበት...
እንዚህ ልጆች ከታሰሩ በኋላ "ሆደ ሰፊው" መንግስታችን ለምን አሰራቸው ብዬ አጥብቄ ስመራመር ቆይቻለሁ። በመጨረሻም እነሆ የምርምሬ ውጤት በሁለት አንቀጽ እንደሚከተለው ይቀርባል።
ዘጠኝ ጓደኛማቾች በአንድ መድረክ ላይ አብረው ለመጻፍ ተደራጁ፤ የሚጸፉበትን መድረክም ዞን ዘጠኝ በለው ሰየሙት። በዞን ዘጠኝ የጡመራ መድረካቸው ለእስር የሚያበቃ ክፉ ነገር አንዳችም እንዳልተናገሩ ከምላሴ ፀጉር በዬ ምዬ እኔ እማኝ እሆናለሁ። እገረ መንገዴንም ሀገራችን ሰዎችን ለምን ጻፋችሁ ብላ እንደማታሰርም ታማኙን ኢቲቪን ጠቅሼ እመሰከራለሁ... መቼም ዘመኑ ታማሚ እና ታማኝ የተምታታበት ዘመን ሆኗል!
እናም እንደምርምሬ ከሆነ ዞን ዘጠኞች የታሰሩት ስለጻፉ አይደለም። ዘጠኝ ሆነው ከመንግስት እውቅና ውጪ የጠበቀ ጓደኝነት ሰለመሰረቱ ነው። መንግስታችን በአሁኑ ጊዜ ዜጎች በ አንድ ለአምስት አደረጃጀት እያደራጀ ባለበት ወቅት እነርሱ ከዚህ አደረጃጀት ውጪ ዘጠኝ ሆነው መደራጀታቸው፤ ለመታሰራቸው ዋና ምክነያት ሆኗል። እነዚህ ወጣቶች አንድ ለአምስት አደረጃጀቱ ካለተመቻቸው በመንግስት እውቀና ባለውን ጥቃቅን እና አነስተኛ ተደራጀተው ያሻቸውን ማደረግ ሲቸሉ እነርሱ አንድ ለአምስትም፤ አነስተኛ እና ጥቃቅንም ሳይሆኑ ዞን ዘጠኝ በሚል ስም ልማታዊ መሆኑ በመንግስት ያልተረጋገጠለት ጓደኝነት መመስረታቸው ታላቅ ጥፋት ሆኖ ተገኝቷል።
መደምደሚያ
ከንግዲህ ኢህአዴግዬ በህይወት ሳለች፤ የሰፈር ወዳጅነትም ሆነ የትምህርት ቤት ጓደኝነት ቁጥሩ ያነሰ እነደሆነ፤ በአንድ ለአምስት አደረጃጀት ቁጥሩ የበዛ ከሆነ ደግሞ በአነስተኛ እና ጥቃቅን መታቀፍ ይገባዋል። ያ ሳይሆን ቢቀር ግን ስብስቡም ሆነ ማህበሩ ቤቱ ቃሊይሆናል!
ምስኪን ኢህአዴግዬ ስንቱን ፈርታ፤ ስንቱንስ አቅፋ ትችለዋለች! እንልና... (በቅንፍም፤ ያገኙትን ሁሉ ልቀፍ ማለት ምስኪነነት ሳይሆን አመንዝራነት ነው በሎ ማሽሟጠጥ ይቻላል!) ብለን ቅንፋችንን ዘግተን ሃሳባችንንም እንቋጫለን!

Source -Abe tokichaw

ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብና በተለይ ለሀገር ተረካቢ ወጣትና ምሁራን ብሎም በውጪ ለሚገኙ ዜጎች!! ከባለራዕይ ወጣቶች ማህበር የተሰጠ መግለጫ

 በተለይ በህዝቧ ያኗኗር ዘይቤ በኢትዮጵያ እድገት ውስጥ ያበበና ጎልቶ የወጣ ልዕልናዋም ከአጉረ አፍሪካ ተሻግሮ ለአለም መደነቂያ የሆነች ሀገራችን ላይ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አጥልቶ ያለው የተቃርኖ እዳ የእርስ በርስ ግጭት እንዲፈጠር እየተጠነሰሰ ያለና በተግባራዊነቱም ጎልቶ የታየበት ጊዜ አይታወስንም በመሆኑም ዜጎች በመንግስት ትንኮሳና ሸር እየተፈፀሙ ያሉት ዜጎችን ከቦታቸው የማፈናቀል ለጠየቁት ጥያቄ አወንታዊ እርምጃ መውሰድ በጋዜጠኞችና በጦማሪያን ላይ የእስር እንዲሁም በቶፎካካሪ ፓርቲ አባላትና መሪዎች ላይ የሚደርሰው እንግልትና ወከባ የዚህች ሀገር ጎዞ ወዴት እያመራ ነው የሚለው እጅግ አሳሳቢ ነው ከዚህም በተረፈ በሚፈጠረው ግርግር ሰፊው የሀገራችን ህዝብ ተጎጂ የሚሆን በመሆኑና በተለይም በግንባር ቀደምነት የሀገራችን አምራችና አንቀሳቃሽ ብሎም ሀገር ተረካቢና አንቀሳቃሽ በምንለው ወጣት እጅጉን እየከፋ በመሄዱና ለጥቃትም ተጋላጭ በመሆኑ ይህን መግለጫ ለማውጣት ተገደናል፡፡
1. የሀገራችንን ህዝቦች ለመከፋፈልና ወደ ማያቋርጥ እልቂት ለመምራት በፈጠራ ታሪክ ላይ ተመስርቶ እየተሰራበት ያለው ሴራ ባስቸኳይ እንዲቆም እና የእልቂት መነሻ የሚሆን በተለይም አኖሌ የተገነባው ሀውልት ባስቸኳይ እንዲፈርስ በምትኩም ህዝቦች በጋራ ተቻችለው የሚኖሩበትና የጋራ አሴት ሊፈጥር የሚችል የመደጋገፍና የመረዳዳት ህልውናውን የሚያጠናክር መዘከር እንዲሰራ እንጠይቃለን፡፡
2. መንግስት በህዝቡ ዘንድ መግባባትና መፋቀር እንዲሰራና ሀገራችን ለዜጎችም ብሎም ለወጣቶች ምቹ ማድረግ ሲጠበቅበት ዜጎችን ኢ.ህገ መንግስታዊ እና ኢ-ፍታዊ በሆነ መልኩ በሀገራቸው በየትኛውም ክፍለ ሀገር የመኖርና ሀብት የማፍራት መብታቸውን በመጣል ከቄያቸው እና ተከባብረው እና ተፋቅረው ከኖሩት ህዝብ በሀይል የማፈናቀል እርምጃ ባስቸኳይ እንዲቆም ይህን 

Monday, May 12, 2014

9 ጋዜጠኞችና ፀሐፊዎች ምን ሰርተው እንደታሰሩ እስካሁን አልተገለፀም

9 ጋዜጠኞችና ፀሐፊዎች ምን ሰርተው እንደታሰሩ እስካሁን አልተገለፀም
"እስረኞች፤ ድብደባና ግርፋት ደርሶብናል አሉ
ከአለማቀፍ የመብት ተሟጋች ተቋም ጋር በገንዘብና በሃሳብ ተደራጅተው በኢንተርኔት አገሪቱን ለማሸበር አሲረዋል በሚል የታሰሩት 9 ጋዜጠኞችና የ“ዞን 9” ፀሐፊዎች ላይ ምርመራ እንዳልጨረሰ በመግለጽ ተጨማሪ ጊዜ እንዲፈቀድለት ፖሊስ የጠየቀ ሲሆን፤ ፍ/ቤት የ10 ቀን ቀጠሮ ሰጠ፡፡ ከሁለት ሳምንት በፊት ተጠርጣሪዎች ሀገሪቱን ለማሸበር በኢንተርኔት ማህበራዊ ሚዲያዎች አሲረዋል ያለው ፖሊስ፤ ሰሞኑን ተጠርጣሪዎቹ ፍ/ቤት ሲቀርቡ፣ የተያዙት በማህበራዊ ድረገፆች ላይ በፃፉት ሳይሆን ከውጭ አሸባሪ ኃይሎች ጋር በመደራጀት፣ አገሪቱን ከቀጣዩ ምርጫ በፊት ለማሸበር እና የሽብር ሴራውንም ለመምራት ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸው ነው ማለቱን የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ አቶ አመሀ መኮንን ተናግረዋል፡፡"

እንደሰሞኑ የኢትዬጵያን ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ወቅት የለም ማለት ይቻላል ?

እንደሰሞኑ የኢትዬጵያን ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ወቅት የለም ማለት ይቻላል ። ዘርኝነት የመጨረሻው ምእራፍ ላይ በከፍተኛ ፍጥነት እዬተምዘገዘገ ነው። በኦሮሞ ተማሪዎች የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም በሚል ሽፋን እልም ያለ የዘረኝነት ምግባር ታይቷል። የፈረደባቸው የአማራ ተወላጆች ዛሬም ሂዎታቸው ተቀጥፏል። ንብረታቸው ወድሟል ። አማራ ስለሆኑ ብቻ!! ህወሓት እያራመደችው ያለውን ዘረኝነት ግብ በማስመታት ደረጃ ተማርኩ የሚለውን የኦሮሞ ወጣት የሚደርስበት ጠፍቷል።
የአማራ ህዝብ ምን ያህል በችግር እዬተጠበሰ …በዲሞክራሲ እጦት እዬተሰቃዬ… እንደሆን ፅንፈፆቹ የኦሮሞ ወጣቶች ሊረዱለት አልቻሉም። ሆዱን በጠፍር እያሰረ ያሰተማራቸው ልጆቹ ከዛሬ ነገ ዩንቨርስቲ ተመርቀው ወጥተው ራህቤን ያስታግሱልኛል ሲል በዘረኝነት በአበዱ ፅንፈኞ እዬተቀጠፉነው።ለኦሮሞ ህዝብ ነፃነት ስንታገል የአማራን ህዝብ ነፃነት እዬጨፈለቅን ከሆነ ትልቅ ስህተት ነው።
የኦሮሞ ወጣቶች እባካችሁ አስተውሉ!! ለኦሮሞ ህዝብ ጠላቱ አማራ፣ትግሬ……አይደለም። ስርአት ነው። ያን ሥርአት ደግሞ ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ የቀመሰው ነው። በጋራ ሆነን ህወሓት የተባለ የማፍያን ስርአትን ታግለን ስንጥል ነው ነፃ ልንወጣ የምንችለው ። እንደሰሞኑ ከሆነ ግን እንጨራረሳለን እመኑኝ!! የህወሓትን ድራማ ልብ ማለት አቅቶናል።
እባካችሁ… ከአማራ ህዝብ ላይ እጃችሁን አንሱ!! የእኛ እንዲህ መሆን ከህወሓት ሰርግ እና ምላሽ ነው። አማሮች በአክራሪ ኦሮሞዎች ተገደሉ ኦሮሞዎች ደግሞ በአጋዚ ጥይት ተለቀሙ። ማን ተጎዳ ማን አተረፈ? ልብ ያለው ልብ ይበል!!!

source -

Messafint Bazezew

እንግሊዝ ፍርድ ቤት ታሪካዊ የተባለ ውሳኔ አሳለፈ

እንግሊዝ ፍርድ ቤት ታሪካዊ የተባለ ውሳኔ አሳለፈ
May 12/2014
ግንቦት ፬ (አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕራይቬሲ ኢንተርናሽናል የተባለው ዜጎችን ከመንግስታዊ ስለላ ለመታደግ የተቋቋመው ድርጅት የእንግሊዝ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣንን ከሶ አስደሳች የፍርድ ውሳኔ ማግኘቱን ገልጿል።
ጋማ ኩባንያን ፊን ፊሸር እየተባለ የሚጠራውን የኮምፒዩተርና የስልክ የመረጃ መጥለፊያ ሶፍት ዌር እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሰብአዊ መብቶችን ለሚጥሱ አገሮች መሸጡ በካናዳው ሲትዝን ላብ ላብራቶሪ መረጋጋጡን ተከትሎ ፕራይቬሲ ኢንተርናሽናል በአገር ውስጥ ገቢና ጉምሩክ መስሪያ ቤት ላይ ክስ መመስረቱ ይታወቃል።
እንግሊዝ የአገር ውስጥ ገቢ መስሪያ ቤት ከአገሪቱ የሚወጡ ምርቶች በቂ ቁጥጥር ሳይደረግባቸው እንዲወጣ ፈቃድ ሰጥቷል በሚል ነው ክስ የተመሰረተበት።
ፍርድ ቤቱ የአገር ውስጥና የጉምሩክ መስሪያ ቤት አስፈላጊውን መረጃ እንዲሰጥ ውሳኔ አስተላልፏል። ኮምፒተራቸው የተሰለለባቸው ዶ/ር ታደሰ ብሩ ውሳኔው አስደሳች ነው ብለዋል።

Sunday, May 11, 2014

‪#‎BRINGBACKOURGIRLS‬



‪#‎BRINGBACKOURGIRLS‬ For generations, Ethiopian women have played major roles in their society. They are the center of the family and shouldered immense responsibilities. They are strong and courageous fighters for freedom. They have come a long way, but they still have a long way to go to achieve equality. The major obstacles in women’s advancement in Ethiopia are the abject poverty and the traditional harmful practices that hinder women’s progress. Because of these, women have continued to face enormous hardships. On the other hand, their resilience in the face of all impediments is quite amazing.

በህቡዕ መደራጀት ወንጀል ነው???

የዞን 9 ጦማሪያን ሁለተኛ ክስ ላይ ያለኝ የህግ አስተያየት (በእዮብ መሳፍንት )

በህቡዕ መደራጀት ወንጀል ነው???
በኢፌድሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 31 “ማንኛውም ሰው ለማንኛውም አላማ የመደራጀት መብት አለው፡፡ ሆኖም አግባብ ያለውን ህግ በመጣስ ወይም ህገመንግስታዊ ስርአቱን በህገወጥ መንገድ ለማፍረስ የተመሰረቱ ወይም የተጠቀሱትን ተግባራት የሚያራምዱ ድርጅቶች የተከለከሉ ይሆናሉ” ይላል፡፡ ከዚህ አንቀፅ በግልፅ እንደምንረዳው በህቡዕም ሆነ በግልፅ መደራጀት መብት ነው፡፡ መደራጀት የሚከለከለው “ህግ በመጣስ ወይም ህገመንግስታዊ ስርአቱን በህገወጥ መንገድ ለማፍረስ” ከሆነ ብቻ ነው፡፡ስለሆነም “ፖሊስ” (በተግባር ከሳሹ ኢሃዲግ ቢሆንም) በዞን 9 ጦማሪያን ላይ ባቀረበው ክስ በህቡዕ መደራጀትን በራሱ ወንጀል ለማስመሰል መሞከሩ ከህግ አግባብ ውጪ ብቻ ሳይሆን ህገመንግስቱን የሻረና የናደ ተግባር ነው፡፡ አላማውም ማንኛውንም መደራጀት ማስፈራራትና ሰዎችን ከመደራጀት እንዲቆጠቡ ማድረግ እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡Zone 9 bloggers
ሲጀመር ዞን9 የጦማሪያን ስብስብ እንጂ ህጋዊ ሰውነት ያለው የተደራጀ አካል ወይም ድርጅት አይደለም፡፡ ለዚህም ነው አቃቤ ህግ ዞን 9ን በቀጥታ ሊከሰው ያልቻለው (በህግ መሰረት ህጋዊ ሰውነት የሌለውን አካል መክሰስ ስለማይቻል)፡፡ መሰባሰብን እና መደራጀትን በቅድሚያ መለየት ያስፈልጋል፡፡ ሁሉም ስብስብ መደራጀት አይደለም፡፡ከዚህ በፊት በልጆቹ ላይ ፖሊስ መስርቶት የነበረውን “ራሱን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ብሎ ከሚጠራ ድርጅት ጋር አብሮ መስራት” የሚለው ክስ እንደማያዋጣ እንደገባው ሁሉ አሁንም ይሄኛው ክስ አያዋጣም፡፡
2. ሁለተኛው የክሱ ነጥብ “ከሽብርተኛ ቡድን ጋር አብሮ መስራት”
ይህ ሽብርተኛ የተባለው ቡድን የትኛው እንደሆነ ባይገለፅም በኢትጲያ ውስጥ ሽብርተኛ የተባሉት ግንቦት 7፣ ኦነግ፤ ኦብነግ እና አልቃይዳ ብቻ ናቸው፡፡ ስለዚህም ልጆቹ ከነዚህ ድርጅቶች ከአንዱ ጋር ሰርተዋል ብሎ ፖሊስ ካመነ ማስረጃ ሊኖረው ይገባል መለት ነው፡፡ ስለዚህም ማስረጃ ላሰባስብ በሚል ፖሊስ ተጨማሪ ጊዜ መጠየቁ አስቂኝ ነው፡፡ መጀመሪያ አስሮ ማስረጃ ማሰባሰብ ማለት ወንጀል መፈብረክ እንጂ ወንጀልን መክሰስ ዐያደለም፡፡
ከነዚህ ከላይ ከጠቀስኳቸው ድርጅቶች ውስጥ አንደኛው የውጭ ሀገር ድርጅት ሌሎቹ ሁለቱ ደግሞ ብሄር ተኮር ድርጅቶች ስለሆኑ ፖሊስ ሊል ያሰበው ምናልባት ግንቦት 7ን ሊሆን ይችላል ወይም ባለፈው ክስ “ራሱን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ብሎ ከሚጠራ ድርጅት” ያሉትን ድርጅት ደረጃውን ወደ አሸባሪ ድርጅት ከፍ አርገውት ሊሆን ይችላል፡፡ እኔ በግሌ ልጆቹ በብሎጋቸው የፃፉት ሰላምን፤ አንድነትን፤ ፍቅርን፤ የሰባዊ መብት መከበርን፤ ዶሞክራሲን እንጂ አንድም ቀን ሽብርን ሲፅፉ አይቼ አላውቅም፡፡ እነዚህ ነገሮች ሽብር ከተባሉም ሽብር መልካም ነገር እንጂ መጥፎ ነገር አይደለም፡፡
ስለዚህም እጠይቃለሁ የዞን 9 ጦማሪያን ወንጀል ሰርተዋል ብዬ አላምንምና ባስቸኳይ ይፈቱ፡፡

የህወሐት/ኢህአዴግ ፌዝ ‪#‎በሬድዋን‬ አንደበት!!

የህወሐት/ኢህአዴግ ፌዝ ‪#‎በሬድዋን‬ አንደበት!!
አቶ ሬድዋን ትላንት መግለጫ ሰጥተው ነበር በመግለጫቸውም መንግስታቸው 23ኛውን ግንቦት-20 ከግንቦት 01 - 30 "ሩቅ አስባ ሩቅ ለማደር የምትተጋ ሀገር" የሚል ሞቶን በማንገብ ለማክበር መዘጋጀቱን ገልፀዋል።የተጠየቁትን የተለያዩ ጥያቄዎች ሲመለሱ አቶ ሬድዋን እንዲህም አሉ "ከግንቦት-20 ድል በኋላ ኢትዮጵያ ትልቅ ለውጥ ውስጥ ገብታለች በከፍተኛ ሁኔታም እያደግች ነው፤የተወሰኑ የአፈፃፀምና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ቢኖሩብንም ዲሞክራሲያችን እያደገና እየጎለበተ ነው፤ኢትዮጵያን አኮብኩቦ ከመሬት መነሳት እነደጀመረ አውሮፕላን ውሰዷት አውሮፕላኑ የተስተካከለ ከፍታ እስኪደርስ ትንሽ መንገጫገጭ እንደሚገጥመው ሁሉ አሁን እኛ ያሉብን ትናንሽ ችግሮችንም ወደ አሰብነው ለውጥ ስንገሰግስ እንደሚገጥሙን መንገጫገጮች ውሰዷቸው"።የሩቅ የሩቁን እንኳን ብንተወው ትላንት በአምቦና በተለያዩ ቦታዎች ጥያቄያቸውን በሰላማዊ መንገድ ያቀረቡ ወጣቶችን የገደለው፣ያቆሰለውና ያሰረው ፤ትላንት ስለ ፍትህና ነፃነት በቅን ልቦና የፃፉ ጋዜጠኞችንና ጦማሪያንን እስር ቤት ወርውሮ ሌት ከቀን በግርፋት የሚያሰቃየው ፤በእምነት ተቋሞች ገብቶ መጅሊሱንም ሲኖዶሱንም የተቆጣጠረው ህወሐት/ኢህአዴግ ነው እነግዲህ የሩቅ አሳቢያችን ይህ ሁሉ በደልና ግፍ ነው ትንሹ መነገጫገጭ።ጅብ የማያውቁት ሀገርን አልተርትም ህወሐት/ኢህአዴግ የምናውቀው የቀን ጅብ ነውና ኢትዮጵያ አይደለም የሩቁን ልታልም ቀርቶ ዛሬዋን አጨልሞ ነገዋን እንዳታይና እንዳታስብ ያደረገ ስርዓት ስለ ሩቅ አላሚነት ሲደሰኩር መስማት በቆሰልነው ቁስላችን ላይ የማላገጥንና የእብሪትን እንጨት መስደድ ነው።አቶ ሬድዋን ግዴለም ኢትዮጵያን አኮብኩቦ ከመሬት መነሳት እነደጀመረ 80 ሚሊዮን መንገደኞች እነደጫነ አውሮፕላን እንወሰዳት ህወሐቶችን/ኢህአዴጎችንስ? በግንቦት-20 ቀን የጦር መሳሪያ ታጥቀው አውሮፕላኑን በጉልበት ጠልፈው መንገደኞቸን በማነገላታትና በመገደል እነደተጠመዱ አውሮፕላኑን ከነ 80 ሚሊዮን መንገደኞቹ የመከስከስ አደጋ እነዲጋረጥበት እነዳደረጉ አሸባሪዎች??
‪#‎ሀናመታሰቢያ‬ 02/09/06

የልጆቻችሁ እስር አንጀታችሁን ላሳሰራችሁ መልካም የእናቶች ቀን

መልካም የእናቶች ቀን
(የልጆቻችሁ እስር አንጀታችሁን ላሳሰራችሁ)
ጽዮን ግርማ
እኔና ጓደኛዬ (ሊሊ) የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ)ን ደጅ የረገጥነው በጠዋት ነበር፡፡ ምግብ ማቀበል እንጂ ታሳሪውን ማግኘት ስለማይቻል የግቢው በር እንደተከፈተ ለልብ ወዳጃችን የወሰድነውን ቁርስ ሰጥተን ያደረ ተመላሽ ዕቃ እስኪመጣልን ከመግቢያው ፊት ለፊት ባለው ድንጋይ ላይ ቁጭ ብለናል፡፡ቀዝቀዝ ባለው አየር ላይ ጥቂት ካፊያ ስለነበር ቅዝቃዜው ኩርምት አድርጎናል፡፡ ጥቂት ቆይቶ አንዲት እናት በስስ ፌስታል አንድ አራት የሚኾን ፓስቲ (ቤት ውስጥ የሚጠበስ ቂጣ መሰል ብስኩት) ጠቅለል አድርገው ይዘው ወደኛ መጡ ፊታቸውን ጭንቅ ብሎታል፡፡ 
የመጨረሻውና የ22 ዓመት ወንድ ልጃቸው ሰሞኑን የታሰረባቸው እናት ናቸው፡፡ ‹‹ዛሬ ሴቷ ልጄ ቁርስ ይዤለት የምመጣው እኔ ነኝ ብላኝ ባዶ እጄን መጥቼ አረፈደችብኝ፡፡ እንደው እስከዛ እንዳይርበው ይቺን ይቀበሉኝ ይኾን?›› ሲሉ በፌስታል ጠቅልልው ወደያዟት ፓስቲ አሳዩን፡፡ እንደ ዕድል ኾኖ ማዕከላዊ በር ላይ ያሉት አብዛኛውን ቀን ምግብ ፈትሸው የሚያስገቡ ፌደራል ፖሊሶች ትሁትና መመሪያው በሚፈቅድላቸው ልክ ተባባሪዎች ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ትንሽ ኾነ ብለው ሊከለክሏቸው እንደማይችሉ ነግረናቸው ፌስታሏን ይዘው ወደ ውስጥ ዘለቁ፡፡
በሩ ክፍት ስለነበርና እኛም በክፍቱ በር ፊት ለፊት ስለተቀመጥን እኚህ እናት ውስጥ ገብተው ምን እንደሚሠሩ በደንብ ይታየናል፡፡ የእስር ቤቱ ግቢ አካል ወደ ኾነችው አነስተኛ ሱቅ አመሩ፡፡ እንደ ውሃ፣ለስላሳ መጠጦች፣ጁስ፣ቆሎ፣ የመሳሰሉና ሌሎች ጥቃቅን ለእስረኛ አስፈላጊ የኾኑ ነገሮችን የሚሸጥባት ሱቅ ናት፡፡ እንደዚህ ያሉ ነገሮችን ከዚች ሱቅ ውጪ ከውጭ ይዞ መግባት አይቻልም፡፡ እናም እኚህ እናት የያዟት ቁርስ ስላነሰችባቸው ነው መሰል ከሱቋ ዕቃ ገዛዝተው ፌስታሉ ውስጥ ሲጨምሩ ተመለከትኳቸው፡፡ ተመላሽ ዕቃ እንዲመጣላቸው ነግረው እኛ ወደ ተቀመጥንበት መጡ፡፡ዐይናቸውን ግን ልጃቸው ትመጣበታለች ባሉት መንገድ ላይ ሰክተው አስቀሩት፡፡ ሐሳባቸውን ወደኛ መለስ እያደረጉም ስለልጃቸው መልካምነትና ከእርሳቸው ጋር ስለነበረው ቅርበት እያስታወሱ ያጫውቱናል፡፡ ‹‹ሦስት ልጆች አሉኝ፡፡ አንዷ አግብታለች፡፡ አንዱ የራሱን ሥራ እየሠራ ነው፡፡ አሁን የታሰረብኝ የመጨረሻው ነው›› አሉን፡፡ ልጃቸው ከገባበት እንዲወጣ ፈጣሪያቸውን እየተማጸኑ፡፡
‹‹ልጄን አንጀቴን አስሬ ነው ያሳደኩት፤ጓደኛዬ ነው፣ልጄ ነው፣ወንድሜ ነው፣አጫዋቼ ነው፡፡ ሁሉ ነገሬ ነው እንደውም ሌሎቹ ለእርሱ ታዳያለሽ ይሉኛል፡፡›› አሉን፡፡ ልጃቸው ተጠርጥሮ ከታሰረበት ጉዳይ ጋር ምን ግንኙነት እንዳለው ለማወቅ ተስኗቸዋል፡፡ልጃቸው በዕድሜ ትንሽ መኾኑን ደጋግመው እየነገሩን፡፡‹‹እርግጠኛ ነኝ ምንም እንዳላዳረገ ሲያውቁ ይለቁታል›› ብለው ተስፋን ሰነቁ፡፡ እኚህ እናት 500 ብር የሚከፈላቸው ጡረተኛ ናቸው፡፡ ከሦስት ዓመት በፊት ከልጆቻቸው አባት ጋር ቢለያዩም እርሳቸው እንደነገሩን ለልጃቸው ሲሉ ያንኑ የቀበሌ ቤት ለሁለት ተካፍለው ምግብ እያዘጋጁ ልጃቸውን ይመግባሉ፡፡
‹‹ልጄ መንግሥት ቤት ነበር የሚሠራው፡፡ እኔ ከምሠራበት መሥሪያ ቤት ጋር የጡረታ ክርክር ላይ ስለነበርኩ ሥራ አልነበረኝም፡፡ በዛን ሰኣት ሲደግፈኝ ቆየና ልክ የጡረታ መብቴ ሲከበር ‘እስካሁን ላንቺ ብዬ ነበር ሥራ ላይ ቆየኹት መልቀቅ አለብኝ’ ብሎ ሥራውን ትቶ ትምሕርት ጀመረ፡፡››ሲሉ ልጃቸው የነበረበትን ኹኔታ ነገሩን፡፡‹‹እኔ ለልጄ ብዬ ነበር በጣም የተጎዳኹት፡፡››አሉን እዝን ብለው፡፡
በትዳራቸው ደስተኛ እንዳልነበሩ ከንግግራቸው ያስታውቃል፡፡ ከፍቺውም በኋላ አብረው በአንድ ግቢ መኖራቸው እንዳልተመቻቸው ከስሜታቸው መረዳት ይቻላል፡፡ ‹‹ልጄ የሚያድረው ከአባቱ ጋር ቢኾንም እንዳይራብብኝ ስለምፈራ የሚመገበው ግን ከእኔ ጋር ነበር፤ጡረታዬ ትንሽ ብትኾንም ቁጭ አልልም በተቻለኝ አቅም አየተሯሯጥኩ እሠራለሁ፡፡ ከመርካቶ ልብስ እያመጣሁና የምግብ ቂቤ ከክፍልሃገር እያስመጣሁ እሠራበት ለነበረው መሥሪያ ቤት ሠራተኞች እሸጣለሁ፡፡ ብቻ ፈጣሪ ይመስገን የከፋ ችግር አላጋጠመኝም››ሲሉ ፈጣሪያቸውን እያመሰገኑ ኑሮአቸውን ተረኩልን፡፡
ለእስረኛ በየቀኑ ስንቅ ማመላለስ በተለይ እንዲህ እንደሳቸው ቋሚና የረባ ገቢ ለሌለው ሰው እጅግ ከባድ ነገር ነው፡፡ እርሳቸው ግን ስለ ክብደቱ መስማትም ማውራትም አልፈልጉም ፤‹‹ እርሱ ይፈታልኝ እንጂ እኔ ስንቅ ማመላለስ አይከብደኝም፡፡ አንጀቴን አስሬ የቻልኩትን ሁሉ አደርጋለሁ፡፡ በፊት እንደምሯሯጠው እየተሯሯጥኩ ሠርቼ ስንቁን አመላልሳለሁ›› አሉን፡፡ ወኔያቸው ከዕድሜያቸው በእጅጉ የገዘፈ ነው፡፡ ገና ካሁኑ አንጀታቸውን ማሠራቸው ያስታውቃሉ፡፡ እናት መኾናቸው ችግራቸውን አስችሎ ጥርስ አስነክሷቸዋል፡፡ አንጀታቸውን አስረው ጥርሳቸውን ነክሰው ስንቅ የሚያመላልሱ እናት እርሳቸው ብቻ አልነበሩም፡፡ እንዲህ ያሉ እናቶች ትናንት ነበሩ፡፡ ዛሬም አሉ ምናልባትም ነገ ይኖራሉ፡፡
ዛሬ የእናቶች ቀን ነውና የልጆቻቸው እስር አንጀታቸውን ላሳሰራቸው እናቶች ‹‹መልካም የእናቶች ቀን፤ስንቅ አቃባይ አያሳጣችሁ›› እላለሁ፡፡


source -ጽዮን ግርማ

Saturday, May 10, 2014

ዳጉ ኢትዮጵያ

ዳጉ ኢትዮጵያ
አንድ የማህበራዊ ድረ-ገጽ ወዳጄ “በአበበ ገላው የሰሞኑ ድርጊት ምን አስደሰተህ?” ሲል ግራ በመጋባት ጠየቀኝ፡፡ የወዳጄ ጥያቄ የአበበ ገላው በፕሬዚደንት ኦባማ ፊት የኢትዮጵያውያንን የነፃነት ጩኸት ማስተጋባት በኔ በኢትዮጵያ ምድር የምኖር ዜጋ ላይ ስለሚኖረው አንደምታ በጥልቅ እንዳስብ አደረገኝ፡፡Abebe Gellaw confronting president Obama
ዜጎች ሐሳባቸውን በነጻነት መግለጽ በማይችሉባት ሐገር፤ ይልቁንም “ለዚህ ሥርዓት ጥሩ አመለካከት የለህም፣ የወጣት ሊግ፣ የሴቶች ፎረም፣ የነዋሪዎች ፎረም ወዘተ በተሰኙ የስርዓቱ አደረጃጀቶች አልተሳተፍክም” በሚል – መገለል፤ ባስ ሲልም መዋከብና ከስራ መፈናቀል በሚደርስበት ሐገር የማስበውን የሚተነፍስልኝ፣ አንደበት የሚሆንልኝ ሳገኝ ብደሰት፣ ባሞግሰው – ጀግና ብለው ምን ይገርማል? የህዝቡን ይሁንታ አግኝቼ ተመርጫለሁ፣ ኮንትራት ተሰጥቶኛል ወዘተ የሚል ማመካኛ እየደረደረ በምከፍለው ግብር የሚተዳደሩ የህዝብ ንብረት የሆኑ ሚዲያዎችን ወደራሱ የግል ንብረትነት አዛውሮ ጠዋት ማታ ሳልጠግብ – ጠግበሃል፣ በሥራ አጥነት እየተንከራተትኩ – ሥራ በሽ በሽ አድርጌልሃለሁ፣ የኑሮ ውድነቱ አጉብጦኝ – ኑሮህ ተሻሽሏል እያለ የራሱን ሹማምንት ምቾት የኔ እንደሆነ አድርጎ ለኔው የሚለፍፍ ስርዓት ባለበት ሐገር የነጻነት ጥማቴን የሚናገርልኝን አበበን ባወድሰው የሚያስገርመው ምኑ ነው?
በአምቦ፣ ሐሮማያ፣ አፋር፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ተምቤን፣ ጎንደር ወዘተ በወንድም እሕቶቼ፣ በእናት አባቶቼ ላይ የሚደርሰውን አፈና፣ ግርፋት፣ ከመኖሪያ ማፈናቀል፣ ግድያ፣ አላግባብ ከስራ ማባረር ወዘተ ሳወግዝ “የ… ከተማ ነዋሪዎች መንግስት የወሰደውን እርምጃ አደነቁ… ከግድያው የተረፉትም አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድባቸው ጠየቁ” እየተባለ በስርአቱ የፕሮፖጋንዳ አንደበቶች ጩኸቴን ስቀማ – ያልኩት ቀርቶ ለመንግስት ጆሮ የሚጥመው በኔ ስም ሲነገር – አበበ ትክክለኛውን ጩኸቴን ሲጮህልኝ እልል ብል፣ ትክክለኛ ብሶቴን ለአደባባይ ሲያበቃልኝ አበጀህ ብለው ተሳሳትክ የሚለኝ ማነው?
በሐገር ውስጥ በመሆን ስርዓቱ ያሰፈነውን የፍርሐት ቆፈን ወግድ ብለው በብዕራቸው ብሶቴን የተነፈሱልኝን፣ ጩኸቴን የጮሁልኝን ተቃዋሚዎች፣ በጋዜጠኝነት ሙያቸው አገዛዙ ያመጣብኝን የመረጃ ረሐብ ሊያስታግሱልኝ የሞከሩ ጋዜጠኞችንና ጦማሪያንን ሰብስቦ በፈጠራ ክስ በእስር ሲያጉራቸው አሰፈንኩት ብሎ ያሰበውን የህዝብ ድምጽ እርጭታ በነጎድጓዳማ ድምፁ የሰበረልኝን – ስርዓቱ ለሚዘጋው እያንዳንዱ በር በአንጻሩ በትግል የሚከፈት ሌላ በር እንደሚኖር በተግባር ያረጋገጠልኝን አበበን አበጀህ የኔ አንደበት ብለው ወዴት ላይ ነው ጥፋቴ?
“የዋህ ነህ – የአበበ ገላው ድምጹን ማሰማት ስርዓቱን አያፈርሰውም፣ ኦባማ በስርዓቱ ላይ ማዕቀብ እንዲጥል፣ በአደባባይ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን በደል እንዲያወግዝ አያደርገውም” ይሉኛል፡፡ እኔስ እሱን መች ጠበቅኩና? ለተበዳይ በደሉ መሰማቱ በራሱ የድሉ መጀመሪያ መሆኑን አታውቁም? ለታፈነ ሰው ጩኸቱ ለአደባባይ መብቃቱ፣ በደሉ ለጆሮ መድረሱ በራሱ ስኬት ነው፡፡ እንጂማ ጀርባዬ ላይ ሆኖ የሚያጎብጠኝን፣ እንደ እንስሳ ስለ ሆዴ እንጂ ስለ ነጻነቴ እንዳልጠይቅ የሚያስፈራራኝን፣ ስራ፣ የመኖሪያ ቤት ወዘተ በጥረቴ ሳይሆን ለስርዓቱ ባጎበደድኩት መጠን የማገኘው ድርጎ ያደረገብኝን ስርዓት ወግድልኝ ብሎ የማሽቀንጠሩ ኃላፊነት የኦባማ ሳይሆን የኔ መሆኑን መቼ አጣሁት? ገዢዎቼ የወንበር ስስት፣ የስልጣን ስጋት ስላለባቸው የአቤን ድርጊት ከወንበራቸው ከመነቅነቅ አንጻር ሊመዝኑት ይፈልጋሉ፡፡ የኔ መስፈሪያ ሌላ ነው፡፡ የማይወክለኝን ከወንበሩ የመነቅነቁ፣ ከምርጫ ኮሮጆ በመጣ የዜጎች ይሁንታ ሳይሆን ከሩስያ በመጣ የኤኬ 47 ጠመንጃ ጉልበት መንግስትነትን የያዘውን ስርአት የማንኮታኮቱ የቤት ሥራማ የኦባማ አስተዳደር ሳይሆን የኛ የኢትዮጵያውያን የመሆኑን ሐቅ መቼ ሳትኩት?
ደግሞስ እውነትን በሐይል ለስልጣን መናገር ያለውን ጉልበት መቼ አጣችሁት? ይኸው አበበ አይደል እንዴ በሐገር ውስጥ በጠመንጃና በእስር ቤት ሐይል፣ በውጪ ሐገር በብልጣ ብልጥነት ሸፋፍነው ይዘውት የነበሩትን የአምባገነንነት ማንነት በአለም አደባባይ እርቃኑን አስቀርቶ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር ለክውታ (ምናልባትም ለህልፈት)፣ የስርአቱን ቲፎዞዎችም ለከፍተኛ ብስጭት የዳረገው? ትግሉ ፈርጀ ብዙ መሆኑን አትርሱ እንጂ፡፡ የቀድሞው መሪ ድምጻችን ይከበር ብለው ወረቀት ይዘው አደባባይ የወጡ ወንድሞቻችንን ግንባር በአልሞ ተኳሾቻቸው አስነድለው መቼ ዝም አሉ? “ባንክ ሊዘርፉ ሲሉ ተገደሉ” ብለው በወጣቶቹ ወላጆች ላይ የስነ ልቦና ጦርነት አልከፈቱም? ይህን ግፍ ያዩ ብዙዎች በኢትዮጵያ ሰማይ የእውነትና የፍትሕ ፀሐይ መቼም አትወጣም ብለው ተስፋ እንዲቆርጡ አልደረጉም? ስለዚህ የአበበ ድርጊትም አፋኞቻችንን – “እውነት ታፍና መቼም አትቀርም፤ ጠመንጃም የእውነትን ወሊድ ያዘገየው ይሆናል እንጂ እስከወዲያኛው አያስቀረውም” የሚለውን ሃቅ በአእምሯቸው እንዲያቃጭል ማድረጉ በራሱ ድል አይደለም? ይልቁንም ክስተቱ የተፈፀመው የስርአቱ ጥቅመኞች ቀድሞ በአካል፣ ሞተውም በ”ራዕይ” የሚመሯቸውን ግለሰብ ልደት ለማክበር ተፍ ተፍ ሲሉበት በነበረው ወቅት መሆኑ በስርአቱ ደጋፊዎች ላይ የፈጠረውን የስነ ልቦና ጉዳት እስኪ ወደ ማህበራዊ ድረ-ገፆች ጎራ በሉና ታዘቡ!
“አበበ አንድ ግለሰብ ነው… ጩኸቱም ምንም ለውጥ አያመጣም” ይላሉ፡፡ እንዴ… የነፃነት መንፈስ እኮ ሁሌም ሲጀመር በአንድ ወይም በጥቂት ሰዎች ነው፡፡ ደግነቱ ግን ቶሎ ይዛመታል፡፡ ውቂያኖስ ሳይገታው፣ ፖለቲካዊ ድንበሮች ሳያስቆሙት፣ የመረጃ አፈና ሳያግደው ወደሺዎች ከዚያም ወደ ሚሊዮኖች ይጋባል፡፡ ምርጫ 1997ን ማስታወስ ይቻላል፡፡ ጥቂቶች የነፃነት መንፈስን ከታሰረበት ፈተው ለቀቁት፡፡ በወራት ጊዜ ውስጥ ከገጠር እስከ ከተማ – ከድሐ ጎጆ እስከ ቤተ መንግስት ተቆጣጠረው፡፡ ዛሬም በአበበ ገላው የተለኮሰው የነጻነት ችቦ የነጻነት እጦት ብርድ ሆኖ ያንዘፈዘፈንን በሙቀቱ ሲያፍታታን፤ የአምባገነንነት ትኩሳት ጭንቅላታቸው ላይ የወጣውን ገዢዎቻችንን ነበልባል ሆኖ ሲፈጃቸው መመልከታችን አይቀሬ ነው፡፡
እናም … እናም… እናም… በወንድሜ አበበ ገላው ሥራ ደስ ተሰኝቻለሁ – ተነቃቅቻለሁ – ተስፋንም ሰንቄያለሁ፡፡ ነገ ይህ የነፃነት ስሜት በአእላፋት ላይ ተጋብቶ ገዢዎቻችንን በየሔዱበት ሲያስጨንቅ፣ አንገት ሲያስደፋ፣ ሲያብረከርክና ሲያፍረከርክ አሻግሬ እያየሁ…

(dagu4ethiopia@gmail.com)

እንደ ስድስት ኪሎ አንበሳ በቅጽር ከልለን ልንጎበኘውና ልናስጎበኘው ይገብባል !

ባለፈው፣በቤተ-መንግስት መውጫ፣ በሸራተን መውረጃ መንገድ ላይ የተሰቀለ ፖስተር አየሁ፡፡‹‹ባፍሪካ የመጀመርያው የሳቅ ትምርት ቤት››ይላል፡፡የዘመኑን መንፈስ ከሚያሳዩ ተቋሞች ዋናው መሆን አለበት ብየ አሰብኩ፡፡በዘመኑ ዝም ብሎ መሳቅ ከባድ ነው፡፡እንድያውም በዘመኑ ከልቡ የሚስቅ ሰው ከተገኘ እንደ ስድስት ኪሎ አንበሳ በቅጽር ከልለን ልንጎበኘውና ልናስጎበኘው ይገብባል፡፡
በረንዳ ላይ ተቀምጠህ ምሳ ስትበላ ከወገቡ በላይ ሥጋ ከወገቡ በታች የመኪና ጎማ የለበሰ ተመጽዋች ወደ ጠረጴዛህ እግር እየተንፏቀቀ ቀርቦ ልመና ይሁን ትእዛዝ ባልለየለት ድምጽ‹‹አጉርሰኝ››ሲልህ እንዴት ትስቃለህ፡፡የቤት አከራይህ ከጓሮህ ያለውን የቀለበት መንገድ ከራሳቸው ኪስ አውጥተው ያስገነቡት ይመስል‹‹አካባቢውን እድገት ግምት ውስጥ በማስገባት ተዛሬ ጀምሮ በኪራዩ ላይ አንድ ሺህ ብር ጨምሬያለሁ›› ብለው ሲያረዱህ እንዴት ትስቃለህ፡፡ኮሌጅ እንዲበጥስ የሰደድከው ታናሽ ወንድምህ ለራዛ ዘመቻ የወጣ ይመስል፤ባውቶብስ ሂዶ በወሳንሳ ሲመለስ እንዴት ትስቃለህ፡፡የሳቅ ትምርትቤት መስራች አቶ በላቸው ገብቶታል፡፡ሳቅ እንደ ሂሳብ ወይም እንደ እደ ጥበብ ውጤቶች በልምምድና በጥናት ካልሆነ በቀር በዋዛ የሚገኝ አልሆነም፡፡ይህ ትምርትቤት ወደ ፊት በቢኤና በፒኤችዲ ማስመረቅ ሲጀምር ሰዎች እንደየደረጃቸው ይስቃሉ፡፡‹‹ያ ሰውየ ፍርርርስ ሲል አየከው? ከበላቸው ግርማ ትምርትቤት ማስተርሱን ስለ ሠራ እኮ ነው›› የምንልበት ቀን ሩቅ አይመስለኝም፡፡
የዘመኑን ፊልሞችን አይተሀል፡፡ሁሉም በልብህም በበብትህም ገብተው ሊያስቁህ የሚደክሙ ናቸው፡፡ባለፈው አንዱን ተከታታይ ‹‹ኮመዲ›› ለማየት ከባለንጀሮቼ ጋር ከቲቪው ፊት ለፊት ቁጭ አልሁ፡፡ተዋናዩ የሆነ መናኛ ነገር ሲናገር ወይም የሆነ አድካሚ ነገር ሲያደርግ ከጀርባ ተቀርጾ የተቀመጠ ሳቅ ይለቀቃል፡፡እኔ እቴ ወይ ፍንክች፡፡አጠገቤ የተቀመጡትማ በትከሻቸው ላይ ጋቢ በመዳፋቸው ላይ ካርታ የለም እንጂ ትኩስ የጎረቤት እዝን ላይ የተቀመጡ ነው የሚመስሉት፡፡የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀልዱን ብቻ ሳይሆን ሳቁንም ለኔ ተውልኝ ያለ ይመስላል፡፡ተከታታዩን ድራማ የሚያጅበውን ተከታታይ ሳቅ ከቢል ኮዝቢ ሾው ላይ ሳልሰማው አልቀረሁም፡፡አዘጋጆቹ import አድርገውት መሰለኝ፡፡ኮንቴነር ሙሉ ሳቅ ከመርከብ ተጭኖ ወደ ኢትዮጵያ ቴሌቪዝን ሲገባ ይታይህ፡፡ዘመኑ ዘመነ ትካዜ አይደል!! የሳቅ ትምርት ቤት በመክፈት ባፍሪካ የመጀመርያ የሆንነውን ያክል ‹‹የሳቅ አስመጭና አከፋፋይ ››በመክፈት የመጀመርያ ብንሆን ምን ይገርማል፡፡
ባለፈው ወደ ሾላ አቅጣጫ በግሬ ‹‹ስነካው›› የጥንቱን አጫዋች ልመንህ ታደሰን አየሁት፡፡በቀይ ሻንጣ ውስጥ ጓዙን ሸክፎ ባጠገቤ ሲሮጥ ፖሊስ የሚያባርረው የኮንትሮባንድ ሸቃይ ይመስላል፡፡ልመንህ መሆኑን ለማጣራት ዓይኔን ባይበሉባየ እሽት እሽት አድርጌ ራሱ መሆኑን ቁርጡን ሳውቅ ከንፈሬን መጠጥሁ፡፡ባንድ ወቅት የሳቅ ምንጭ የነበረው ሰውየ ዛሬ የትካዜ ምንጭ ሆኖኝ አረፈ፡፡
ሳቅ የሚባለው ነገር እንደ ክቡር ዘበኛ ብርጭቆ ወይም እንደ በርኖስ የሙዝየም እቃ ሆኖ መቅረቱ ያሳስባል፡፡ደበበ ሰይፉ ይህ ታይቶት ነው መሰል እንዲህ ገጥሞ ነበር፡፡
‹‹ይበቅል ይሆን ከዚህ ጠፍ ላይ፣ከዚህ መና ከዚህ ወና
ተስፋ ማድረግን የሚያውቅ ህልው፣ሳቅን የሚያውቅ ሰብእና
….
ይበቅል ይሆን››
(ለፌስቡክ ባለንጀሮቼ ብቻ የተጻፈ)
Bewketu syum

አስደንጋጭ አደጋ!

አስደንጋጭ አደጋ!
ከጎተራ ማሳለጫ ወደ ቄራ በጓዝ ላይ የነበረ ነዳጅ የጫነ የፈሳሽ ማመላለሻ መኪና ከነተሳቢውና ተሳፋሪ ጭኖ ከቄራ በኩል ይጓዝ የነበረ ሚኒባስ ታክሲ ሞሐ ለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ(ፔፕሲ) ፊት ለፊት ራሳቸውን ከመጋጨት ለማትረፍ ባደረጉት ጥረት ተሳቢው ታክሲው ላይ ተገልብጦ በደረሰ ከፍተነኛ የእሳት አደጋ ሰዎች ተቃጠሉ።በአሁኑ ሰዓት የተቃጠሉ አስክሬኖች እየተለቀመ ነው።ተጎጂዎች ወደ ሆስፒታል እየተወሰዱ ነው።አደጋው ከደረሰ አንድ ሰዓት ሆኖታል። የዐይን እማኞች እንደተናገሩት ተሳቢው ታክሲው ላይ በወደቀበት ቅጽበት ሚኒባስ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ለማትረፍ ርብርብር የተደረገ ቢሆንም ተሳቢው ውስጥ የነበረው ነዳጅ በመፍሰሱ በድንገት ከፍተኛ እሳት ተነስቷል።በዚህን ጊዜ ሁሉም ራሱን ለማዳን መራወጥ ጀመረ።እንደምንም ከሚኒባሱ ውስጥ የወጡ ሰዎች እሳት እየነደደባቸው ራሳቸውን ለማትረፍ ሲሞክሩ ታይተዋል። አደጋውን ተከትሎም በአካባቢው ወዲያው የደረሱ መኪኖች ተጋጭተዋል። አካባቢው በከፍተኛ ጭስ ታፍኖ ነበር። (ዜና በፅዮን ግርማ) | Road accident involving Oil transporter causes massive fire at Gotera in Addis Ababa | May 10, 2014
Click Here To Watch | ለማየት እዚህ ይጫኑ፦

Friday, May 9, 2014

ጋዜጠኛ አበበ ገላው ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ በካሊፎርኒያ

ጋዜጠኛ አበበ ገላው ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ በካሊፎርኒያ ክፍለ-ግዛት ንግግር በሚያደረጉበት ጊዜ 'ነጻነት ለኢትዮጵያ' በሚል መፈክር ንግግራቸውን አቋርጧቸዋል:: ኦባማም 'ከአንተ ጋር እስማማለሁ.. ነገር ግን አሁን ንግግሬን ልጨረስ ስለሆነ በኋላ እናውራ" በለው መልሰውለታል | During a speech at a Democratic National Committee event in California, Obama was interrupted by Abebe Gellaw yelling, "Freedom for Ethiopia!" Obama attempted to continue with his prepared remarks, but soon relented, responding "I agree with you, but why don't we talk about it later because I'm just about to finish!".

.....በግንቦት ወር ውስጥ የተከሰቱ ነገሮች........

.................................በግንቦት ወር ውስጥ የተከሰቱ ነገሮች................................
1. ግንቦት 1, 1947 ዓ.ም ሀገራቸውን ከድተው ለጣሊያን በባንዳነት ሲያገለግሉ የነበሩት የአስረስ ተሰማ የልጅ ልጅ የነበረው የቀድሞው አምባ-ገነኑ፣ ከፋፋዩና ጎጠኛው መሪ ለገሰ/መለስ/ ዜናዊ የተወለደበት ቀን።
2. ግንቦት 8, 1981 ዓ.ም የሀገሪቱ ጄኔራሎች በመንግስቱ ሀይለማሪያም ላይ የመፍንቅለ መንግስት ሙከራ ያደረጉበት ቀን።
3. ግንቦት 8, 1982 ዓ.ም በመንግስቱ ኃይለማሪያም ላይ መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ያደረጉት ጄኔራሎች የተረሽኑበት ቀን።
4. ግንቦት 13, 1983 ዓ.ም አምባ-ገነኑ፣ ሰው በላውና ጨፍጫፊው መንግስቱ ኃይለማሪያም ሀገሪቱን ጥሎ ወደ ዚምባቡዌ የፈረጠጠበት ቀን።
5. ግንቦት 16, 1983 ዓ.ም ሻዕቢያ የኢትዮዽያ ሁለተኛ ትልቅ ከተማ የነበረችውን አሥመራን የተቆጣጠረበት ቀን።
6. ግንቦት 20, 1983 ዓ.ም አምባ-ገነኑ ኢህአዴግ የቀድሞውን አምባ-ገነን ደርግን የተካበት ቀን።
7. ግንቦት 4, 1990 ዓ.ም ሻዕቢያ ኢትዮጵያን የወረረበት ቀን።
8. ግንቦት 7, 1997 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በነቂስ ወጥቶ በምርጫ የራሱን መሪዎች የመረጠበት ቀን። /በኋላ ኢህአዴግ ቢያጭበርብረንም/
9. ግንቦት 7, 1997 ዓ.ም ማታ ላይ መለስ የራሱን ሕገ-መንግስት ጥሶ ከግንቦት 8, 1997 ዓ.ም ጀምሮ ምንም አይነት ከቤት ውጪ ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ መከልከሉን ያወጀበት ቀን። ከ8 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ከመለስ ሞት በኋላ በመለስ የታወጀው ሕገ-ወጥ ክልከላ እንዲሻር ማድረጉ ይታወቃል።
10. ግንቦት 8, 1997 ዓ.ም በሀገሪቱ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ የምርጫ ቆጠራው ሳይጠናቀቅና ምርጫ ቦርድም ምንም አይነት መግለጫ ከመስጠቱ በፊት ኢህአዴግ ከአዲስ አበባ በቀር በሁሉም የሀገሪቱ ክልል ምርጫውን ማሸነፉን በጉልበት ያወጀበት ቀን።
11. ግንቦት 10, 2004 ዓ.ም አበበ ገላው በአሜሪካ የመለስን ቀልብ የገፈፈበትና መለስም በአደባባይ ሲደነግጥ የታየበት ቀን። ከድንጋጤው ሳያገግም ከዚያ በፊት የነበረበት ህመም ተባብሶበት ከ2 ወር በኋላ በዚያው ሞተ። የተረሳ ካለ ጨምሩበት።

Thursday, May 8, 2014

የሃሮማያ ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት ታስርው እየተመረመሩ ነው።

የሃሮማያ ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት ታስርው እየተመረመሩ ነው።
ወርቅነህ ገበየሁ ሃሮማያ ናቸው።
በሀሮማያ ዩኒቨርስቲ ያሉ ተማሪዎች ማደርያ ፍለጋ በሀረር ከተማ እየተቅበዘበዙ ነው፡፡
ምንሊክ ሳልሳዊ ፦ መንግስት ሀላፊነት ወስዶ ሊያስተምር የተቀበላቸውን የ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እየጨፈጨፈ ነው። 300 ተማሪዎች ስላሴ ቤተክርስትያን የተጠለሉ ሲሆን በብአዴን ካድሬዎች ቤተክርስትያኑን ለቀዉ ወደዶርም እንዲገቡ ቢነገራቸውም ተማሪዎች ግን ወደ ጊቢ ገብተን እንደገና ላለመደብደባችን ምን ዋስትና አለን በማለት ላይ ናቸው፡፡
በተጨማሪም የዩኒቨርስቲው አስተዳደር ለቤተክርስቲያኒቱ ተማሪዎችን ከግቢዋ እንድታሶጣ ደብባቤ እንደጻፈ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በተጨማሪም በትላንትናው እለት ትራንስፖርት ሚኒስተሩ አቶ ወርቅነህ ገበየው ሓሮማያ ዋናው ጊቢ የመጡ ሲሆን ተማሪው ትምህርት እንዲጅምር እያግባቡ ቢሆንመ በግቢው ውስጥ ሲማሩ ከነበሩት 12500 ተማሪዎች ውስጥ በ አሁን ሰአት ያሉት 3000 ተማሪዎች መሆናቸው የታወቀ ሲሆን ብዛታቸውም የተገኘው የተማሪዎች መመገቢያ እየመጡ የሚመገቡት እነዚህ ብቻ በመሆናቸው እንደሆነ ታውቃል፡፡
በዛሬው እለት ግን ቁርስ ለመመገብ የመጡት ተማሪዎች 1900 ብቻ ናቸው፡፡ ይህ በእንዲሀ እንዳለ ዩኒቨርስቲው ውስት የመንግስተ ሹመኞች ተደጋጋሚ ስብሰባ ያደረጉ ሲሆን ከምክትል ፕሬዜዳንት ፕ/ር ጨመዳ ፊንሳ በቀር ዋናው ፕሬዜዳንት ሰሞኑን እንዳልታዩ ለማወቅ ተችላል፡፡ አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ዋናው ፕሬዜዳንት ታስሮ እየተመረመረ ነው፡፡ ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

ያልተጣራ ክስ ፦ "ኬንያ እና ስዊዲን ሄደው የሽብርተኝነት የሃገር መበጥበጥ እና ተያያዥ ጉዳዮች ኮርስ ወስደዋል"

ያልተጣራ ክስ ፦ "ኬንያ እና ስዊዲን ሄደው የሽብርተኝነት የሃገር መበጥበጥ እና ተያያዥ ጉዳዮች ኮርስ ወስደዋል" ... ወይ ወያኔ ፈጠራ አያጣም እኮ .. እነዚህ ሃገራት የሽብር ኮርስ ይሰጡ ጀመር እንዴ..፡ ? ከኢርትራ ነው ከወያኔ ፕሮፖዛሉን የገዙት? WE ARE ALL ZONE 9!!! የዞን 9 አባላት የፍርድ ቤት ውሎ :
ሦስቱ የዞን 9 አባላትና ሶስቱ ሌሎች ጋዜጠኞች ዛሬ ሚያዝያ 29 2004 አም ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ የዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ በዝግ ችሎት የቀረቡ ሲሆን ፓሊስ ለምርመራ 10 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል፡፡ በዚህም የተሰጠው ምክንያት
1. ተጨማሪ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ እንዳንችል ሊሸሹ ይችላሉ
2. ከውጪ ገንዘብ በማስገባት የተገዙ ቁሳቁሶችን ለመያዝ ጊዜ ያስፈልገናል
3. የሰነድ ትርጉምና የባለሞያ ድጋፍ ለምርመራው አንፈልጋለን
4. ምስክሮችን ለማዘጋት ጊዜ ያስፈልገናል
ሲሆን ጠበቃቸው ከላይ የተጠቀሱት ምክንያቶች ዋስትና ለማስከልከል በቂ አይደሉም ሲል ተከራክሮአል፡፡ ፍርድ ቤቱ አስር ተጨማሪ ቀን የጊዜ ቀጠሮ የፈቀደ ሲሆን ግንቦት 9 ቀን ተመልሰው ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፡፡ በተጨማሪም ተከሳሾች በቤተሰብና በህግ አማካሪ መጎብኘት አለመፈቀዱ አግባብ አለመሆኑን ፍርድ ቤቱ ጠቅሶ ከነገ ጀምሮ ቤተሰብ እና የህግ ባለሞያ እነዲያያቸው እንዲፈቀድ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡ ይህ በእነደህ እንዳለ የመጀመሪያ የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው ቀን የተጠረጠሩበት የተባለው ወንጀል ላይ ቀላል የማይባል ለውጥ የተደረገ ሲሆን የመጀመሪያው ክስ ላይ የነበረው |” ራሱን የሰብአዊ መብት ድርጅት እያለ ከሚጠራ ድርጅት ጋር በሃሳብና በፋይናንስ መተባበር በማህበረሰብ ሚዲያ ብጥብጥ ለማነሳሳት ” የሚለው ወደ “በህቡህ በመደራጀት በሽብርተኛነት ተግባር ከተፈረጀ ድርጅት ጋር በመገናኘት ገንዘብ በመቀበልና አገር እና ህዝብን ለማሸበር ሲንቀሳቀሱ” በሚል ለውጥ እነደተደረገበት የጠበቃው ንግግር ያመላክታል
በመጀመሪያውም ሆነ ሁለተኛው ክስ ላይ የተጠቀሱትን ወንጀሎች የዞን ዘጠኝ አባላት እንዳልፈጸሙት ማንኛውም የሽብር ተግባር ከተጠረጠረ ድርጅት ጋርም ፈጽሞ ግንኘነት እነደሌላቸው ና ምንም አይነት የገንዘብ ድጋፍ ተቀብለው እነደማያውቁ እየገለጽን የተጠረጠሩበትን ወንጀል በየቀጠሮው መቀያየሩ ያለምንም ተጨባጭ ማስረጃ እንደዞን 9 በሚያደርጉት እነቅስቃሴ ብቻ መታሰራቸውንና ጉዳዩ የፓለቲካ ክስ መሆኑን እንደሚያሳይ እንደምናምን ደግመን ለመናገር እንወዳለን፡፡ የዞን 9 ነዋሪያን ዛሬ ፍርድ ቤት በመገኘት ላሳዩትን አጋርነት ምስጋናውን እያቀረበ ነገ በተመሳሳይ ሰአት በፍቃዱ ማህሌትና አቤል ስለሚቀርቡ አጋርነታችሁን ማሳየት እንድትቀጥሉ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

የዞን 9 ጦማርያን ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል

የዞን 9 ጦማርያን ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል
የዞን 9 ጦማርያንን የጊዜ ቀጠሮ ሊያይ ተሰየመው ችሎት ዛሬ ሌላ አሰቃቂ ዜና አብሮ ሰምቷል፡፡ ሁለቱ የዞን9 አባላት በፍቃዱ ሃይሉና አቤል ዋበላ በማእከላዊ መመታታቸውን እና ውስጥ እግራቸው ላይ ግርፋት እንደተፈጸመባቸው የገለጹ ሲሆን ፓሊስ ማስረጃ የላቸውም ሲል ተከራክሯል፡፡ ለክርክሩ ምላሽም ውስጥ እግራቸውን ለፍርድ ቤቱ ማሳየት እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ቶርቸር ህግ መንግስታዊ አይደለም ሲል "አስተያየቱን" ሰጥቷል፡፡ እነደትላትናው ሁሉ በተመሳሳይ ምክንያቶች የተነሳ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው ሲሆን ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ 10 ቀናትን ለምርመራ ፈቅዶአል፡፡
በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ለተከሳሾቹ ጭብጨባ እና ፉጨት ማሰማት የተከለከለ ሲሆን ተከሳሾች ሲወጠ ባሳዩት አጋርነትም ከዛሬ በሁዋላ ካጨበጨባችሁ እነዳትገቡ እናደርጋለን የሚል ማስፈራሪያም ተሰጥቷል፡፡ ወ/ ሮ ስንታየሁ የተባሉ የሬጅስትራር ሰራተኛ ጭብጨባውን እና ፉጨቱን ለዳኛ በመንገር አጋርነት እያሳዩ የነበሩትን ወጣቶች ተግባር ለማስቆም ሞክረዋል፡፡
ሙሉ ዘገባው ከዞን9 የፌስቡክ ገጽ የተገኘ ነው።

Friday, May 2, 2014

እነደሁልጊዜው ሁሉ ህገ መንግስታዊ መብቶቻችን መጠየቅ እንቀጥላለን በማሰርና በመደብደብና በመግደል የአገር ችግር አይፈታም

እነደሁልጊዜው ሁሉ ህገ መንግስታዊ መብቶቻችን መጠየቅ እንቀጥላለን በማሰርና በመደብደብና በመግደል የአገር ችግር አይፈታም
ክቡራን የዞን ዘጠኝ ነዋሪያን
ሳምንቱ በአራማጅነት ቆይታችን ከነበሩን ጊዜያት መካከል በጣም ከባድ ሆኖ አለፈ። የዞን ዘጠኝ አባላትና ወዳጅ ጋዜጠኛ ጓደኞቻችን ከታሰሩ 7 ቀናትን አሳለፋ፡፡ በሳምንቱ ውስጥ ቤተሰብና የህግ ባለሞያ ሳያገኛቸው እሁድ ቀን ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ከመስማት ውጪ አያያዛቸውንም ሆነ ያሉበትን የጤንነት ሁኔታ ለማወቅ አልተቻለም፡፡ እስካሁንም ቤተሰብም ሆነ የህግ ባለሞያ እነዲያያቸው አልተፈቀደም፡፡ ይህ በግልጽ ህገ መንግስቱን የሚጥስ የምርመራ ሂደት በማእከላዊ ሲካሄድ አዲስ አይደለም፡፡ ከዚህ በፌት የነበሩ የፓለቲካ እስረኞችም በተመሳሳይ ሁኔታ የመታየት መብታቸው ከማእከላዊ ጀምሮ ተነፍጎ አሁንም ቤተብሰብም ሆነ ወዳጅ እነዳይጎበኛቸው የተደረጉ እንዳሉ ይታወቃል ፡። ዞን 9 ከመጀመሪያ ዘመቻዎች አንስቶም ህገመንገስቱ አንዲከበረ ስንጠይቅ መቆየታችን ይታወቃል፡። ይህ መሆኑ ሳያንስ የመሰብሰብና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብታቸውን ሲጠቀሙ የነበሩ (ሶስተኛው የዞን ዘጠኝ ዘመቻ) የኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች እስር የአካል ጉዳትና ሞት እየደረሰባቸው ይገኛል፡፡ይህ በመላው አገሪትዋ እየታየ ያለውን ተቃውሞ መንግስት ምላሽ እየሰጠ ያለበት መንገድ አሳሳቢ አስፈሪና አሳፋሪ ከመሆኑም በላይ ሳምንቱንም በሰብአዊ መብቶች ረገድ በጣም የከፋ ያደርገዋል፡፡
መንግስት የዞንዘጠኝ አባላትንና ጋዜጠኞቸን ሰርተዋል ብሎ ያቀረበው ወንጀል በማህበረሰብ ሚዲያ በመጠቀም ህዝብን ለብጥብጥ ማነሳሳት ነው ሲል የመንግስት ቃል አቀባይ በበኩላቸው በጻፉት ሳይሆን በወንጀል በመሰማራታቸው ነው የታሰሩት ብለዋል፡፡ ወንጀሉ ፓሊስ እንዳቀረበው ደግሞ በማህበረሰብ ሚዲያ ብጥብጥን የማንሳት ተግባር ከአገር ውጨ ከሚገኝ ራሱን ከሰብአዊ መብት ብሎ ከሚጠራ ተቋም ጋር ተባብረው ብጥብጥ ማስነሳት ነው ብሎታል ፡፡ ክሱ በአጭሩ ሁለት ነገሮችን ይይዛል፡፡ አንደኛው በማህበረሰብ ሚዲያ ብጥብጥ ማስነሳት ሲሆን ሁለተኛው በሃሳብና በገንዘብ ከውጪ ድርጅቶች ጋር መተባበር ነው ፡፡
ማህበረሰብ ሚዲያ ብጥብጥ?
በማህበረሰብ ሚዲያ ብጥብጥ ማንሳት የሚል ክስ ለማቅረብ በማህበረሰብ ሚዲያ ብጥብጥ የሚያስበሱ መልእክቶቸን ማስተላለፍ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ረገድ ማንኛውም የዞን 9 ነዋሪያን እነደሚመሰክሩት ህገ መንግስታዊ መብቶች እነዲከበሩ ከመጠየቅና መንግስትን የሚተቹ ጽሁፎችን ከማቅረብ ባለፈ አንድም የዞኑ ስራ ለብጥብጥ እና ለሁከት ምክንያት ለመሆን የሚበቃም አይደለም፡፡ ይህንነ ለመረዳት የዞኑን ዘመቻዋች እና ጽሁፎች ማየት ብቻውን የክሱን አስቂኝነት ለማስረዳት ይበቃል፡፡ እስከዛሬ በጻፍናቸው የመንገስት ትችቶች ካልሆነ በስተቀር ባነሳሳናቸው ብጥብጦች አንታወቅም ፡፡ ለዚያም ነው በጽሁፋቸው አይደለም የታሰሩት የሚለውን የመንግሰት ማስተባበያ አስቂኝ የሚያደርገው ፡። በጽሁፍ ካልሆነ በምንድነው የዞን 9 አባላትን እንድ ላይ እንደቡድነ ሰብስቦ መክሰስ የሚቻለው??
ከውጨ ድርጅት ጋር መተባበር
ዞን 9 ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ ላለፉት ሁለት አመታት በነበረው ቆይታ የተለያዩ አጋርነቶችነ ከተለያዩ አካላት ጋር ፈጥሮአል፡። በዚህም በተለያየ ጊዜ እነደግለሰብም አንደቡድን ተወካይ በመሆን አባላቱ አገሪትዋ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ መብጥ ጥሰት አያያዝ አስመልክቶ ለተለያዩ ቦታዎች ንግግር አድርገዋል፡፡ ኢንተርኔት ለነጻነትና ለዴሞክራሲ የሚያደርጋቸውን አስተዋእጾም አስመልክቶ በቡድንም በነጠላም በተለያዩ ቦታቸዎች ላይ በመገኘት ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡ ይህ መንግስት ሲፈልግ የሚፈቅድላቸው ሲፈልግ ወንጀል የሚያስመስለው ተግባር ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጲያዊ ህገ መንግስታዊ መብት ነው፡፡ ዜጎች በመጓዛቸው ስራቸውን እና ልምዳቸውን በማካፈላቸው እነዲሁም ራሳቸውን ብቁ በማድረግ የሚሰሩትን የሰብአዊ መብት እነቅስቃሴ ለሌሎች መናገራቸውን ወንጀል ለማስመሰል የሚደረገውን ጥረት አሁንም ቢሆን እንደዞን 9 አጥብቀን እናወግዛለን፡፡ ከዚህ በፌትም እነደተናገርነው በህግ እስካልተከለከለ ድረስ ህጋዊ እንቅስቃሴዎቸን መንግስት ስላልወደዳቸውና ህገ ወጥ ስላስመሰላቸው የምናቆምበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ሁሉም የዞን ዘጠኝ አባላትና ወዳጆች በፓርላማ በህገ ወጥነት ከተፈረጁ ተቋማት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት አልነበራቸውም የላቸውምም፡። ለዞን ዘጠኝ ስራም ምንም አይነት የፋይናንስ ድጋፍ አግኝተን አናውቅም፡፡ (በመሰረቱ የፋይናንስ ድጋፍ የማያስፈልገው የበጎ ፍቃደኝነት ስራ ነው የምንሰራው ) ከዚያ ውጪ ግን በፓርላማ ህገ ወጥ እስካልተባሉ ወይም ከልካይ ህግ እስካልመጣ ድረስ ከተለያዩ በተባበሩት መንግስታት እውቅና ካላቸው የመብት ተሟጋች ተቋማት ጋር ያለንን ግንኙነት ወንጀል ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት አንቀበለውም፡።
አንዳንድ አስቂኝ የመንግስት ወዳጆች በህቡህ ተደራጅተው የሚል ክስም ሲለጥፉብን ሰምተናል፡፡ ህቡህ ማለት ምን ማለት እነደሆነ ትርጉሙን እንዲያጣሩ ከመጠየቅ ባለፈ ምንም የምንጨምረው ነገር የለንም ፡፡ ባለፉት ሁላት አመታት ቆይታችን ፎቶአችን የሚታይ ሙሉ ህጋዊ ስማችን የሚታወቅ አገር ውስጥ የምንኖር ኢንተርኔት ላይ የተናገርነውን በግንባር የምንደግም ህጋዊ ዜጎች ነን፡። ከዞን ዘጠኝ እሴቶች መካከልም አንዱ ለተናገሩትም ሆነ ለሚያስተላልፉት መልእክት ሙሉ ሃላፌነትን መውሰድም ጭምር ነው ፡፡ በመሰረቱ ኢንተርኔት ላይ ቡድን መመስረት በየትኛውም ህግ የማይከለከል ህጋዊ ተግባር መሆኑን ለመንግስትና የመንግሰት እርምጃ ለደገፉ ለማስታወስ አንወዳለን፡፡
ባለፉት ቀናት ስንናገር እንደነበረው መንግሰት የዞን ዘጠኝ አባላትና ወዳጆችን እነዲፈቱ መጠየቁን አሁን ደግሞ በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ በመቃወም በጋራ ድምጻችንን ማሰማታችንን እንቀጥላለን፡፡ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እየተደበደቡና እየሞቱ የዞን9 አባላትን እስር ብቻ ለይተን ዘመቻ ማድረጉን ሃላፌነት የሚሰማው ሆኖ አላገኘነውም፡፡ በመሆኑም ሁለቱ ጉዳዪች ላይ አተኩረን የሚመለከተው አካል ሃላፌነቱን እነዲወጣ ግፌት ለማድረግ እንሞክራለን፡። ዞን ዘጠኝ እንቅስቃሴን በማሰር ለመገደብ ቢሞክርም ብዙ የዞኑ ነዋሪያን ጋር በመተባበር ከምርጫ ጋር የተያያዙ ስራዎችን የመስራት እቅዳችነን አጠናክረን እንቀጥልበታለን፡።
ከነገ ሚያዝያ 25 ጀምሮ የዞን 9 ጦማርያንን እና ወዳጅ ጋዜጠኞችን መፈታት እነዲሁም በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት የምን ቃወምበት መጠነ ሰፌ ዘመቻ እንጀምራለን፡፡ እስካሁን በተናጠል ላሳያችሁን ህብረት በከፍተኛ ሁኔታ እያመሰገንን በጋራ የአገራችንን “ዞን ዘጠኝተነት” በመቃወም ህብረታቸንን እናሳይ ፡።
የዘመቻውን ዝርዝር በሚቀጥሉት ፓስቶች የምናሳውቅ ይሆናል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ህግን ለማስከበር በመጣራቸው ተጨማሪ ቅጣት ተጣለባቸው

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ህግን ለማስከበር በመጣራቸው ተጨማሪ ቅጣት ተጣለባቸው
ሚያዝያ 19/2006 ዓ.ም ለተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ በቅስቀሳ ላይ የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት በ1000 (አንድ ሺህ ብር) ዋስ እንዲወጡ መወሰኑን ተከትሎ ‹‹እኛ ነጻ ነን፡፡ ገንዘብ አስይዘን እንወጣም፡፡ ስራችን ህግ ማስከበር እስከሆነ ድረስ እየታሰርንም ቢሆን ህግ እናስከብራለን፡፡ በመሆኑም ነጻ እስካልተለቀቅን ድረስ እሰሩን፡፡›› በማለታቸው ተጨማሪ ክሶችና ቅጣቶች እየተጣለባቸው ነው፡፡ በትናትናው ዕለት ሜሮን አለማየሁና ትግስት ወንዲፍራው ‹‹ግቢ በመረበሸ›› ተጨማሪ ክስ መከሰሳቸው ይታወቃል፡፡ በአሁኑ ወቅት በቤላ ፖሊስ ጣቢያ የሚገኙ 14 ያህል የሰማያዊ ፓር አመራሮችና አባላትም ተመሳሳይ ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን ባለፈው ከፍላችሁ ውጡ ከተባሉት 1000 (አንድ ሺህ ብር) በተጨማ 600 (ስድስት መቶ ብር) ጨምረው ከፍለው እንዲወጡ ተፈርዶባቸዋል፡፡
እነዚህ አመራሮችና አባላት መጀመሪያ የካ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የነበሩ ቢሆንም እስረኛውን በማሳመጽና በመረበሽ ከመከሰሳቸውም በተጨማሪ ወደ ቤላ ፖሊስ ጣቢያ ተዛውረዋል፡፡ በወቅቱ ድብደባና ማዋከብ እንደደረሰባቸው የሚናገሩት ታሳሪዎቹ ‹‹ህግን ለማስከበር የምናደርገውን ጥረት እንደ ህገ ወጥነት ተቆጥሮ ተጨማሪ ክስና በደል ቢፈጸምብንም እኛ ህግ ማስከበራችንን እንቅጥላለን›› ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ በጉለሌ ፖሊስ ጣቢያ የሚገኙትና ዛሬ ስምንት ሰዓት ላይ ፍርድ ቤት የቀረቡት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት እያንዳንዳቸው 5500 ብር አስይዘው እንዲወጡ ተፈርዶባቸዋል፡፡ ታሳሪዎቹ ይህንን ውሳኔ በመቃወም ‹‹ነጻ ካልተለቀቅን አንወጣም!›› ያሉ ሲሆን ከዳኛው የተሰጣቸው መልስ እንዳሳዘናቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ዳኛውና አቃቤ ህጉ ተመካክለው ነው የገቡት፡፡ በእያንዳንዳችን 5500 ብር እንድንከፍል ሲፈርዱ፤ ‹እኛ ተማሪዎችና የመንግስት ሰራተኞች ነን ከየትም አምጥተን መክፈል አንችልም!› አልናቸው፡፡ እነሱ ልክ አንድ ሰው እቃ ሲገዛ እንደሚከራከረው ‹በቃ! 2000 ብር ይሁንላችሁ› አሉን፡፡›› ያሉት ታሳሪዎቹ በህግ ሳይሆን በዘፈቀደ እየተሰራ መሆኑ አሳዝኗቸዋል፡፡ በሌላ በኩል ‹‹ህገ ወጥ ቢሆንም በሌላ አካባቢ የታሰሩት የእኛ ጓደኞች 1000 ብር ነው እንዲከፍሉ የተወሰነባቸው፡፡ የእኛውን ለምንድን ነው 5500 ያደረጋችሁት?›› ብለው ሲጠይቁ ዳኛው ‹‹ቅጣቱ ከጣቢያ ጣቢያ ይለያያል፡፡›› የሚል አስገራሚ መልስ እንደሰጧቸው ገልጸውልናል፡፡

Arrests of Ethiopian journalists and bloggers are part of what critics say is a 'shocking' crackdown.

Arrests of Ethiopian journalists and bloggers are part of what critics say is a 'shocking' crackdown.
-------
Addis Ababa, Ethiopia - The arrest of six bloggers and three journalists by Ethiopia's government last week, has led to widespread outcry in the Horn of Africa nation - even among those generally supportive of the ruling party's policies.
The detainees were unusually brought to court on Sunday, April 27 in the capital Addis Ababa where judges granted investigators more time to make their case. Authorities suspect the nine of working with foreign advocacy groups to try to create unrest using social media, according to local media reports. The next court hearings are May 7 and 8, when formal charges may be brought.
Ethiopia's government, a staunch Western ally in a poor and violent region, has a track record of jailing journalists and political activists, often using a 2009 anti-terrorism law. While officials say no one has ever been imprisoned for expressing their opinion, rights groups accuse authorities of using the broad terms of the law to crush legitimate dissent.
Friends and readers portray the Zone 9 bloggers as young and principled activists pressuring Ethiopia's government to respect the country's liberal 1995 constitution.
"Most of the time they're engaged in advocating freedom of expression and what they call Dreaming of a Better Ethiopia," says Merkeb Negash, a politics lecturer from Jimma University in Ethiopia's southwest. The group had recently started blogging again after a 7-month break and complaints of surveillance and harassment by security forces.
Merkeb believes Ethiopia's state-centric development model, which critics accuse of being heavy-handed with dissidents, has delivered security, infrastructure and economic growth to a previously destitute, strife-torn country. However, these latest arrests are another indication that the victorious rebel group turned ruling coalition, the Ethiopian Peoples' Revolutionary Democratic Front (EPRDF), doesn't respect constitutional guarantees for freedom of expression, he said.
'Shocking' changes
The EPRDF came to power when it overthrew a military regime in 1991 and has governed ever since as a coalition of four ethnic parties. Its only serious challenge came in the 2005 elections, but it subsequently reasserted extensive control.
"Even people like me who were optimistic about the emergence of civilised debate and vibrant media and activism have been shocked by these detentions," Merkeb said.
Mikias Sebsibe, a journalist who works for an EPRDF-affiliated media outlet, makes a similar point. "We need to ask the government why it keeps telling us that it upholds the right to freedom of expression but contradicts itself with its actions," he said.
One person with particular reason to be shocked is Tsedale Lemma, the managing editor of Addis Standard, a monthly magazine that analyses current affairs in the region. She regularly received dispatches from Tesfalem Waldyes, one of the detained journalists. Diminutive and energetic, with a wide grin and oversized backpack, Tesfalem is familiar to many in Addis Ababa's media community.
His detention is "very strange", his editor said, as he is a "meticulous and professional" freelancer. Although he mixed socially with the independent Zone 9 activists, whose writings were more critical and provocative, he wasn't a member, she explains. The other arrested journalists are Asmamaw Hailegeorgis of Addis Guday newspaper and Edom Kassaye, a freelancer.
A journalist and a friend of Tesfalem's, Tsion Girma, is a neighbour in a low-cost apartment complex. She became aware of his plight late on Friday when she got "a massive knock at my door".
"I opened and the guy screamed at me 'Tesfalem is calling for you outside.'" When Tsion asked who was carting him off to the capital's main investigation centre, known as Maekelawi, a man in plain clothes pointed at a uniformed official.
"Now you see they are policemen. That is all you need to know," he said. A government spokesman, Shimeles Kemal, told Al Jazeera on Saturday he was not aware of the arrests. Getachew Reda, an adviser to Prime Minister Hailemariam Desalegn, said on Tuesday the group was suspected of criminality, without providing further details. Some of the arrested had "a penchant for incitement of violence and unrest", Getachew said.
The plain-clothed individuals were probably from the National Intelligence and Security Services, which investigates political conspiracies. Tsedale worries that intelligence agents have too much power. "You feel that way over the weekend when you're kept in the dark and they're taken to court on Sunday. You feel this government has lost its centre of gravity," she said.
"Is it random action by the security forces? Who is in the driving seat?" Now that a judicial process is under way other officials may not be able to intervene even if they want to, she said.

Source-Obang Metho