Sunday, April 27, 2014
እኛ እና እነሱ
እኛ እና እነሱ
እኛ፦
በወላጅ ተመክረን፣ስናጠፋ ተገስጸን፣
ጠመም ስንል እየተወቀርን ስላደግን ታንጸን፣
የስብዕናን ታላቅነት፣
የህሊናን ክቡርነት፣
ስለተረዳን ጠንቅቀን፣
የወገን በደል መረረን፣ የገዥዎች ግፍ ተናነቀን።
እነሱ፦
በስርቆት አንቀልባ ታዝለው፣
በተዘ ረፈ ጨርቅ ተጠቅልለው፣
በስድብ አፋቸውን ፈ’ተው፣
በድንጋይ ተፈናክተው፣
አደጉና ሳይታረቁ፣
ህሊናቸው ታወረ፣የስብዕናን ክብር ናቁ።
ስለፍት ሲሞገቱ፣ስለ ነፃነት ሲጠየቁ…
ስለ ሆድ መላቅ ሊነግሩን፣የባልትና መጣፍ ገለጡ፣
እዳሪ ለሚሆን ምስር ወጥ፣ማንነታቸውን ለወጡ።
እኛ፦
የመጽሐፉ ቃል ዘ ልቆን፣
የእውነቱ አንድምታ ጠልቆን፣
“በቀና መንፈስ ጭምር እንጂ፣ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም፣
እህል ሟች ስጋን እንጂ፣ህያው ነፍስን አያወፍርም።”
እያልን ዳዊት ስንደግም፣እያልን ቁርዓን ስንቀራ፣
ስለነፃነት፣ስለፍትህ ፣አበክረን ስንጣራ….
እነሱ እነ ሆድ አምላኩ፣ተገልብጦባቸው ሥዕሉ፣
“ጆንያ በእህል ነው የሚቀም፣ምግብ ነው የሚልቅ ከሁሉ፣
ለደሀ ዲሞክራሲ፣ፍትሕ፣ነፃነት ቅንጦት ነው” እያሉ፣
በበሉበት፣በጠጡበት፣በዋጡነት ይጮኻሉ…. እያለ ይቀጥላል።(ተናግሮ አናጋሪን ይያዝላችሁ!"
source:Dereje Habtewold facebook
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment