Saturday, May 31, 2014

Breaking News

he Swiss government granted asylum to Co-pilot Hailemedhin Abera
(EMF) — The Switzerland government has granted asylum to the Ethiopian co-pilot who seized control of the Boeing 767-300 on 17 February 2014 and flew it to Geneva, according Ethiopian attorney who closely following the case.
The Ethiopian government has pushed the Swiss government to extradite the Co-pilot Hailemedhin Aberaby labeling him as a “traitor”. The regime has also opened file to try him in absentia, sources said.
The Swiss Federal Office of Justice has confirmed that it has refused the extradition request by the Ethiopian government.
Hailemedhin Abera can freely move now and defend his case out of confinement.
The pro-democracy Ethiopian Diaspora and, attorneys, like Shakespeare Feyissa, are trying to defend the rights of the co-pilot.
The airliner’s second-in-command, Hailemedhin Abera Tegegn, 31, took control of the plane when the pilot left the cockpit to use the toilet. He then sent a coded signal announcing he had hijacked his own aircraft. The plane landed safely, and none of the 202 passengers and crew members on Flight ET-702, which originated in Addis Ababa, the Ethiopian capital, were injured.
The Co-pilot has exposed the gross human rights violations in Ethiopia at a global scale.
Diaspora Ethiopians took the streets of American and European cities in Support of the Co-pilot Hailemedhin Abera.

Thursday, May 29, 2014

Breaking News -ባልታወቁ ኃይሎች ታፈነ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 1ኛ ዓመት ተማሪ ከዩኒቨርስቲ ግቢ ባልታወቁ ኃይሎች ታፈነ
------------------------------------------------------------------------
በጎንደር ምዕራብ አርማጨሆ ነዋሪ የሆነውና በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 6ኪሎ የአካውንቲግ 1ኛ ዓመት ተማሪ የሆነው እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአንድነት መዋቅር ስራ አስፈጻሚ አባል ወጣት መልካሙ አምባቸው ሰኞ ግንቦት 18 ቀን 2006 ዓ.ም ማታ ራት ከበላ በኋላ ከዩኒቨርስቲ ግቢ ባልታወቁ ኃይሎች ታፍኖ ተወስዷል፡፡ ወጣት መልካሙ በጎንደር የሚደረገውን የድንበር ማካለል የአካባቢው ነዋሪ እንደመሆኑ መጠን የሚያውቀውን መረጃ በመስጠቱ ክትትል አንዳንዴም ማስፈራሪያ ይደረግበት እንደነበር ለፍኖተ ነፃነት ዘጋቢ ይገልጽ ነበር፣ አሁንም የተያዘው ከድንበር ማካለሉ ጋር በሰጠው መረጃ እንደሆነ በቦታው የነበሩ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ፓርቲው ወጣት መልካሙ ያለበትን ሁኔታ ለማጣራት በዩኒቨርስቲው አካባቢ ያሉ ፖሊስ ጣቢያዎች ቢሞከርም እስካሁን ድረስ ያለበት አልታወቀም፡፡

Monday, May 26, 2014

ችሎቱ- ልብ አንጠልጣዩ ቴአትር

ችሎቱ- ልብ አንጠልጣዩ ቴአትር
ደረጀ ሀብተወልድ( ኢሳት)
እንደወትሮው ሁሉ ዛሬም ከቃሊቲ ወህኒ ቤት እስከ ጊዜያዊው ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ድረስ ባለው አስፋልት ዳርና ዳር
እስካፍንጫቸው የታጠቁ ወታደሮች በተጠንቀቅ ቆመዋል።መንገድች ለእግረኞችም ሆነ ለሌሎች ተሽከርካሪዎች ዝግ ናቸው። ወደ
130 የምንጠጋ እስረኞች በአራት ኮስተር መኪናዎች ተጭነን ወይም እንደወቅቱ ቀልዳችን እንደ አቶ መለስ ታጅበን ወድ ችሎቱ
እያመራን ነው። በየመኪናዎቹ ውስጥ ያሉትን ታጣቂዎች ሳይጨምር መትረየስ የደገኑ ሶስት ፒክ አፖች ከፊት፤ ሶስት ፒክ አፖች
ከሁዋላ አጅበውናል።አቶ መለስ በአንድ ወቅት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፦‛ስልጣን እስር ቤት ነው‛ሲለ ምን ማለታቸው እንደሆነ
በደንብ ገብቶኛል። በእርግጥም በህዝብ መካከል በነፃነት መራመድ ልማይችልና ዘመኑን ሁለ በጥቁር መስተዋትና በታጣቂ ተከብቦ
ለሚኖር እንደ እርሳቸው ላለ ሰው- ስልጣን የከፋ እስር ቤት ለመሆኑ ምርምር የሚጠይቅ አይደለም። ለዚህም ይመስለኛል
በግንቦት 97 ምርጫ ውድድር ወቅት አርቲስት ደበበ እሸቱ፦‛ቅንጅት ስልጣን ሲይዝ የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን አቶ መለስም
ጭምር ነፃ ይወጣሉ፤ የፈለጉበት ሱቅ ገብተው ሲጃራቸውን ይገዛሉ፤ በህዝብ መካከል ያለ ስጋት ይራመዳሉ‛ በማለት በተደጋጋሚ
ሲናገር የነበረው።
እናም... ታጅበን ወደ ችሎቱ ስናመራ ... ወደ ቤታቸው እንዲከተቱ የተደረጉት የአካባቢው ነዋሪዎች አንገቶቻቸውን በመስኮት
በማውጣት፣ በየቤታቸው በር ሊይ በቆሙት ቅልብ ታጣቂዎች ጀርባ በማንጋጠጥና በሁለት ጣቶቻቸው የቅንጅትን አርማ
በማውለብለብ ያስለመዱንን ‚የአለንላችሁ በርቱ!‛ አሸኛኘት ዛሬም አሊጓደሉብንም። ልክ ከጧቱ 3፡00 ሲሆን የቅንጅት መሪዎችን
በጊዜያዊነት እንዲያስችል ወደተዘጋጀው ሰፊ አዳራሽ ደረስን።የስድስት ኪሎው ቋሚ ችሎት ወደዚህ እንዲቀየር የተደረገው፤ፍርድ ቤት
በቀረብን ቁጥር “መሪዎቻችን ይፈቱ!” የሚለው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የተፈሪ መኮንን ተማሪዎች አመፅ፤በስፍራው እንደ አሸን
በሚፈሱት ደረት አልሞ ተኳሾች ጥይት ሊቆም ባለመቻሉ ነው።
*** ***** ****
ችሎቱን ለመከታተል አስቀድመው በመመዝገብ መግቢያ ካርድ ያገኙ የታሳሪ ቤተሰቦችና የወቅቱ ጭፍን እርምጃ የሳታቸው
አንዳንዴ የአገር ውስጥ ጋዜጠኞች ፤እየተፈተሹ፣መታወቂያቸውን እያሳዩና በፌዴራል ፖሊሶች እየተመዘገቡ ወደ አዳራሹ ከተቱ።
ዘወትር እንደሚደረገው ሁሉ የእነሱ መግባት እንደተጠናቀቀ በከፍተኛ አጀባና ጥበቃ ከመኪናዎቹ ወርደን በሁለት መስመር በመሰለፍ
ወደ አዳራሹ ገባን። ታዲሚዎች ከመቀመጫቸው በመነሳት እጃቸውን አወዛወዙ፤እኛም እጃችንን በማወዛወዝ የአፀፋ ሰላምታ ሰጥተን ተቀመጥን።ያ ሰፊ አዳራሽ ከአፍ እስከ ገደፉ ሞላ።
ሁሉም የቴአትሩን መጀመር በጉጉት እየተጠባበቀ ነው።ጥቁር ካባ የደረቡት ሶስት ዳኞች በአዳራሹ ጓሮ በር በመግባት መድረኩ ላይ
የተዘጋጀላቸውን ስፍራ ያዙ፦ የቀኝ ዳኛ ልኡል ገብረማርያም፣ የግራ ዳኛ አህመድ ኢብራሂም ሳኒ እና የመሀል ዳኛው አዲል።
አቃብያነ -ህጎቹ በትንሹ ለ30 ደቂቃ መዘግየት ልምዳቸው ነበርና ዛሬም ወንበራቸው ክፍት ሆኖ ይታያል። እንደምንም
ተንጠባጥበው መሟላታቸውን ተከትሎ፦
“እባካችሁ አቃቤ ህጎች በሰዓቱ ተገኙልን፤ እናንተ ቀድማችሁ መገኘት ሲገባችሁ እንዴት ታረፍዳላችሁ? ሁለተኛ እንዲይደገም!”
የተለመደው የመሀል ዳኛው ማሣሰቢያ ዛሬም ተሰማ።እነሱ ግን አልበረዳቸውም፤ አልሞቃቸውም። እነዚህ አቃብያነ-
ህጎች ከዳኞች በላይ አርፋጆችና ፈራጆች ሲሆኑ፤ ተከሳሾች ሊይ አፋቸውን ያሊቅቁ ዘንድ ረዥም የስድብ አፍ የተሰጣቸው
ይመስላሉ። ተከሳሾች “የንጉስ ሌጆች” የሚሌ ቅፅል ስም የሰጡዋቸው እነዚህ አቃበያነ ህጎች፦ አብርሀም ተጠምቀ፣ ሽመልስ ከማልና
ሚካኤሌ አብርሀ ይባሊሉ።
ጊዜያዊው ችሎት ለመጀመሪያ ቀን በቀረብን ዕለት አንደኛው አቃቤ ህግ 1ኛ ተከሳሽ የሆኑትን
ኢንጅነር ሀይሉ ሻውልን “አንተ!” እያለ ሲዘልፋቸው፤ ድንገት ብድግ በማለት ቁጣ ባዘለ ቃል፦‛ በእድሜ አባትህ ይሆናሉ፤ደግሞም
ሊቀ-መንበራችን ናቸው፤ አንተ ብለህ ልትጠራቸው መብት የለህም!” በማለቱ፤ ችሎት በመድፈር እዚያው ተከሶ በፖሊሶች እየተዳፋ
እንዲወጣ የተደረገው ማን ነበር? አዎ !ያችው መከረኛ ብርቱካን ሚዴቅሳ ነበረች።
ኩት! የማይባሉትን የሹም ዶሮዎች ዯደፍራለቻ! የንጉስ ልጆችን ገላምጣለቻ!
እሷ ለመብቷ በራሷ ቆመች፤ እነሱም በአለቃቸው ተመክተው አቅራሩ።
እነሱ፣
በጌታቸው እያመኑ- ባ’ለቃቸው እየፎከሩ፣
ላታቸውን ውጪ አሳደሩ።
እኛም፣
ቀንዳቸንን አውጥተን-ቀያችን እንዳይጠቃ፣
ፀንተን ቆመናል በጥበቃ።
……. እናም ከሳሾች (አቃብያነ-ህጎች) ምስክራቸውን ያሰሙ ዘንድ መሀል ዳኛው ጠየቁ ። መጋረጃው ተገለጠ፤ የእለቱ ድራማ ተጀመረ።
የዛሬውን ድራማ ከወትሮው በተለየ መልኩ አጓጊ ያደረገው፤ የአቃቤ ህግ ምስክር ሆነው የቀረቡት ግለሰብ ከሶስት ቀናት
በፊት አቃቤ ህግ ባቀረባቸው ሌላ ምስክር አንዴ “ሞተዋል”‚ አንድ ጊዜ “ተድብድበው ሞት አፋፍ ላይ ሆነው እያጣጣሩ ነው፤
እንደውም እስካሁን ህይወታቸው ሊቆይ አይችልም፤ አብቅተዋል” የተባሉ ሰው መሆናቸው ነው።ነገሩን በተከሳሽነትነት ለሚከታተል ብቻ ሳይሆን ለታዳሚዎች ሁሉ ሁኔታው እንቆቅልሽ ነው።በተለይ፦
“አማን በ አማን፣
ተንስአ እምነ ሙታን‛ እያለ እንደኔ ሲዘምር ላደገ ሰው፤‛ ኑር ሁሴን ከሞት ተነስቶ በቅንጅት ተከሳሾች ላይ ሊመሰክር ሲመጣ ማየት -እንዴት ግራ ያጋባል መሰላችሁ?
*** ***** ****
ድራማ ክፍል 1
ከጓደኞቹ እንደተረዳሁት፤ ኑር ሁሴን በምርጫ 97 ወቅት የንቧን ቲሸርት ለብሶ፦‛ኢህአዴግን ምረጡ!‛ እያለ በሳር ቤት አካባቢ
ሲቀሰቅስ የነበረ አነስተኛ ገቢ ያለው ግለሰብ ነው።ሆኖም የአዲስ አበባ ነዋሪ፦ “ምርጫችን ቅንጅት ነው” በማለቱ ሳይከፋው
አልቀረም። ቢያንስ በሰፈሩ ኢህአዴግ እንዲያሸንፍ ለማድረግ የነደፈው እቅድ እንደማይሳካ ሲረድ፤የምርጫውን መድረስ ተከትሎ
ከኢህአዴግ እየተሰፈረችለት ያለችው ስንቅ የምትቀርበት መሰለው። የሚይዘውን የሚጨብጠውን አጣ። በዚህ ሳይበቃው
“የቅንጅት ቀንደኛ ደጋፊዎች ሆነው ኢህአዴግ እንዲይመረጥ እንቅፋት እየፈጠሩ ያሉት እነ እገሌ ናቸው” ብሎ ከሚገምታቸው
ሰዎች ጋር በተድጋጋሚ ፀብ ይፈጥር ጀመር። የኑር ሁሴን አዲስ አመል የሰፈሩ መነጋገሪያ እስከመሆን ደረሰ።በዚህ መሀከል
ባልታወቁ ሰዎች በምሽት ተደብድቦ መንገድ ሊይ መውደቁ ተሰማ። የድራማው መቼት እዚህ ላይ በደንብ ተሰራ። እናም ኑር
ሁሴንን ማን መታው?? ማን ደበደበው?እነ መላኩ? ወይስ እነ መላኩን በህግ ቁጥጥር ስር ለማስገባት ሴራ የጠነሰሱ የደህንነት
ሀይሎች??የሚል ጥያቄ አንጠጥሎ ክፍል አንድ ቀጠለ....
አቃቤ ህግ ከቅንጅት መሪዎች ጋር በዘር ማጥፋት ወንጀል የከሰሳቸውን አምስት የአካባቢው ወጣቶች በኑር ሁሴን ድብደባ
ተጠያቂ አድርጓቸዋል።መላኩና ጓደኞቹ በቅንጅት ደጋፊነት መታሰራቸው እየታወቀ ለዚህ ነገር ተጠያቂ እንዱሆኑ የተፈለገው ፤
በክሱ ሂደት ሉቀርብባቸው የሚችል ማስረጃ ስላልተገኘ ነው።ምክንያቱም ወጣቶቹ ከደጋፊነት በዘለለ በቅንጅት ውስጥ
እዚህ ግባ የሚባል ሀላፊነት አልነበራቸውም። እናም ከሶስት ቀን በፊት የቀረበው የአቃቤ ህግ ምስክር፤ ኑር ሁሴን በነመላኩ
ድብደባ መሞቱን ለፍርድ ቤቱ ተናገረ፤ ወይም መሰከረ። የአምስቱንም ወጣቶች ማንነት በጣቱ በመጠቆም ጭምር አመሊከተ።
“ደብዳቢ እና ገዳይ” የተባለተ ወጣቶችም እየተባለ ያለው ነገር ፈፅሞ ስህተት እንደሆነ ለማስረዳት ቢሞክሩም ፤ለጊዜው ሰሚ አልተገኘም።
ዳኛው የምስክሩን ቃል መዝግበው አሰናበቱት።
ድራማ ክፍል 2
ይህ በሆነ በሶስተኛው ቀን ነው ዛሬ ኑር ሁሴን እንደ ኢየሱስ ተነስቶ የተገለጠልን። የንጉስ ልጆችም(አቃብያነ ህጎች)፦ የደረሰበትን ከፍተኛ ድብደባና ሰቆቃ በራሱ አንደበት ይገልፅ ዘንድ ኑር ሁሴንን ታሞ ከሚያጣጥርበት አልጋ ላይ እንዳመጡት ተናግረው ተቀመጡ። ተከሳሾችና ታዲሚዎች ብቻ ሳንሆን ችሎቱን የሚመሩት የመሀል ዳኛ ጭምር ግር ተሰኙ። ከቀናት በፊት በአሁኑ መስካሪ(ተጠቂ) ላይ - ሌላ ሰው የሰጠውን የ”ሞቷል” ምስክር አስታወሱ መሰል‛ ምንድነው ነገሩ?‛ በሚመስል ሁኔታ አንዴ ወደ መዝገባቸው፤ አንዴ ወደ አቃቤ ህጎቹ በማየት ነገሩን እንደገና ግልፅ ያድርጉላቸው ዘንድ ጠየቁ።
ልኡላኑም “ሞቷል..” ማስባላቸው ትዝ አላቸውና ፦
“ተከሳሾቹ ሞቷል እስኪባል ድረስ ክፉኛ እንደደበደቡት እና በህይወትና በሞት መካከል ጥለውት እንደሄዱ፣ ሆኖም ‘ኮማ’ ውስጥ ገብቶ ሞቷል ከተባለ በሁዋላ መትረፉን አሻሽለው በማብራራት፤ በህይወት ከተረፈ አይቀር የደረሰበትን አደጋ በራሱ አንደበት ይናገር ዘንድ እንዳመጡት እየተወለካከፉ ምላሽ ሰጡ። አዳራሹ ውስጥ ሳቅ ተሰማ። ዳኛው ታዳሚውንና ተከሳሾችን ስለመሳቃቸው ከተቆጡና ዳግም እንዲይለምዳቸው ካስጠነቀቁ በሁዋላ ከሞት የተነሳው ኑር ሁሴን ምስክርነቱን ይቀጥል ዘንድ ፈቀደ። ድራማው እየጦዘና አጓጊነቱ ይበልጥ እየጨመረ መጣ ።”ስክሪፕቱ” አሰልችና በቀሽም ደራሲ የተፃፈ ቢሆንም፤ ዋናው ገፀ-ባህሪ አሪፍ ስለነበር ተውኔቱን ህይወት ሊሰጠው ችሎአል። “የቲአትር ድርሰት ደረቅ አፅም ነው ፤ስጋና ደም አልብሰው ህይወት የሚሰጡት ጎበዝ ተዋንያን ናቸው” ‚ይባል የለ?አዎ! ኑር ሁሴን አሪፍ(genuine) ገፀ-ባህሪ ነበር።
እነሆ የገጸ- ባህርይው በቃት የታየበት ተከታይ ክፍል፦
የመሀል ዳኛው የደረሰበትን በአጭሩ ለፍርድ ቤቱ ይናገር ዘንድ ባቀረቡለት ጥያቄ መሰረት ኑርሁሴን የተፈፀመበትን ድብደባ ሆድ
እየባሰውና እያለቀሰ ብዙዎቻችንን ባሳዘነን ሁኔታ ተናገረ።
አዎ! ኑር ሁሴን ክፉኛ ተደብድቧል። ይህን ማስተባበል ከእውነት ጋር መጣላት ይሆናል።እንደውም ከሁኔታው ለመገመት
እንደሚቻለው ጠንከር ያለ በትር ሳያርፍበት አልቀረም።ይህ በማንም ዘንድ ተቀባይነት የሌለው ፀያፍ ድርጊት እስከሆነ ድረስ፤የኑር ሁሴን ደብዳቢዎች በህግ መጠየቅ የለባቸውም የሚል የለም። አብዩ ነጥብ፦ ”ደብዲቢዎቹ እነማን ናቸው? የሚለው ወሳኝ ጥያቄ መመለሱ ላይ ነው። እናም ዳኛው ቀጠሉ፦‛የመቱዎት እነማን እንደሆኑ ያውቃሉ?‛
“እ…እ…መላኩ፣ ..እእእ...ፈቃደ፣እእእ....ቻይና....‛ እያለ የጓደኞቹን(የአምስቱን ወጣቶች) ስም እየተንቀጠቀጠ ተናገረ። “ሞቷል” የተባለው
ኑር ሁሴን በአካል ሊመሰክር ሲመጣ ፊታቸው በደስታ የበራውና ነፃ እንደሚወጡ በሙሉ መተማመን እያንሾከሾኩ ሲነጋገሩ
የነበሩት አምስቱ ወጣቶች ፤ በራሱ ከኑር ሁሴን አንደበት “ደብዲቢ” ተብለው ሲመሰከርባቸው በድንጋጤ እጃቸውን አፋቸው ላይ
አኖሩ።‛ እንዴ ምነካው?‛ የሚል ድምፅም ንዴቱን መቆጣጠር ከተሳነው ከአንድኛው ወጣት ተሰማ። አቃቤ ህጎቹ የስነ
ስርአት ጥያቄ አስከተሉ፤ ዳኛው ተናጋሪውን ወጣት ገሰፁ፤ ድራማው ቀጠለ...
አሁን ኑር ሁሴን በአካል ተነስቶ “ደበደቡኝ” ያላቸውን ጓደኞቹን በጣቱ እየጠቆመ የሚያሳይበት ክፍል ነው።”ደብዳቢ” በተባሉት
ወጣቶች መደድ የተቀመጥን ተከሳሾች በሙሉ ከመቀመጫችን እንድንነሳ ዳኛው ጠየቁ፤ሁላችንም ተነሳን።ከተነሳነው ውስጥ እነ መሊኩን፣እነ ፈቃደን፣አነ ቻይናን እየጠቆመ እንዲያሳይ ኑሩ ሁሴን ተጠየቀ። ኑር ሁሴን በስግታ እየተራመደ ወደ እኛ መጣ፤ ነገሩ ሳያስጨንቀው አልቀረም። “ደበደቡኝ” ብሎ ወደመሰከረባቸው ጓደኞቹ ሲደርስ ከውስጡ ጋር የሚሟገት ይመስል ነበር። ለመጠቆም በጣም ዘገየ። መሀል ዳኛው “ልትለያቸው አልቻልክም ማለት ነው?” እስኪጠይቁት ድረስ አጠገባቸው ደርሶ በዝምታ ቆመ። መጨነቁን የተመለከቱት ተከሳሽ ጓደኞቹም ያለ ምንም ፍርሀት፦‛ኑር ሁሴን፤ እዚህ ነን‛ ብለው እንደ ወትሮው በፍቅር ጠሩት።እሱም ተከትሎ እየሳቀ ፦‛እኚሁት‛አለ።እየጠቆማቸው እርስ በርስ ተሳሳቁ። ሁላችንም እስክንስቅ ድረስ ነገረ-ስራቸው ግራ አጋባን። ዳኛው የተለመደ ቁጣቸውን ካሰሙ በሁዋላ ኑር ሁሴን ቦታውን እንዱይዝ አዘዙ ።አስከትለውም ተከሳሾቹ መስቀለኛ
ጥያቄ ካላቸው ኑርሁሴንን መጠየቅ እንደሚችሉ አሳወቁ፤ድራማው ውበቱን እየጨመረ ወደ መጠናቀቂያው ደረሰ...
የመጨረሻው ክፍል(መስቀለኛ ጥያቄ)
ተከሳሽ ፈቃዱ፦”ኑር ሁሴን እኔ አንተን መትቼሀለሁ?”
ኑር ሁሴን፦”ፈቃደ ጓደኛዬ ፤ ገንዘብ አበዳሪዬ፤ የልብ ምስጢረኛዬ ...በፍፁም አልመታኸኝም” አዲራሹ በከፍተኛ ሳቅ ተናጋ።
የአቃቤ ህጎቹ አይን ከመቅፅበት ደም መሰለ።ዳኞቹ ግራ ተጋቡ።ፈቃዱ ፦‛ይኸው ይመዝገብልኝ፤ጥያቄየን ጨርሻለሁ”ብሎ
ተቀመጠ። ተከሳሽ መላኩ በተራው ተነሳ፦
“ኑር ሁሴን እኔ አንተን መትቼሀሇሁ?”
ኑር ሁሴን፦”መሊኩ ጓደኛዬ፤ ፀጉሬን አስተካካዬ፤ወንዴሜ ፣መካሪዬ....‛ የብዙዎቻችን ሳቅ የአዲራሹን ጣራ ሰንጥቆ ወጣ።አቃቤ
ህጎቹ በመሀከል ገብተው ለመናገር ቢፈልጉም ጊዜው የመስቀለኛ ጥያቄ ነበርና አልተፈቀደላቸውም። መላኩም፦“ይኸው ይመዝገብልኝ፤
ጥያቄየን ጨርሻለሁ” ብሎ ተቀመጠ።ቻይና እና ሌሎቹም ለጊዜው ስማቸውን የዘነጋሁዋቸው ሁለት ወጣቶች እንደዚሁ
ተመሳሳይ ጥያቄ በማቅርብ ንፅህናቸውን አረጋገጡ።በሁኔታው በጣም ግራ የተጋቡት ዳኛም፦” አቶ ኑር ሁሴን ቅዴም ማነው የደበደበዎት ተብለው ሲጠየቁ፤ እነ መላኩ፣ እነ ፈቃዱ፣እነ ቻይና....ናቸው እያሉ መስክረው ሲያበቁ፤ አሁን በመስቀለኛ ጥያቄ ላይ እንዴት አልደበደቡኝም ይላሉ? ነገሩን ግልፅ ሉያደርጉልን ይገባል! እነ መላኩ ደብድበዎታል?ወይስ አልደበድቡዎትም?”
ኑር ሁሴን፦‛አልደበደቡኝም!‛
ዳኛ፦‛ቅድም ለምን ደብድበውኛል አሉ?’
ኑር ሁሴን፦‛ጧት እቤቴ መጥተው እንደሱ በል ብለውኝ ነው‛
ዳኛ፦‛ማናቸው እንደሱ በሉ ያለዎት?‛
ኑርሁሴን፦‛መንግስት፣የመንግስት ፖሉሶች‛ ........የአቃቤ ህጉቹ የማያባራ ‚ስነ ስርአት !ስነ-ስርአት!‚ያልገደበው የማያባራ
ሳቅ................ሳቅ.......................
.የእለቱ ድራማ በዚሁ ተጠናቀቀ።
***********************************
ኑር ሁሴን ከህሊናው ጋር ታረቀ።ከአቃቤ ህጎቹ ቁጣና ማባበል የጓደኞቼ እውነት ይበልጥብኛል አለ።የአምላክ ነፍስ በብርቱ
ከምትፀየፋቸው ነገሮች ዋነኛው፦‛በወንድማማቾች መካከል ፀብ የሚዘራን‛ እንደሆነ ታላቁ መፅሀፍ ይነግረናል።በኑር ሁሴንና በነ
መላኩ መካከል ፀብ የዘሩት ወገኖች እንደ ሀገርም ያቆየነውን የመዋደድ፣ የመከባበርና አብሮ የመኖር እሴት ፤በሀይማኖትና በዘር እሳት
ለመሸርሸር እንቅልፍ አጥተው መራወጥ ከያዙ ጥቂት የማይባሉ ዓመታት አለፉ። በጓደኛሞቹ በኑር ሁሴንና -በነመላኩ ላይ
የተሞከረው ነገር ፤የትልቁ “በታትነው ‚ፖሲሲ” ነፀብራቅ ነው።ግን አልተሳካም።በወቅቱ ፈቃዱ እንደነገረኝ ከሆነ ከእስር ሲፈታ የልብ ጓደኛ ከሚያደርጋቸው ሰዎች መካከል አንዱ- ኑር ሁሴን ነው።
ድራማው በዚህ መልክ ቢጠናቀቅም ችሎቱ በሌሎች ቀናት ቀጠለ...ቀጠለ...በእነዚህና በሌሎች መሰል አስቂኝ ማስረጃዎች ፍርድ ቤቱ በእነኢንጅነር ሀይለ ፋይሌ በተከሰሱ የቅንጅት መሪዎች፣የሲቪሌና የሙያ ማብበራት መሪዎችና ጋዜጠኞች ላይ የዕድሜ ልክ እስራት ፈረደ።
ምክንያት?
ይኽ የግንቦት 20 ፍርድ ቤት ነው።

Saturday, May 24, 2014

-----------ሰበር ዜና-----------

----------------------------ሰበር ዜና-----------------------------------
ያለ በቂ ማስረጃ በሕገ ወጥ መንገድ ከአራት ሳምንት በፌት ከተያዙት ስድስቱ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን በተጨማሪ በአንድ ጦማሪ አባል መኖሪያ ቤት ላይ ፖሊስ ለ7 ሰአት የቆየ ብርበራ አካሄደ፡፡
በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 12 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ በዞን ዘጠኝ ጦማሪና መስራች ሶልያና ሽመልስ ቤተሰብ መኖሪያ ቤት ፖሊስ ብርበራ ያካሄደ ሲሆን የጸረ-ሽብር ሕጉ ይፈቅድልናል የሚል ምክንያት ሰጥተው ያለ ፍርድ ቤት የብረበራ ማዘዣ ከካሜራ ቀራጭ ጋር የተገኙት ሰባት ፖሊሶች በጦማሪዋ ክፍል እና ሌሎች አስፈላጊ ነው ባሉዋቸው ክፍሎች ሲያካሂዱ ነበረውን ብርበራ ጨርሰው ይጠቅመናል ያሉትን የዶ/ር መረራ ጉዲና የመጨረሻ መጽሀፍ እና ሌሎች ወረቀቶች ወስደው ቤት ውስጥ የነበሩትን የጦማሪዋን ወላጅ እናት አስፈርመው ከጠዋቱ 4 ሰአት አካባቢ ቤቱን ለቀው ወጥተው ነበር፡፡ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ተመልሰው በመምጣት ተጨማሪ ፍተሻ በዋናው መኖሪያ ቤት መካሄድ እንፈልጋለን ብለው ሁለተኛ ዙር ብርበራ በምግብ ማብሰያ ክፍል ውስጥ እናካሂዳከን በሚል ሰበብ ትንሹ ክፍል ውስጥ የጦማሪዋን እናት እነዲወጡ በማግለል ከማቀዝቀዛውን አንቀሳቅሰው አፍታም ሳይቆዩ 19 ገጽ የግንቦት ሰባት ፕሮግራም አግኝቻለሁ ሲል አንዱ ፈታሽ ተናግሯል፡።
የጦማሪዋን ወላጅ እናት እነዲፈርሙ ያግባቡ ቢሆንም ወላጅ እናትዋ ከክፍሏ እና ሌላም ቦታ በመፈተሽ ስታገኙ ያየሁት ወረቀት ላይ ፈርሜያለሁ ይህ ግን ምግብ ማብሰያ ክፍል ውስጥ ያልነበረ እና እዚህ ያልተገኘ ሌላ ወረቀት ነው ሲገኝም አላየሁም በማለት አልፈርምም ብለዋቸዋል፡፡ በመሆኑም ፈታሾች ተጨማሪ የሰው ሃይል ደውለው በማስጠራት ለማግባባት ቢሞክሩም ስላልተሳካላቸው ይዘዋቸው የመጡትን የራሳቸውን ሁለት ምስክሮች ብቻ አስፈርመው ባለቤትዋ ለመፈረም ፍቃደኛ አይደሉም ብለው ቤቱን ለቀው ሄደዋል፡፡ ከፓሊስ ጋር የመጡት ምስክሮች አንደኛው አድራሻቸው በብርበራ ምስክርነት ዶክመንቱ ላይ ያልተጻፈ መሆኑንም ለመረዳት ችለናል ፡፡
በብርበራው ወቅት በነበራቸው የ7 ሰአት ቆይታ የጦማሪዋን መጸሃፍት የጉዞ ትኬቶች የስልጠና ማንዋል እና የመሳሰሉትን ጥቃቅን ወረቀቶች የወሰዱ ሲሆን ማብሰያ ክፍል ከፍሪጅ ጀርባ አገኘነው ካሉት ወረቀት ግን ቤት ውስጥ ያልነበረና ፓሊሶች ራሳቸው ያመጡት በመሆኑ እናትዋ ተናግረዋል፡፡
የዞን ዘጠኝ ጦማሪ አባላት ከየትኛውም በፓርላማ በአሸባሪነት ከተፈረጀ የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆኑና ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸው እነዲሁም አነዚህ ድርጅቶች ላይ በተለያየ አጋጣሚ ትችቶቻቸውን ሲያቀርቡና ሲቃወሙ የሚታወቁ ቢሆንም ሲሆን በተያዙት አባሎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው አስገድዶ ለሃሰተኛ መረጃ እንዲፈርሙ የማድረግ ተግባር ሳያንስ ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ለማያያዝ ማስረጃን እንደተገኘ አድርጎ የማቅረቡ ተግባር መንግሰት ይታማበት የነበረውን የፓለቲካ ውንጀላን በሽብር የመቀየር ክስ በተግባር እንድናይ ያስቻለን ነው ፡።
በመሆኑም አሁንም ቢሆነ ጦማሪ ጓደኞቻችን ሃሳባቸውን በነጻነት ከመግለጻቸው ውጪ ምንም አይነት የወንጀልም ሆነ ሽብር ከተፈረጁ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት እንደሌላቸው እያስታወስን መንግስት ያሰራቸውን ጦማርያን እና ጋዜጠኞች አንዲፈታ አሁንም አንጠይቃለን፡፡

Sunday, May 18, 2014

ፖሊስ ሊመሰረት ያሰበው የሽብርተኝነት ክስ በፍርድ ቤቱ ውድቅ ተደረገ

ፖሊስ ሊመሰረት ያሰበው የሽብርተኝነት ክስ በፍርድ ቤቱ ውድቅ ተደረገ
(By Bisrat Woldemichael)
ዛሬ እሁድ ግንቦት 10 ቀን 2006 ዓ.ም. አራዳ በሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት በፍቃዱ ኃይሉ፣ አቤል ዋበላ እና ማህሌት ፋንታሁን ከረፋዱ 4፡20 ቀርበው ነበር፡፡ ይዟቸው የመጣውና እስካሁንም መደበኛ ክስ ያልመሰረተው የማዕከላዊ ፖሊስ ምርመራዬን አልጨረስኩም፣ ጉዳዩ ከሽብር ጋር ስለሚያያዝ ተጨማሪ የ 28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ ሲል ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል፡፡
ፍርድ ቤቱም ከዚህ በፉት ለ24 ቀናት አስራችሁ ያቀረባችሁት ከሽብር ጋር የተያያዘ ባለመሆኑ እና ሌላ አዲስ ሂደት ስለሌለ ከዚህ በፊት ያላቀረባችሁትን ከሽብር ጋር የተያያዘ የሚለውን ጭብጥ አልቀበልም፣ ተጨማሪ የ28 ቀናት የምርራ ጊዜ የተጠየቀውም ተገቢ አይደለም ካለ በኋላ የ14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ በመስጠት ለእሁድ ግንቦት 24 ቀን 2006 ዓ.ም. ጠዋት ተለዋጭ ቀነ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ፍርድ ቤቱም ፖሊስ ያቀረበውን ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ የሚውን ውድቅ አድርጎታል፡፡
ትናንት ግንቦት 9 ቀን 2006 ዓ.ም. የነበረው የ 6ቱ ጋዜጠኞች እና ብሎገሮች ፖሊስ ጉዳዩን ከሽብር ጋር አያይዞ ተጨማሪ የ28 ቀናት የጠየቀው ተፈቅዶለት ለሰኔ 7 ቀን 2006 ዓ.ም. ጠዋት ተለዋጭ ቀነ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል፡፡ ትናንት የነበረው የ6 ቱን ጉዳይ የተመለከተው ዳኛ ወንድ ሲሆን የዛሬውን ጉዳይ የተመለከተችው ዳኛ ሴት መሆኗ ተጠቁሟል፡፡

ጋዜጠኞቹ እና ብሎገሮቹ የፍርድ ቤት ውሎ

የጋዜጠኞቹ እና ብሎገሮቹ የፍርድ ቤት ውሎ
“የሥነልቡና ጫና ደርሶብኛል”
ጋዜጠኛ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ
“ከሌሊቱ 8 ሰዓት እየተወሰድኩ ድብደባ፣ ማስፈራራት እና ወከባ ተፈጽሞብኛል”
አጥናፍ ብርሃኔ
“ለምርመራ የምጠቀምበት አንድ ኮምፒውተር ነው ያለኝ፤ ጊዜ ይሰጠኝ”
ፖሊስ
ቅዳሜ ግንቦት 9፣ 2006 በቀጠሯቸው መሠረት አራዳ ምድብ ችሎት የቀረቡት 3 ጋዜጠኞች እና 3 ብሎገሮች ነበሩ፡፡ ፖሊስ የተጠርጣሪዎቹን ጉዳዩ ከወንጀል ወደ ሽብር በማሻሻሉ እና ምርመራዬን አላጠናቀቀኩም በማለቱ የ28 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቆ ተፈቅዶለታል፡፡ ሦስት ሰዓት ይሰማል የተባለው ችሎት 4፡30 አካባቢ የተጀመረ ሲሆን በመዝገብ ቁጥር 118721 የተከሰሱት ሦስት ተጠርጣሪዎች ኤዶም ካሣዬ፣ አጥናፍ ብርሃኔ እና ናትናኤል ፈለቀ በመጀመሪያ ቀርበዋል፡፡ በዛሬው ችሎት ከእየአንዳንዱ ታሳሪ ሦስት የቤተሰብ አባላት ወደ ችሎት ገብተው እንዲታደሙ ተፈቅዶ ነበር፡፡ ፖሊስ ክሱን ከወንጀል ወደ ሽብር ከፍ አድርጎ ቀርቧል፡፡ ምርመራዬን ስላላጠናቀቅኩ የተጨማሪ የ28 ቀናት ጊዜ ይሰጠኝ ብሎም ለችሎቱ ጥያቄ አቅርቧል፡፡ የተከሳሽ ጠበቆች ግን ከዚህ ቀደም በተሰጠው ሁለት ቀጠሮዎች ውስጥ አጣራቸዋለሁ ያላቸው 6 ጉዳዮች አሁንም አልተሰሩም፤ ድርጊቱ ደንበኞቻችንን በቀጠሮ ማጉላላት ነው፣ ማስረጃ ባልተሰበሰበበት ሁኔታ ከወንጀል ወደ ሽብር የተቀየረበት መንገድም ተገቢ አይደለም ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ ፖሊስ መተርጎም ያለባቸው ሰነዶች ወደ ትርጉም ቤት ተልከዋል፣ ግብረአበሮቻቸው አድራሻ እየለዋወጡ ሊያዙልኝ አልቻሉም፣ አቀርባለሁ ያልኳቸውን ምስክሮችም እያስፈራሩብኝ ለማቅረብ አልተቻለኝም ሲል መልሷል፡፡ ፍርድ ቤቱም የተጠየቀውን የ28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ፈቅዷል፡፡ በዚህም መሠረት ጋዜጠኞቹ እና ብሎገሮቹ ቅዳሜ ሰኔ 7፣ 2006 ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት እንዲቀርቡ አዟል፡፡ አጥናፍ ብርሃኔ ከሌሊቱ በስምንት ሰዓት ወደ ምርመራ ክፍሎች እየተወሰደ በመርማሪዎች ወከባ፣ ድብደባ እና ማስፈራሪያ እንደደረሰበት ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ ባለፈው ቀጠሮ ሚያዚያ 30 ቀርበው የነበሩት በፍቃዱ ኃይሉ እና አቤል ዋበላ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ለፍርድ ቤቱ ማስረዳታቸው ይታወሳል፡፡ ቀጥሎ በታየው መዝገብ 118722 ተጠርጥረው የቀረቡት አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ፣ ተስፋዓለም ወልደየስ እና ዘላለም ክብረት ክሳቸው ወደ ሽብር ተለውጦ በመቅረቡ እነሱም ሰኔ 7 ቀን 2006 እንዲቀርቡ ታዟል፡፡ ለችሎቱ የመናገር እድል እንዲሰጠው ጠይቆ የተፈቀደለት ጋዜጠኛ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ “መርማሪው የዞን 9 አባል አለመሆኔን ቢያምንም በተደጋጋሚ ጊዜ እየተጠራሁ አንድ ዓይነት በሆነ ጥያቄ ስለዞን 9 የምታውቀው ነገር አለና ተናገር እየተባልኩ ከፍተኛ የሥነልቡና ጫና ደርሶብኛል፡፡ ጋዜጠኛ እንደሆንኩም ያውቃሉ፡፡” በማለት ቅሬታውን እንባ እየተናነቀው አሰምቷል፡፡ የአስማማው ሁኔታ የችሎቱን ታዳሚያን እንባ አራጭቷል፡፡ ጠበቆቻቸውም ፖሊስ ከዚህ ቀደም በጠየቃቸው ቀጠሮዎች የሰራው ነገር ስለሌለ የ28 ቀን ቀጠሮ ሊሰጠው አይገባም፤ ዋስትና ይፈቀድልን፤ ዋስትና አያሰጥም እንኳን ከተባለ ፖሊስ ከዚህ በኋላ በጠየቀው ጊዜ ምን ሊሰራ እንዳሰበ ይግለጽልን ሲሉ ለችሎቱ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ መልስ የሰጡት መርማሪም በመረጃ ዴስካችን ውስጥ ያለን ኮምፒዩተር አንድ ብቻ በመሆኑ የሁሉንም ተጠርጣሪዎች ፋይል ለማጣራት ጊዜ ወስዶብናል ብለዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በሕቡዕ ተደራጅተዋል፤ ከእያንዳንዳቸው ኢ-ሜይል ለአመጽ የሚቀሰቅሱ ማስረጃዎች አግኝተናል እያንዳንዱን ለማስተርጎም ጊዜ ይወስዳል፤ በስማቸው ከውጭ የተላከ ገንዘብ እንዳለና ለሽብር ድርጊት ሊጠቀሙበት እንደሆነ ደርሰንበታል ያለ ቢሆንም ጠበቆቻቸው ግን ፖሊስ የጸረ-ሽብር ሕጉን አለአግባብ እየተጠቀመበት ነው፤ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ እና ተስፋለም ወልደየስ የዞን ዘጠኝ አባላት አይደሉም፡፡ ጋዜጠኞች ናቸው፡፡ ደንበኞቻችንን ሊያስጠረጥራቸው የሚችል ወንጀል አልተገኘባቸውም ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ የዞን 9 አባላት ከውጭ የሽብር አካላት ስልጠና አግኝተዋል የሚለው ልክ አይደለም፡፡ አርቲክል 19 እና ፍሪደም ሃውስ ሀሳብን የመግለጽ መብት እንዲከበር የሚንቀሳቀሱ ዓለም አቀፍ ተቋማት ናቸው፡፡ የትም ሀገር እና ቦታ የሽብር ተቋማት ተብለው አያውቁም፡፡ በኛም ሀገር በፓርላማ ሽብርተኛ ተብለው አልተወገዙም ሲሉ ጠበቆቻቸው ተናግረዋል፡፡ በመዝገብ ቁጥር 118720 የተካተቱት በፍቃዱ ኃይሉ፣ ማህሌት ፋንታሁን እና አቤል ዋበላ እሁድ ግንቦት 10 ቀን 2006 ዓ.ም ጠዋት ይቀርባሉ፡፡ ጋዜጠኞቹ እና ብሎገሮቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሚያዚያ 18 እና 19 ቢሆንም ጠበቆቻቸው እንዲጎበኟቸው የተፈቀደው ግን ባሳለፍነው ረቡዕ ግንቦት 6 እና አርብ ግንቦት 8፣ 2006 ነው፡፡

Friday, May 16, 2014

ጁነዲን ሰዶ አትላንታ አሜሪካ ገቡ

ጁነዲን ሰዶ አትላንታ አሜሪካ ገቡ
May 15, 2014
Junedin Sado“ይሄ ፋሽስት መንግሥት!” ማለት ጀምረዋል!
አገር ለቀው የኮበለሉትና የኦሮምያ ፕሬዚዳንትነትን ጨምሮ በተለያዩ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች በሚኒስትርነት ማዕረግ ያገለገሉት እንዲሁም የኦህዴድና የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ጁነዲን ሰዶ አሜሪካ መግባታቸውን በዋሺንግተን ዲሲ የሚታተመው ዘ-ኢትዮጵያ የተባለው የአማርኛ ጋዜጣ ይፋ አድርጓል። ኬንያ ለአንድ ዓመት ያህል በስደተኝነት ተቀምጠው የአሳይለም ወረቀታቸውን አግኝተው አትላንታ ከገቡ ሁለት ወራት እንደሆናቸውም የዘኢትዮጵያ ጋዜጣ ምንጮች ገልጸዋል።
አቶ ጁነዲን በአባ ዱላ ገመዳ እስኪተኩ ድረስ ከኦክቶበር 28/2001 እስከ ኦክቶበር 6 /2005 የኦሮምያ ክልል ፕሬዚዳንት ነበሩ። ከዚያም የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስትር በመሆን እስከ ኦክቶበር 2008 አገልግለዋል። በመቀጠልም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትርነት ከሠሩ በኋላ በመጨረሻም በ2010 የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር በመሆን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊን መንግሥት አገልግለዋል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲም የቦርድ ሊቀመንበር ነበሩ። መንግሥታቸው ብዙ ዓመት ከኖሩበት የሚኒስትሮች ካቢኔ ያሰነባታቸው የአቶ ኃይለማርያም የጠቅላይ ሚኒስትርነት ዘመን ሲጀመር ነው።የስደት ኑሯቸውን ማቃናት የያዙት አቶ ጁነዲን ከወዳጆቻቸው ጋር ሲያወጉ “ይሄ ፋሽስት መንግሥት እኮ የሚያደርገውን አያውቅም” በሚል መገረም ሲናገሩ መደመጣቸውን ምንጮቻችን ገልጸዋል። ባለቤታቸው ወ/ሮ ሀቢባ መሀመድ “በሽብር ተግባር ተጠርጥረዋል፣ ከሳዑዲ ኤምባሲ ገንዘብና መጽሐፍት ይዘው ሲወጡ ሐምሌ 9 ቀን 2004 እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል” በሚል ተዘውታሪ ሰበብ በእስር መቆየታቸው ይታወሳል። ከሥልጣናቸው በመስመጥ ላይ ለነበሩት አቶ ጁኒዲም ይህ የባለቤታቸው እስር ተጨምሮ ከአገር ለመኮብለል መንስኤ መሆኑ ሲዘገብ መሰንበቱ ይታወቃል።
ባለቤታቸውና ልጃቸው አሁንም በኢትዮጵያ የሚገኙ በመሆኑ አቶ ጁኒዲን በይፋ ምንም አስተያየት ሳይሰጡ ተቆጠበው መቀመጡን መምረጣቸው ተነግሯል። ሰሞኑን በኦሮምያ ክልል ተማሪዎች ላይ እየደረሰው ያለው ግድያና ሁከት በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የሚመለከታቸው ቢሆንም፣ እንደ ተራ ሰው “ይሄ ፋሽስት መንግሥት ምን እያደረገ ነው” ብለው መገረማቸው መልሶ ማሰገረሙን ምጮቻችን ገልጸውልናል። የኦሮምያ ክልል ፕሬዘዳንት ከነበሩት ውስጥ ሀገር ጥለው የኮበለሉ ፕሬዘዳንቶች ከአቶ ሀሰን ዓሊ ጋር አቶ ጁነዲን ሲደመሩ ሁለተኛ መሆናቸው ነው። ሁለቱም አትላንታ መሆናቸው ሲገለጽ አቶ ጁነዲን በአንድ ዩኒቨርስቲ መምርህነት ሥራ ለማግኘት ማመልከቻ ማስገባታቸውም ተነግሯል።
ምንጭ:(ዘኢትዮጵያ)