Sunday, April 27, 2014

በአዲስ አበባ በሰማያዊ ፓርቲ የተመራ ደማቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ።

በአዲስ አበባ በሰማያዊ ፓርቲ የተመራ ደማቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ።
ምንሊክ ሳልሳዊ ፡ በአዲስ አበባ ከተማ የተነጠቁ መብቶቻችንን እናስመልስ በሚል መሪ መፈክር ሰማያዊ ፕርቲ የጠራው ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በደምቀ ህኔታ የተካሄደ ሲሆን መነሻውን ከፓርቲው ጽ/ቢት አድርጎ በ እንግሊዝ ኢምባሲ በኩል መድረሻውን ወረዳ 8 ታቦት ማደሪያ ሜዳ ላይ ያደረገው ሰልፍ በሰላም ተጀምሮ በሰላም እንደተጠናቀቀ ታውቋል።
በሰልፉ ስነስር ስር አት ማጠናቀቂያ ንግግር ያደረጉት የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ወደስ ሰልፉ የመጡትን እና ስልፉን ያስተባበሩትን ወጣቶች እና መላውን ባለ መብት ተሳትፊ አመስግነው ......... ስርዓቱ በሙስና ተጨማልቋል፡፡ አገራችን አደጋ ላይ ወድቃለች፡፡ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ሆነን እጣ ፈንታችን እንወስን! በየትኛውም አገር አምባተገነን እንዲሁ መብት አይሰጥም! አስፈላጊውን መስዕዋትነት መክፈል አለብን ብለዋል ። ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት አያይዘውም ከ19 አመት ጀምሮ እስከ 63 አመት ያሉት አባላትና አመራሮቻችን ታስረዋል፡፡ ክርስቲያኖች፣ ሙስሎሞች ወጣቶች፣ ኢንጅነሮች፣ ሌሎቹም ታስረውብናል! ይህም የኢህአዴግ አምባገነንነት ያሳይል፡፡ ሰማያዊ ለሁሉም የህዝብ ክፍል እንደሚቆምም በዚህ ሰልፍ የታሰሩት አባላትና አመራሮቻችን ማሳያ ናቸው ነው! ክብርና ፍርሃት፣ ማጎብደድ የኢትዮጵያውያን ባህል አይደለም፡፡
ማሸነፍን ያስተማርን ህዝቦች ነን፡፡ ሙስሊም ክርስቲያኑ በጨዋነት አብሮ የሚኖርባት አገር ናት፡፡ እነሱ ግን ይከፋፍሉናል፡፡ አሁን በአዋራጅ ሁኔታ ላይ እንገኛለን! ይህን ከእነ አስፈላጊው መስዋትነት ሌት ተቀን እንሰራለን፡፡ ሲሉ ተናግረዋል ።
ሰልፉ ላይ ሲሰሙ የነበሩ መፈክሮች እና መዝሙሮች የህዝቡን ብሶት እና ሮሮ ያንጸባረቁ ሲሆን ገዥው ፓርቲ ስልጣኑን ለህዝብ ያስረክብ! የምኒልክ ልጆችነን፣ የጣይቱ ልጆች ነን! ውሃ ጠማን፣ ዘመድ ናፈቀን፣ ውሃ ጠማን፣ ጨለማ ዋጠን፣ ዜጎችን ማፈናቀል ይቁም፣ ፍትህ ናፈቀን! የተነጠቁ መብቶቻችን ይመለሱልን! ነጻነት ነጻነት! እኩልነት! ናትናኤል አሸባሪ አይደለም! አቡበክር አሸባሪ አይደለም! በቀለ አሸባሪ አይደለም!
አድዋ ድልድይ ላይ ፖሊስ ሰልፉን ለማስቆም እየጣረ ነው! እውቅናው በባልደራስ በኩል እንዲያልፍ ቢሆን በሲግናክ በኩል እንድናልፍ እየጣረ ነው፡፡ ሆም የሰልፉ አስተባባሪዎች በእውቅናው መሰረት እንደሚደረግ እየተናገሩ ነው፡፡ ሰልፈኞቹ በፖሊስ ላይ እየጮሁ ነበር ።
ደህንነቶቹ የግዳቸውን ሰልፉን አክብረዋል፡፡ ፖሊሶች መብታቸው ተመልሶላቸዋል፡፡ ወጣቶቹ ባደረጉት ግፊት የህዝ ሆነዋል! ኧረ ጎበዝ!ኧረ ጎበዝ ! ህዝቡ ድምጹን ከፍ አድርጎ እያሰማነው! ድል የህዝብ ነው! ድል የኢትዮጵያውያን ነው! እምብይ በል! እምብይ በል! ድንበራችን አንሰጥም! ህዝቡን በአደባባይ የሚሳደብ መንግስት አይመጥነንም! ርዕዮት ርዕዮት! እስክንድር! ዞን ዘጠኝ ዞን ዘጠኝ! አቡበክር አቡ በክር! ናትናኤል አሸባሪ አይደለም፣ ህገ መንግስቱን የሚንዱት ናቸው አሸባሪዎች! መብራት መብራት፣ ስልክ ስልክ! ነጻነት ነጻነት፣ አበበ አበበ! ህገ መንግስቱ ይከበር!
ሰልፍ ሥነ ስር አቱን እንደጠበቀ በሰላም መጠናቀቁ ታውቋል።

 ምንሊክ ሳልሳዊ

No comments:

Post a Comment