Tuesday, April 29, 2014

ኢህአዴግ የዞን9 ጦማሪዎችን “አገር በማተራመስ” ወንጀል ከሰሰ

ኢህአዴግ የዞን9 ጦማሪዎችን “አገር በማተራመስ” ወንጀል ከሰሰ
ሚያዝያ 21, 2006ዓም
ጎግል:-የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ የኢትዮጵያ ጉዞ በርካታ ጉዳዮች የሚከናወኑበት እንደሆነ ተጠቆመ። የዘወትር የጎልጉል ምንጭ አንዳሉት የኬሪ አዲስ አበባ ጉዞ አስቀድመው የተሰሩ ስራዎች ውጤት ነው። ጥቁሩ ሰው “ውሻ ምንም ሳይመለከት አይጮህም” ሲሉ አገር ቤት ያሉ ተቃዋሚዎች ራሳቸውን ብቃት ያላቸው አማራጮች መሆናቸውን እንዲያሳዩ ጠይቀዋል። ኢህአዴግ አሜሪካንንና የምዕራቡን ዓለም እንደለመደው “ከሶማሊያ ጦሬን አወጣለሁ” በማለት መደራደሪያ ከማቅረብ ውጪ ሌላ አቅም እንደሌለው ተገለጸ። ኢህአዴግ የዞን9 ጦማሪዎችና ጋዜጠኞች “አገር በማተራመስ” ወንጀል ክስ መሰረተባቸው።የድረገጽና የማህበራዊ ገጽ የኢህአዴግ ደጋፊዎችና የስርዓቱ ተጠቃሚ አባላት ባይዋጥላቸውም አሜሪካና ኢህአዴግ የነበራቸው ግንኙነት እየሻከረ መሔዱን ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በተደጋጋሚ ሲገልጽ እንደነበር ይታወሳል። ጎልጉል የዋሽንግቶን ዲፕሎማት ምንጩን በመጥቀስ እንደዘገበው አሜሪካ ኢህአዴግን “የምስራቅ አፍሪካ ስጋት” አድርጋም ፈርጃለች። የኢትዮጵያን ጉዳይ የሚከታተለውና በስቴት ዲፓርትመንት ውስጥ የተቋቋመው የቀውስ መከላከልና ዕርቅ ቢሮ ሃላፊ ከጥር ወር ወዲህ ባሉት ጥቂት ወራት ውስጥ አራት ጊዜ አዲስ አበባ ተጉዘዋል።ኢህአዴግ እየተከተለ ያለው ፍትሃዊነት የጎደለው አገዛዝ ኢትዮጵያን ወደ ቀውስ እንዳመራትና ይኸው ቀውስ እልባት ካልተበጀለት የምስራቅ አፍሪካን የሚያዳርስ እንደሚሆን በአሜሪካ በኩል አቋም መያዙ ኢህአዴግን እንዳስበረገገው ተንታኞች እየገለጹ ነው። የምስራቅ አፍሪካ “የሰላም አባት ነኝ የሚለው ኢህአዴግ በውስጣዊ የፖለቲካ ቀውስ ስለሚገኝ የመወላለቅ ችግር ሳይገጠመው በፊት አሜሪካ አስቀድማ ስራዋን መስራት መጀመሯ ከራሷ ጥቅም አንጻር ነው” ሲሉ ዲፕሎማቱ እንደቀድሞው ሁሉ ሳይሸሽጉ ተናግረዋል። የኬሪ ጉዞም የዚሁ አካል እንደሆነ አስታውዋል። “ኢህአዴግ” አሉ ዲፕሎማቱ “የቀለም አብዮት እያለ እንደሚደነፋው ሳይሆን በመጪው ምርጫ በሩን ከፍቶ ለመወዳደር ከተስማማ ብቻ የለመደው ርጥባን ይሰጠዋል የሚል ግምት አለኝ” ብለዋል።በ97 ምርጫ ወቅት እንዳደረገው በሶማሊያ ያለውን አለመረጋጋት እንደ ማስፈራሪያ በመጠቀም ጦሩን የማስወጣት ርምጃ ቢወስድስ? በሚል ለተጠየቁት “ኢህአዴግ የመጫወቻ ካርዶቹ ያለቁበት ይመስለኛል” በማለት የግሌ ያሉትን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ኢህአዴግ በምርጫ 97 ተደራደር ሲባል ጦሩን ሰብስቦ ለመውጣት በዝግጅት ላይ እንደሆነ መግለጹን የተለያዩ የውጪ አገር ሚዲያዎች መዘገባቸው አይዘነጋም።የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር ኦባንግ ሜቶ /ጥቁሩ ሰው/ “ውሻ ከጮኸ የሆነ ነገር አለ ማለት ነው” ሲሉ ለጎልጉል አስተያየት ሰጥተዋል። ኦባንግ አገር ቤት የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይህንን ጩኸት ሰምተው ህዝብን በማስቀደም ራሳቸውን አማራጭ አድርገው እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርበዋል። አማራጭ የለም የሚለውን ፍርሃቻ በመስበር ወቅቱን ለህዝብና ለአገር ጥቅም ለማዋል እንዲተጉ አሳስበዋል። የሚመሩት ድርጅት በቅርቡ በዚህ ዙሪያ የሚለው ነገር ስላለ ዝርዝር ጉዳይ ውስጥ ከመግባት ተቆጥበዋል።የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤትን በመጥቀስ የጀርመን ድምጽ እንደዘገበው ኬሪ፤ ሃይለማርያም ደሳለኝን፣ ቴድሮስ አድሃኖምንና የሚመለከታቸውን ባለስልጣናት በሰብአዊ መብት አያያዝና በዲሞክራሲ ትግበራ ዙሪያ እንደሚያነጋግሩ ማረጋገጫ መሰጠቱን ጠቁሟል። በዚሁ ዜና ላይ ቃላቸውን እንዲሰጡ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው ረዳ ኬሪ ከሌሎች የፖለቲካ ድርጅት አመራሮች ጋር ይነጋገራሉ የሚል ስጋት እንዳለባቸው የሚያሳብቅ መልስ ሰጥተዋል። ኬሪ የዞን9 ድረገጽና ማህበራዊ ድር ጦማሪዎች እስርን አስመልክቶ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው ረዳ ጆን ኬሪ ስለ ዞን9 አባላት እስር ሊያነሱ እንደሚችሉ ተጠይቀው “እንደምናከብረው መሪ ጥያቄውን ካቀረቡ አስፈላጊውን መልስ እንሰጣለን” ካሉ በኋላ “የዞን9 ጦማሪዎች በጋዜጠኛነታቸው አልታሰሩም” በማለት ከገጀራና ከስርቆት ወንጀል ጋር በማዛመድ ለማቃለል ሞክረዋል።ጌታቸው ረዳአገዛዙ ዝም ማለቱን አስመልክቶ “የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ያደረገ ሴል ቢኖር መግለጫ እናወጣለን” ሲሉ የመለሱት አቶ ጌታቸው፣ ጆን ኬሪ የእስረኞቹን ጉዳይ እንዲያነሱ ያሳሰበውን ሂውማን ራይትስ ዎችን “ልማዱ ነው” ሲሉ ዘልፈዋል።የዞን9 አባላትን ታፍኖ መወሰድና በአገር ማተራመስ ወንጀል መከሰሳቸውን የሰሙ “ኢህአዴግ ማንንም ለአገር ተቆርቋሪ ሆኖ የመወንጀል ሞራላዊ ብቃት የለውም” በማለት ነው አስተያየታቸውን የሚጀምሩት። ኢህአዴግ ከአፈጣጠሩ ጀምሮ አሁን አስከደረሰበት ደረጃ ድረስ ዜጎችን በአገር ክህደት የመፈረጅ ብቃት ከቶውንም እንደሌለው ራሱም ጭምር የሚያወቀው እውነት እንደሆነ የደረሱን አስተያየቶች ያመላክታሉ።ያለፈው እሁድ አራዳ ምድብ አንደኛ ችሎት የቀረቡት ሶስት ጋዜጠኞችና ስድስት ጦማሪዎች በሶስት የተለያዩ መዝገቦች መከሰሳቸው የጀርመን ሬዲዮ ይፋ አድርጓል። ከታሰሩ በኋላ ከቤተሰብና ከተመልካች ተሰውረው ምርመራ ሲደረግባቸው የነበሩት የዞን9 ጦማሪዎች አስመልከቶ ወ/ሮ ሚሚ ስብሃቱ የራሳቸው በሆነው የዛሚ ኤፍ ኤም 90.7 ሬዲዮ ክስ ከመመስረቱ በፊት ስለተከሰሱበት ጉዳይ የፖሊስ ምንጭ ጠቅሰው መናገራቸውን ቪኦኤ ተናግሯል።ወ/ሮ ሚሚን ጠቅሶ የዞን9 ጦማሪዎች አርቲክል 19 ከሚባለው ተቋም ጋር ግንኙነት ያላቸውና የተለያዩ አገራት ሄደው የሰለጠኑ መሆናቸውን፣ በአገሪቱ ትርምስ ለመፍጠር በሻዕቢያና በግብጽ በገንዘብ እንደሚረዱ ቪኦኤ በዘገበ ማግስት ነው ፖሊስ በተመሳሳይ የክስ መዝገብ የተጨማሪ ቀጠሮ ቀን የጠየቀባቸው። የዞን 9 ጦማሪዎች ኢህአዴግ ላይ ጠንካራ ትችት በመሰንዘር የሚታወቁ ናቸው።“አርብ ሚያዝያ 17 ቀን 2006 አመሻሹ ላይ 11፡20 ገደማ ስድስት የዞን ዘጠኝ ጦማርያን አባላት ናትናኤል ፈለቀ፣ በፍቃዱ ሀይሉ፣ አጥናፍ ብረሀነ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ ዘላለም ክብረት እና አቤል ዋበላ በበነጋው ደግሞ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስም በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ከያሉበት ተይዘዋል፡፡ታሳሪዎቹን ለመያዝ የመጡት አካላት የማሰሪያና የመፈተሻ የፍርድ ቤት ፈቃድ የያዙ መሆናቸውን መስማታቸውን በዚሁ አጭር መግለጫ ላይ ተጠቅሷል።“ዞን 9” የጦማርያን ስብስብ አባላት ሚያዚያ 15፣2006 ባወጣነው መግለጫ ላለፉት ሰባት ወራት የዞኑ አባላት ከፍተኛ የሆነ ክትትል ሲደረግባቸው እንደነበር በጠቅላላው የተጠቆመ ሲሆን ክትትሉ የተወሰኑ የቡድኑን አባላትና የቅርብ ወዳጆችን ጭምር ያካተተ ነበር፡፡ አሁን በመንግስት የተወሰደው እርምጃ የዞኑን ተመልሶ ወደ ስራ መግባት ተከትሎ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል ሆኖም የዞን 9 አባላትና ወዳጆች በምንም አይነት ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው እንዳልነበር ለማረጋገጥ እንወዳለ” በማለት በራሳቸው የፌስ ቡክ ገጽ ላይ ዜና አሰራጭተው ነበር።በተመሳሳይ ዜና ቻይናን “ቃል የገባሽውን ብር አምጪ” ብሎ የሙጥኝ የያዘው ኢህአዴግ “ቀለም ይፈራል” ሲሉም በቅርብ የሚከታተሉ እየተቹት ነው። “ሆድ በባሰው ቁጥር የቀለም አብዮት ” በማለት ቅስቀሳ የሚያዘወትረው ኢህአዴግ አሁን ያስፈራው የትኛው ቀለም እንደሆነ በይፋ ባይገልጽም የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑትን ኢንጂነር ይልቃል “ተስፋ የተጣለባቸው ወጣት መሪዎች” በሚል ተመርጠው ከሌሎች አቻዎቻቸው ጋር አሜሪካ ለስልጠናና ለልምድ ልውውጥ መጋበዛቸው፣ ወደ ስፍራው እንዳያመሩ መደረጉ፣ እንዲሁም አሁን በድፍረት የሚንቀሳቀሱና የሚያስተባብሩ መሆናቸው አንዱ የስጋት ምንጭ ሊሆን አንደሚችል ግምት አለ።“የቀለም አብዮት ሰለባዎች” በሚል ርዕስ ኢህአዴግ ዩክሬንን አስታኮ ያሰራጨው ቪዲዮ አሜሪካንን በሽብር ስራ የማሰልጠን ክህሎት ያላት፣ ሽብርተኞች አገርን አንዲያተራምሱ በመደገፍ የሚታወቁ ተቋማት ባለቤት የሆነች አገር ብሎ መፈረጁ አይዘነጋም። ኢህአዴግ ተንታኝ አድርጎ ያቀረባቸው ጎረምሶች አሜሪካንና የምዕራብ አገሮችን ሲዘልፉ የሚያሳየው ፊልም መጨረሻው “ከፊል የዩክሬን ህዝብ ራስን በራስ በመወሰን መብቱ ተጠቅሞ የቀድሞ አካሉን ሩሲያን ተቀላቀለ” በሚል መሆኑና ጉዳዩ ከአሁኑ የኢትዮጵያ ሁኔታ ጋር ተዛምዶ መቋጨቱ የኢህአዴግን በተለይም የህወሃትን ስጋት እንደሚያጎላው የሚያሳይ እንደሆነ አስተያየት እየተሰጠበት ነው። በሕገመንግሥቱ አገር እንድትበታተን በአንቀጽ 39 በግልጽ አስቀምጦ እስካሁን ኢትዮጵያን በ“ነጻ አውጪ ግምባር” ስም የሚመራውና “የነጻ አውጪ ግምባሩን” መሪ ወደ ተባበሩት መንግሥታት በመላክ ኤርትራ ከኢትዮጵያ እንድትገነጠል ዓለምን የለመነው ህወሃት/ኢህአዴግ፤ “የቀለም አብዮት ሰለባዎች” በማለት ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጭ ከሶቪየት ህብረት የተገነጠለችውና የዩክሬን አካል የነበረችው ክሬሚያ ወደ እናት አገሯ ሩሲያ መመለሷን አብሮ ማሰራጨቱ ዘጋቢ ፊልሙን ዋጋቢስ የሚያደርገው መሆኑን አለማስተዋሉ በራሱ ሌላ ዘጋቢ ፊልም የሚያሰራ ነው፡፡

Ethiopia: Arrests Upstage Kerry Visit - 9 Bloggers and Journalists Held Before US Official Arrives

Ethiopia: Arrests Upstage Kerry Visit - 9 Bloggers and Journalists Held Before US Official Arrives



Nairobi — The Ethiopian authorities should immediately release six bloggers and three journalists arrested on April 25 and 26, 2014, unless credible charges are promptly brought, Human Rights Watch said today.United States Secretary of State John Kerry, who is scheduled to visit Ethiopia beginning April 29, should urge Ethiopian officials to unconditionally release all activists and journalists who have been arbitrarily detained or convicted in unfair trials, Human Rights Watch said. The arrests also came days before Ethiopia is scheduled to have its human rights record assessed at the United Nations Human Rights Council's universal periodic review in Geneva on May 6."The nine arrests signal, once again, that anyone who criticizes the Ethiopian government will be silenced," said Leslie Lefkow, deputy Africa director at Human Rights Watch. "The timing of the arrests – just days before the US secretary of state's visit – speaks volumes about Ethiopia's disregard for free speech."On the afternoon of April 25, police in uniform and civilian clothes conducted what appeared to be a coordinated operation of near-simultaneous arrests. Six members of a group known as the "Zone9" bloggers – Befekadu Hailu, Atnaf Berahane, Natnael Feleke, Mahlet Fantahun, Zelalem Kibret, and Abel Wabela – were arrested at their offices and in the streets. Tesfalem Weldeyes, a freelance journalist, was also arrested during the operation. Edom Kassaye, a second freelance journalist, was arrested on either April 25 or 26; the circumstances of her arrest are unclear but all eight individuals were apparently taken to Maekelawi Police Station, the federal detention center in Addis Ababa, the capital.The police searched the bloggers and journalists' offices and homes, reportedly with search warrants, and confiscated private laptops and literature. On April 26, another journalist, Asmamaw Hailegeorgis of Addis Guday newspaper, was also arrested and is reportedly detained in Maekelawi.The detainees are currently being held incommunicado, Human Rights Watch said. On the morning of April 26, relatives were denied access to the detainees by Maekelawi guards, and only allowed to deposit food.Human Rights Watch released a report in October 2013 documenting serious human rights abuses, including torture and other ill-treatment, unlawful interrogation tactics, and poor detention conditions in Maekelawi against political detainees, including journalists. Detainees at Maekelawi are seldom granted access to legal counsel or their relatives during the initial investigation phase.The Zone9 bloggers have faced increasing harassment by the authorities over the last six months. Sources told Human Rights Watch that one of the bloggers and one of the journalists have been regularly approached, including at home, by alleged intelligence agents and asked about the work of the group and their alleged links to political opposition parties and human rights groups. The blogger was asked a week before their arrest of the names and personal information of all the Zone9 members. The arrests on April 25, 2014, came two days after Zone9 posted a statement on social media saying they planned to increase their activism after a period of laying low because of ongoing intimidation.A Human Rights Watch report in March described the technologies used by the Ethiopian government to conduct surveillance of perceived political opponents, activists, and journalists inside the country and among the diaspora. It highlights how the government's monopoly over all mobile and Internet services through its sole, state-owned telecom operator, Ethio Telecom, facilitates abuse of surveillance powers.Kerry is scheduled to meet with Prime Minister Hailemariam Desalegn and Foreign Minister Tedros Adhanom in Addis Ababa "to discuss efforts to advance peace and democracy in the region." Kerry should strongly urge the Ethiopian government to end arbitrary arrests, release all activists and journalists unjustly detained or convicted, and promptly amend draconian laws on freedom of association and terrorism that have frequently been used to justify arbitrary arrests and political prosecutions. The Obama administration has said very little about the need for human rights reforms in Ethiopia, Human Rights Watch said."Secretary Kerry should be clear that the Ethiopian government's crackdown on media and civil society harms ties with the US," Lefkow said. "Continued repression in Ethiopia cannot mean business as usual for Ethiopia-US relations."

Sunday, April 27, 2014

ከኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ(ኢጋመ) የተሰጠ መግለጫ

ከኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ(ኢጋመ) የተሰጠ መግለጫ
የጋዜጠኞቹና የአክቲቪስቶቹ እስር አሳሳቢ ነው፡፡
ትላንት ሚያዝያ 17 2006 አመሻሽ ላይ ዞን 9 በተሰኘ ድረ ገጽ (ብሎግ) ላይ በሳል ፖለቲካዊና ማህበራዊ ትችቶችን በማቅረብ ከሚታወቁት ፀኀፍት መሀከል 7ቱ (ማህሌት ፋንታሁን በፍቃዱ ሀይሉ ናትናኤል ፈለቀ ዘላለም ክብረት አጥናፍ ብርሀነ አቤል ዋበላ ኤዶም ካሳዬ) እና የአዲስ ነገር ባልደረባ የነበረው ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ይታወቃል፡፡
ግለሰቦቹ በተለያየ ቦታ በየስራ ገበታቸዉ ላይ እያሉ ሁሉም በተመሳሳይ ሰዓት በፀጥታ ሀይሎች ተይዘዉ በማዕከላዊ ምርመራ ማዕከል ታስረዉ የሚገኙ ሲሆን፤ የተለያዩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት እስሩ በደንብ የታሰበበት ነበር፡፡
የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ ታሳሪዎቹ ታሰሩ ከተባለበት ሰዓትና ደቂቃ ጀምሮ የሚገኙበትን አጠቃላይ ሁኔታ ለማጣራት አየሰራ ሲሆን ፤ እስካሁን በሰበሰበዉ መረጃ መሰረት ልጆቹን ለእስር የሚያበቃ ምን አይነት ማስረጃ እንደተገኘባቸው ለማወቅ አልቻለም፡፡
ሆኖም ግን ለእስር ከመዳረጋቸው በፊት ከመንግስት ሲርስባቸዉ በነበረዉ ህገወጥ ድርጊቶች ምክንያት ለረጅም ጊዜ ስራቸዉን ካቋረጡ በኋላ በቅርቡ ወደ ስራ መመለሳቸዉን ይፋ አድርገው እንደነበር ከድረገጻቸው ላይ ለመረዳት ችለናል፡፡ ይህ ጉዳይ እስሩን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎብናል፡፡
ስለሆነም የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ መንግስት ታሳሪዎቹን ለማሰር ያበቃዉ ተጨባጭ ማስረጃ ካለ ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ፤ ያ ካልሆነ ግን እስረኞቹን በአስቸኳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ እናሳስባለን፡፡
የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ባናየውም ምግብ አቀብለነዋል

ባናየውም ምግብ አቀብለነዋል


ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ተኩል አካባቢ ተስፋለምን ለመጠየቅ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ስንደርስ ምግብ ለታሠሩ ዘመዶቻቸው ለማቀበል ሰዎች ተሰልፈዋል፡፡ 

ከኛ በፊት የበፍቃዱና የአጥናፉ ቤተሰቦች የያዙትን ምግብ ለማቀበል ጠየቁ፡፡ማታ የታሠሩ እስረኞች ዝርዝር ስላልደረሰ ትንሽ ጠብቁ ተባልን፡፡

ብዙም ሳይቆይ ዝርዝር መጣና እንደየ አመጣጣችን ወደ ውስጥ ገብተን ምግባችንን አስፈተሸን፡፡ስም ዝርዝራችን ባመጣነው ዕቃ ውስጥ ገብቶ 

ግቢውን ለቀን እንድንወጣ ተደረግን፡፡ምሳም በዚህ መልኩ ገብቶለታል፡፡ ምርመራው እስኪጠናቀቅ ማየት አትችሉም ተብለናል፡፡ የዞን ዘጠኝ 

አባላት የኾኑት አጥናፍ ብርሃነ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ ዘላለም ክብረት፣ በፈቃዱ ሀይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አቤል ዋበላ እዛው መታሠራቸውን ጠያቂ 

ቤተሰቦቻቸው ዕቃ ሲያስገቡላቸው ተመልክቻለሁ፡፡ከትናንት ማታ ጀምሮ እንደ ታላቅ ወንድም የሚደረገውን ሁሉ እያደረክለት ላለኸው ታምራት 

ገብረጊዮርጊስ እናመሰግናለን፡፡


ጺወን ግርማ

በአዲስ አበባ በሰማያዊ ፓርቲ የተመራ ደማቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ።

በአዲስ አበባ በሰማያዊ ፓርቲ የተመራ ደማቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ።
ምንሊክ ሳልሳዊ ፡ በአዲስ አበባ ከተማ የተነጠቁ መብቶቻችንን እናስመልስ በሚል መሪ መፈክር ሰማያዊ ፕርቲ የጠራው ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በደምቀ ህኔታ የተካሄደ ሲሆን መነሻውን ከፓርቲው ጽ/ቢት አድርጎ በ እንግሊዝ ኢምባሲ በኩል መድረሻውን ወረዳ 8 ታቦት ማደሪያ ሜዳ ላይ ያደረገው ሰልፍ በሰላም ተጀምሮ በሰላም እንደተጠናቀቀ ታውቋል።
በሰልፉ ስነስር ስር አት ማጠናቀቂያ ንግግር ያደረጉት የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ወደስ ሰልፉ የመጡትን እና ስልፉን ያስተባበሩትን ወጣቶች እና መላውን ባለ መብት ተሳትፊ አመስግነው ......... ስርዓቱ በሙስና ተጨማልቋል፡፡ አገራችን አደጋ ላይ ወድቃለች፡፡ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ሆነን እጣ ፈንታችን እንወስን! በየትኛውም አገር አምባተገነን እንዲሁ መብት አይሰጥም! አስፈላጊውን መስዕዋትነት መክፈል አለብን ብለዋል ። ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት አያይዘውም ከ19 አመት ጀምሮ እስከ 63 አመት ያሉት አባላትና አመራሮቻችን ታስረዋል፡፡ ክርስቲያኖች፣ ሙስሎሞች ወጣቶች፣ ኢንጅነሮች፣ ሌሎቹም ታስረውብናል! ይህም የኢህአዴግ አምባገነንነት ያሳይል፡፡ ሰማያዊ ለሁሉም የህዝብ ክፍል እንደሚቆምም በዚህ ሰልፍ የታሰሩት አባላትና አመራሮቻችን ማሳያ ናቸው ነው! ክብርና ፍርሃት፣ ማጎብደድ የኢትዮጵያውያን ባህል አይደለም፡፡
ማሸነፍን ያስተማርን ህዝቦች ነን፡፡ ሙስሊም ክርስቲያኑ በጨዋነት አብሮ የሚኖርባት አገር ናት፡፡ እነሱ ግን ይከፋፍሉናል፡፡ አሁን በአዋራጅ ሁኔታ ላይ እንገኛለን! ይህን ከእነ አስፈላጊው መስዋትነት ሌት ተቀን እንሰራለን፡፡ ሲሉ ተናግረዋል ።
ሰልፉ ላይ ሲሰሙ የነበሩ መፈክሮች እና መዝሙሮች የህዝቡን ብሶት እና ሮሮ ያንጸባረቁ ሲሆን ገዥው ፓርቲ ስልጣኑን ለህዝብ ያስረክብ! የምኒልክ ልጆችነን፣ የጣይቱ ልጆች ነን! ውሃ ጠማን፣ ዘመድ ናፈቀን፣ ውሃ ጠማን፣ ጨለማ ዋጠን፣ ዜጎችን ማፈናቀል ይቁም፣ ፍትህ ናፈቀን! የተነጠቁ መብቶቻችን ይመለሱልን! ነጻነት ነጻነት! እኩልነት! ናትናኤል አሸባሪ አይደለም! አቡበክር አሸባሪ አይደለም! በቀለ አሸባሪ አይደለም!
አድዋ ድልድይ ላይ ፖሊስ ሰልፉን ለማስቆም እየጣረ ነው! እውቅናው በባልደራስ በኩል እንዲያልፍ ቢሆን በሲግናክ በኩል እንድናልፍ እየጣረ ነው፡፡ ሆም የሰልፉ አስተባባሪዎች በእውቅናው መሰረት እንደሚደረግ እየተናገሩ ነው፡፡ ሰልፈኞቹ በፖሊስ ላይ እየጮሁ ነበር ።
ደህንነቶቹ የግዳቸውን ሰልፉን አክብረዋል፡፡ ፖሊሶች መብታቸው ተመልሶላቸዋል፡፡ ወጣቶቹ ባደረጉት ግፊት የህዝ ሆነዋል! ኧረ ጎበዝ!ኧረ ጎበዝ ! ህዝቡ ድምጹን ከፍ አድርጎ እያሰማነው! ድል የህዝብ ነው! ድል የኢትዮጵያውያን ነው! እምብይ በል! እምብይ በል! ድንበራችን አንሰጥም! ህዝቡን በአደባባይ የሚሳደብ መንግስት አይመጥነንም! ርዕዮት ርዕዮት! እስክንድር! ዞን ዘጠኝ ዞን ዘጠኝ! አቡበክር አቡ በክር! ናትናኤል አሸባሪ አይደለም፣ ህገ መንግስቱን የሚንዱት ናቸው አሸባሪዎች! መብራት መብራት፣ ስልክ ስልክ! ነጻነት ነጻነት፣ አበበ አበበ! ህገ መንግስቱ ይከበር!
ሰልፍ ሥነ ስር አቱን እንደጠበቀ በሰላም መጠናቀቁ ታውቋል።

 ምንሊክ ሳልሳዊ

እኛ እና እነሱ


እኛ እና እነሱ
እኛ፦ 
በወላጅ ተመክረን፣ስናጠፋ ተገስጸን፣
ጠመም ስንል እየተወቀርን ስላደግን ታንጸን፣
የስብዕናን ታላቅነት፣
የህሊናን ክቡርነት፣
ስለተረዳን ጠንቅቀን፣
የወገን በደል መረረን፣ የገዥዎች ግፍ ተናነቀን።
እነሱ፦
በስርቆት አንቀልባ ታዝለው፣
በተዘ ረፈ ጨርቅ ተጠቅልለው፣
በስድብ አፋቸውን ፈ’ተው፣
በድንጋይ ተፈናክተው፣
አደጉና ሳይታረቁ፣
ህሊናቸው ታወረ፣የስብዕናን ክብር ናቁ።
ስለፍት ሲሞገቱ፣ስለ ነፃነት ሲጠየቁ…
ስለ ሆድ መላቅ ሊነግሩን፣የባልትና መጣፍ ገለጡ፣
እዳሪ ለሚሆን ምስር ወጥ፣ማንነታቸውን ለወጡ።
እኛ፦
የመጽሐፉ ቃል ዘ ልቆን፣
የእውነቱ አንድምታ ጠልቆን፣
“በቀና መንፈስ ጭምር እንጂ፣ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም፣
እህል ሟች ስጋን እንጂ፣ህያው ነፍስን አያወፍርም።”
እያልን ዳዊት ስንደግም፣እያልን ቁርዓን ስንቀራ፣
ስለነፃነት፣ስለፍትህ ፣አበክረን ስንጣራ….
እነሱ እነ ሆድ አምላኩ፣ተገልብጦባቸው ሥዕሉ፣
“ጆንያ በእህል ነው የሚቀም፣ምግብ ነው የሚልቅ ከሁሉ፣
ለደሀ ዲሞክራሲ፣ፍትሕ፣ነፃነት ቅንጦት ነው” እያሉ፣
በበሉበት፣በጠጡበት፣በዋጡነት ይጮኻሉ…. እያለ ይቀጥላል።(ተናግሮ አናጋሪን ይያዝላችሁ!"



source:Dereje Habtewold facebook