Thursday, May 8, 2014

የዞን 9 ጦማርያን ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል

የዞን 9 ጦማርያን ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል
የዞን 9 ጦማርያንን የጊዜ ቀጠሮ ሊያይ ተሰየመው ችሎት ዛሬ ሌላ አሰቃቂ ዜና አብሮ ሰምቷል፡፡ ሁለቱ የዞን9 አባላት በፍቃዱ ሃይሉና አቤል ዋበላ በማእከላዊ መመታታቸውን እና ውስጥ እግራቸው ላይ ግርፋት እንደተፈጸመባቸው የገለጹ ሲሆን ፓሊስ ማስረጃ የላቸውም ሲል ተከራክሯል፡፡ ለክርክሩ ምላሽም ውስጥ እግራቸውን ለፍርድ ቤቱ ማሳየት እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ቶርቸር ህግ መንግስታዊ አይደለም ሲል "አስተያየቱን" ሰጥቷል፡፡ እነደትላትናው ሁሉ በተመሳሳይ ምክንያቶች የተነሳ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው ሲሆን ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ 10 ቀናትን ለምርመራ ፈቅዶአል፡፡
በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ለተከሳሾቹ ጭብጨባ እና ፉጨት ማሰማት የተከለከለ ሲሆን ተከሳሾች ሲወጠ ባሳዩት አጋርነትም ከዛሬ በሁዋላ ካጨበጨባችሁ እነዳትገቡ እናደርጋለን የሚል ማስፈራሪያም ተሰጥቷል፡፡ ወ/ ሮ ስንታየሁ የተባሉ የሬጅስትራር ሰራተኛ ጭብጨባውን እና ፉጨቱን ለዳኛ በመንገር አጋርነት እያሳዩ የነበሩትን ወጣቶች ተግባር ለማስቆም ሞክረዋል፡፡
ሙሉ ዘገባው ከዞን9 የፌስቡክ ገጽ የተገኘ ነው።

No comments:

Post a Comment