Sunday, April 27, 2014

ባናየውም ምግብ አቀብለነዋል

ባናየውም ምግብ አቀብለነዋል


ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ተኩል አካባቢ ተስፋለምን ለመጠየቅ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ስንደርስ ምግብ ለታሠሩ ዘመዶቻቸው ለማቀበል ሰዎች ተሰልፈዋል፡፡ 

ከኛ በፊት የበፍቃዱና የአጥናፉ ቤተሰቦች የያዙትን ምግብ ለማቀበል ጠየቁ፡፡ማታ የታሠሩ እስረኞች ዝርዝር ስላልደረሰ ትንሽ ጠብቁ ተባልን፡፡

ብዙም ሳይቆይ ዝርዝር መጣና እንደየ አመጣጣችን ወደ ውስጥ ገብተን ምግባችንን አስፈተሸን፡፡ስም ዝርዝራችን ባመጣነው ዕቃ ውስጥ ገብቶ 

ግቢውን ለቀን እንድንወጣ ተደረግን፡፡ምሳም በዚህ መልኩ ገብቶለታል፡፡ ምርመራው እስኪጠናቀቅ ማየት አትችሉም ተብለናል፡፡ የዞን ዘጠኝ 

አባላት የኾኑት አጥናፍ ብርሃነ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ ዘላለም ክብረት፣ በፈቃዱ ሀይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አቤል ዋበላ እዛው መታሠራቸውን ጠያቂ 

ቤተሰቦቻቸው ዕቃ ሲያስገቡላቸው ተመልክቻለሁ፡፡ከትናንት ማታ ጀምሮ እንደ ታላቅ ወንድም የሚደረገውን ሁሉ እያደረክለት ላለኸው ታምራት 

ገብረጊዮርጊስ እናመሰግናለን፡፡


ጺወን ግርማ

No comments:

Post a Comment