Tuesday, March 25, 2014

[የመልካም አስተዳደር እጦት በወሎ] የዘረፈ፣ እግር የቆረጠ፣ ሕዝብን በጥይት እየገደለ ያለ ስልጣን ላይ ሆኖ ይንደላቀቃል

ለዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ አዘጋጆች

ክቡር ሰላምታየ ይድረሳችሁ
ከዚህ በመቀጠል የዘወትር የፕሮግራምችሁ ተከታታይ ስሆን ይህን የመልካም አስተዳደር ችግር አየር ላይ እንድታውሉልኝ እየጠየኩ እን ሁልግዜው ለሁሉም የምታቀርቡትን አስተያየት ሙያችሁ በሚፈቅደው መሠረት እንደምታቀርቡልኝ ወይም አየር ላይ እንደምታውሉልኝ በመተማመን ነው፡፡
በሰሜን ወሎና ዞን በሀብሩ ወረዳና በመርሳ ከተማ እንደማንኛውም የኢትዮጵያ አካባባቢ በየግዜው የሚስተዋሉት የመልካም አስተዳደርና የሙስና ችግሮች ነዋሪውን የከተማና የገጠር ህዝብ እግር ተወርች ሰቅለው ይዘውታል፡፡ ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር ከመንግስት ደቀመዛሙርት መሰል ሚዲያዎች የምንተነፍስበት ወይም ሃሳባችንን የምንገልፅበት አማራጭ አለመኖሩ ነው፡፡ ይህም የናንተ የዘገባ አድማስ ሁሉንም አካባቢዎች የሚሸፍን አለመሆኑ ይመስለኛል ፡፡
ከዚህ በተረፈ ጉዳዩ አዲስና ልዩ ባይሆንም ድግግሞሽና አንደኛው ከሌለኛው ሲነፃፀር በጣም የከፋ እየሆነ በመምጣቱ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት አቤቱታው በምድር ላይ ያሉት ቱባ ባለስልጣኖች ጆሮ ነፊውን በየእምነቱ በፈጣሪው መፀለይ እና አቤት ለማለት ተገዷል እናም የናንተ የአቀራረብ ብስለት ታክሎበት መልዕክቱን ለአየር ታውሉልኛላችሁ ብዩ ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡
መቸም የመልካም አስተዳደር ጉዳይ ሲነሳ ተነግሮ አያልቅም ነገር ግን ቀደም የተፈፀመው በደል ላያንሰው አዳዲስና ከፀሐይ ጋር አብረው ብቅ የሚሉት የትም የለሉ ቢሆንም የቅርቡን ለመግለፅ ያህል

1. በመርሣ ከተማ አስተዳደር ነዋሪ የሆኑ 35 /ሰላሳ አምስት/ መንጃ ፈቃድ ያላቸው ነዋሪዎች በአማራ ክልል በቅርቡ እንዳያወጡ በመከልከላቸውና
ሙስና የበዛበት አሰራር ስላለ ወደ ተሻለውና አገሪቱን በበላይነት ወደ ሚመራው ክልል 1 ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ በመሄድ መንጃ ፈቃድ አውጥተው አሁን በከተማው የትግራይ ክልል መንጃ ፈቃድ አማራ ክልል ላይ አይሰራም በማለት ታግደዋል ፡፡ ክልሉ በማንና በምን እንደሚመራ ካለመታወቁም በላይ የወያኔን መሪነት ብአዴን መካዱ ይሆን ወይስ በአንድ አገር ሁለት ዓይነት ህግ መኖሩ ነው መልስ ያጣ ጉዳይ ሆኗል፡፡

2. በዚሁ በመርሣ ከተማ ዙሪያዋን በሚገኙ ወደ ከተማ የተከለሉ ቀበሌዎች ነዋሪ የሆኑ አራሽ ገበሬ ለፍቶና ጥሮ ለአመታት ጥሪቱን በሚያስጨርስ ሁኔታ የሰራውን ቤት ለምሳሌ አቧሬ አካባቢ የአቶ ሙመድ ሰይድ ቤት 8X9 የሆነ ቤት አገልግሎት በማይሰጥ መልኩ አፍርሰው ወደ ሌሎች መሰል ግለሰቦች ሲገቡ ነዋሪው ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ባለስልጣኖቹን በመፈታተኑ እንዲባረሩ አድርጓቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በ25/6/2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 /አራት ሰዓት ተኩል / አካባቢ በዚሁ ከተማ ልዩ ቦታው መልካጨፌ ከተባለው አካባቢ የ8 /ስምንት/ ሰው አርሶ አደር ቤት አፍርሰው ወደቀጣዩ ሲሸጋገሩ ጉዳዩ ያበሳጨው ነዋሪ ህዝብ ከአንድ መቶ በላይ የሚቆጠር ፖሊስ ፣ሚሊሻ አመራር በመሆን ህዝቡ በአመፅ በመነሳት ከሃምሳ በላይ ጥይት ተተኩሶ ሁለት ግለሰብ አርሶ አደሮች የህዝብ ተወካይ ነን በሚሉ ታጣቂዎች ተመትተው ቆስለው ህክምና ላይ ሲገኙ የጣፋው ጠፍቶ ቀሪውን በትግል ማዳን ችሏል ይሁንና መብቱን መገፋቱ ሳያንሰው ብሎም በቤት ውስጥ የነበሩ መንታ የወለደች ሴት ሜዳላይ እንድትወድቅ ተደርጓል ድርጊቱን ለምን ተከላከላችሁ ተብለው ሁከት ፈጣሪ በመባል ማረሚያ ቤት ገብተው ይገኛሉ ፡፡ ቀሪዎቹ ነዋሪዎች የተተኮሰውን ጥይት ዋጋ እንዲከፍሉ ተጠይቀዋል፡፡ ይህ የህዝብ ወገናዊነት ወይስ ምን ይሉታል ?

3. የህዝብን ሀብትና ንብረት ስልጣናቸውን ተጠቅመው የከበሩ የወረዳ አመራሮች ከመጠየቅ ይልቅ ወደ ፓርላማ እንዲገቡ ለከፍተኛ ትምህረት ተቋም ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ መሬት በሽልማት የሚሰጥበት ለህገ-መንግስቱ መሬት መሸጥ መለወጥ ላሳር የተባለበትን ለካቢኔ በሽልማት የሚሰጥበትን ሁኔታ ሲኖር ከዚህ እንደሚቀጥለው ይሆናል
ለአብነት ያክል፡-
• የቁጥር 27 ቀበሌን የገበሬውን መሬት የሸጡ ወይም እንዲሸጥ በቃለ ጉባዔ የያዙ የከፍተኛ ትምህርት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሲበረታቱ የቀበሌው አስተዳዳሪ ግን በ9/ዘጠኝ/ አይነት ክስ ተከሶ ማረሚያ ቤት ይገኛል
• በተጨማሪ11/አስራ አንድ ቤት /ያቃጠለ የአንድ ሰው እግር የቆረጠ ይባስ ብሎ በዚሁ ድርጊቱ ሳይበቃው ከሌላ የካቢኔ ጓደኛው ጋር በመሆን በሽጉጥ ከስደት ተመላሽ የሆነን ግለሰብ በሴት ምክንያት ጠግቦ አደሮች እጁ ላይ ተመትቶ በሆስፒታል በመረዳት ላይ ሲገኝ ይህ ሳያንስ ቤተሰቦቹ ተለቅመው እንዲታሰሩ ተደርጎ ሲቀጡ ጉዳዩን የፈፀሙት ባለስልጣኖች እድሜ ለስልጣን ብለው ሌላውን ባለተራ የጥይት ማረፊያቸውን ይጠብቃሉ።

4. የወረዳው አመራር /የሀብሩ ወረዳ ማለቴ/ ነው ከክልል በመጣ የኦዲት ባለሙያ በተረጋገጠው መሠረት አንድ አመራር ከ44 – 75 ሽህ ብር ከ365
ቀን በላይ በውሎ አበልና መሰል የወጭ ዘዴ ተጠቅሞ ከህግ ውጭ ማድረጋቸው ስለተረጋገጠ የክልሉ ኦዲተር ሪፖርት ቀርቦ እያለ እስካሁን ድረስ በህግ ፊት ሁሉም ሰው እኩል ነው የሚባለውን በነሱ ላይ ስለማይሰራ በፍታብሄርም ሆነ በወንጀል እንዳይጠይቁ ጠያቂና ተጠያቂ ጠፍቶ የአገር ሀብት ባክኖ ቀርቷል፡፡ አቤት የሚባልበት ቦታ ጠፍቷል ፡፡

5. ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት ጉዳዮች ማለትም የገጠር ወረዳውና የከተማ አስተዳደሩ የሚፈፅማቸውን አላግባብ የሆኑ አሰራሮች መከታተልና መቆጣጠር የተፈፀመውንም ሆነ ችግሮች እንዳይፈፀሙ መከላከል ሲገባቸው ይባስ ብለው የወረዳው ፍ/ቤት ሰብሳቢ ዳኛ ከዳኝነት ነፃ የሆነው እንኳ ሳይቀር የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ ካቢኔ ተብየው እነዚህ አመራሮችና ሙሰኞች በህግ እንዳይጠየቁ ምርመራ ሲጀመር ከዞን ጀምሮ ምርመራ እንዲቋረጥ እየተደረገ የዳኝነት ነፃነት በሚጋፋ መልኩ በህግ ፊት ሁሉም ሰው እኩል ነው ተብሎ በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 25 ላይ በግልፅነት ተቀምጦ እያለ ለአመራር /ተሿሚ / ህጉ የማይሰራበት ለሌች ዜጎች ግን ተተንትኖና ተዘርዝሮ የሚሰራበት ወረዳ በመሆኑ ህግ አልባነት ወይስ ህግ የተላበሰ አሰራር ይህን ሁሉም መልሶ አጥቶበታል።
በአጠቃላይ በከተማችንና በወረዳችን ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግር የሰዎች ሰብዓዊ መብት አለመከበር ድብደባ ዛቻና ማስፈራራት በመጠቀም ስልጣናቸውን ለማራዘም ከላይ ታች የሚባዝኑ ስለሆነ ለሀገርም ሆነ ለህዝብ የማይጠቅም በመሆኑ ይህነን አስነዋሪ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የማይመጥንና የማይገልጽ ነውር ተግባር በህዝቡ ስምና በራሴ ስም ለአየር ይበቃ ዘንድ መልካም ትብብራችሁን ከአክብሮት ጋር እንደማትነፍጉኝ በመተማመን አቀርባለሁ፡፡
የዘወትር አንባቢያችሁ ይነበብ ታምሩ
ከመርሳ ከተማ

Sunday, March 23, 2014

በአዲስ አበባ አንድ አንበሳ አውቶቡስ 15 ሜትር ጥልቀት ካለው ድልድይ ገባ፤ 8 ሰዎች ሞቱ

(ዘ-ሐበሻ)
በአዲስ አበባ ከተማ ከካራ ቆሬ ወደ ለገሃር ሲጓዝ የነበረ አውቶቡስ ዘነበወርቅ አለርት ሆስፒታል ፊትለፊት ረዥም ድልድይ ውስጥ ገባ፤ በዚህ አሰቃቂ አደጋ ስምንት ሰዎች መሞታቸው ይፋ ሆነ።
አውቶቡሱ ቁጥራቸው እስካሁን በውል ያልታወቁ ተሳፋሪዎችን ጭኖ ይጓዝ የነበረ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ሲያስታውቅ የአውቶቡሱ ቁጥር 66 እንደሆነ ታውቋል።
ካራ ቆሬ ወደ ለገሃር ሲጓዝ ዘነበወርቅ አለርት ሆስፒታል ፊት ለፊት ባለው ረዥም ድልድይ ውስጥ በገባው አውቶቡስ የተነሳ በአደጋው እስካሁን አንድ እግረኛን ጨምሮ አራት ወንድ እና አራት ሴት ተሳፋሪዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ሲገለጽ 46 የሚሆኑት ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ዘ-ሐበሻ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል። የአውቶቡሱ ሹፌር እና ትኬት ቆራጭ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በሕይወት ተርፈዋል።
የአውቶቡሱ አደጋው መንስኤ ላይ መሆኑ ሲታወቅ በአውቶቡሱ ድልድይ ውስጥ መግባት ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑ ዘ-ሐበሻ ጨምሮ የደረሳት ዜና ያስረዳል።

Friday, March 21, 2014

Breaking News

Semayawi party chairman barred from boarding flight to the US.

March 21, 2014

Eng. Yilkal Getnet, Chairman of the Blue Party (semayawi party) was barred from boarding a plane to the US by TPLF (Ethiopian government security) agents at Bole Airport tonight, March 21, 2014.
Eng. Yilkal was coming to the US as a fellow under “Young African Leaders Initiative” of the United States govt.
Eng. Yilkal’s luggage were unloaded from the plane and he stayed at the airport for more than 3 hours questioned by TPLF thugs.
Stay tune for updates…

አንዳንዴ ኑሯችን በራሳችን እንድንቀልድ ያስገድደናል


አንዳንዴ ኑሯችን በራሳችን እንድንቀልድ ያስገድደናል:: ካለፉት በርካታ አመታት ጀምር በአዲስ አበባ የሚታየውን የመብራት መቆራረጥ የተመለከተ ሰው በሙሉ ያዝናል:: ይህ ሃዘን ወደ ብሶት ቁጣ ተቀይሮ ሰሞኑን በተከታታ ህዝቡ በመብራት ሃይል ላይ የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ ቁጣውን እየገለጸ ነው:: አንድነት ፓርቲም ይህን አስመልክቶ “የ እሪታ ቀን” ብሎ የሰየመውን የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀምሯል:: እኛ ከውጭ ሆነን ነገሮችን ስንመለከታቸው እውነት የማይመስሉ እውነቶችን እያየን መገረማችን አልቀረም:: ይህንን ግርምት በቀልድ ቢጤ ብናዋዛው ብለን ስናስብ ደግሞ የሜትሮሎጂ አየር ትንበያ ታወሰን:: መብራት ሃይል በሜትሮሎጂ ዜና አይነት የሰሞኑን የመብራት መጥፋት እና መጥፋት ዘገባ ምን ብሎ ቢያቀርብልን ይገርመናል:: እስኪ በራሳችን እየሳቅን የመብራት ሃይልን… ሜትሮሎጂያዊ ዜና ከዚህ በታች እናንብብ::
የሰሞኑ የአዲስ አበባ የመብራት ሃይል… ይቅርታ የመጥፋት ሃይል ትንበያ ከዚህ በመቀጠል ይቀርባል:: በሰሜን አዲስ አበባ… ከበላይ ዘለቀ ጎዳና እስከ ፒያሳ፣ ውቤ በርሃ፣ አራዳ፣ ዶሮ ማነቂያ፣ ሰራተኛ ሰፈር፣ ከቸርችል ጎዳና እስከ ቴዎድሮስ አደባባይ ድረስ መጠነኛ የሆነ የመብራት መቆራረጥ ይደርሳል:: ከዚያ ወረድ ብሎ በስቴዲየም እና አካባቢው, መስቀል አደባባይ, ከእስጢፋኖስ እስከ መገናኛ 22 ማዞሪያ እና ኮተቤ ድረስ… እንዲሁም በካዛንቺስ አካባቢ ደብዛዛ እና ፈዛዛማ የመብራት ብርሃናት ይታያሉ::
በቦሌ እና ቦሌ ቡልቡላ መብራት እንደበጋ መብረቅ ብልጭ ድርግም ይላል:: ከላፍቶ እስከ ሳሪስ; ወሎ ሰፈር፣ ጎፋ ማዞሪያ፣ ቄራ፣ ሳር ቤት፣ እንዲሁም ከአየር ጤና እስከ ሜክሲኮ አደባባይ ነጎድጓዳማ የመብራት መቆራረጥ ያጋጥማል:: በጨርቆስ እና አካባቢ… እንደከዚህ ቀደሙ ደረቅ አየር እና ድፍን ጨለማ ሆኖ ይሰነብታል::

የአዲስ አበባ ምእራባዊ ዞን… ከተክለሃይማኖት ሰፈር ጀምሮ በአብነት አድርጎ እስከ ሰባተኛ እና መርካቶ ድረስ፣ መሳለሚያ፣ ኮልፌ ከዊንጌት እስከ ቡራዩ ድረስ ምንም አይነት የኤሌክትሪክ ስለማይኖር ከመብራት አደጋ ነጻ ይሆናሉ::
በመሆኑም ክቡራን ደንበኞቻችን፤ በተለይም የንግዱ ህብረተሰብ ይህንኑ አውቆ አካባቢ በካይ የሆኑ የናፍጣ ጄነሬተሮችን እንዲጠቀም እናሳስባለን:: የባንክ አገልግሎት ሰጪዎች፣ የኮምፒዩተር ቤቶች… መብራት ቢመጣም እንኳን ኔትዎርክ ስለሌለ፤ ጽጉር ቤት እና ምግብ ቤቶችም… መብራት ብንሰጣችሁ ውሃ ስለማይኖር፤ ይህንን ተግዳሮት ግምት ውስጥ በማስገባት ነፋሻማ የሆነውን ቫት እና መብረቃማውን የሽያጭ ታክስ በመክፈል የዜግነት ግዴታችሁን እንድትወጡ ከወዲሁ እናሳስባለን::

በአጠቃላይ አዲስ አበባ እና ሌሎች ከተሞች ምሽቱን ጧፋማ፣ ኩራዛማ እና ሻማማ በመሆን ይሰነብታሉ:: ዛሬ ከሳተላይት ያገኘነው ተንቀሳቃሽ ምስል እንደሚያሳየው… አዲስ አበባ ከላይ ወደ ታች ስትታይ እንደክሪስማስ ዛፍ ብልጭ ድርግም ትላለች:: በዚህም ምክንያት ምሽት ሲሆን; አዲስ አበባን በአነስተኛ አውሮፕላን የሚጎበኟት ቱሪስቶች ቁጥር በእጥፍ ጨምሯል:: ከዘርፉ የሚገኘው የገቢ መጠን በመጨመሩ መንግስት ለዚህ አዲስ የስራ መስክ ትኩረት በመስጠት የማበረታቻ ገንዘብ እንደሚመድብ አስታውቋል:: ለስራውም መሳካት… መብራት ሃይል የሰፈር መብራቶቹን በፈረቃ በማብራት እና በማጥፋት; ምሽቱን “በብልጭ ድርግም” የሚያደምቀው መሆኑን በደስታ ገልጿል::

Tuesday, March 18, 2014

በነፃነት ቀን ነፃነት ማጣት !

ከይድነቃቸው ከበደ

ሰብአዊ መብቶች እያንዳንዳችን ሰው በመሆናችን ብቻ የሚገቡን ከሰብአዊነታችን ተለይተው ሊታዩ የማያችሉ መብቶች ናቸው፡፡ መንግስታት እነዚህን በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የተሰጣቸውን ሰብአዊ መብቶች ለማክበር ለማስከበርና ለማሟላት በቀዳሚነት ኃላፊነት አለባቸው፡፡ በዚህም መሰረት ኃላፊነት ከፈረሙ ቀደምት አገራት መካከል ኢትዩጵያ ትገኝበታላች፡፡ይሁን እንጂ የሴቶች ሰብአዊ መብቶች በሚፈለገው መልኩ ተግባራዊ ካለመሆኑ ባሻገር ኢ-ፍትሃዊነት እጅግ የበዛ ነው፡፡ ይህም በመሆኑም እ.ኤ.አ. በ1908 በአሜሪካ ኒወርክ ከተማ በጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ይሰሩ የነበሩ ላብአደር ሴቶች ‹‹ለእኩል ሥራ እኩል ክፍያና የተመቻቸ የሥራ ሰዓት ለሴቶች›› በሚል መፈክር የሥራ ማቆም አድማ በማካሄድ የሴቶች ድምፅ እንዲስተጋባ አድርገዋል፡፡ ይህን ተከትሎ የዓለም ሴቶች በማህበር በመደራጀት ትግላቸውን በማጠናከራቸው የዓለም መንግስታትን አስተሳሰብ በመለወጥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል አገሮች የሴቶች መብት ስምምነት/ኮንቪክሽን/ እንዲፈራረሙ እብይ ምክንያት ሆነዋል፡፡


እ.ኤ.አ. በ1910 በኮፕን አገር ከተማ በተደረገው ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የሴቶች ጉባሄ ላይ የመነሻ ሃሳብ በማቅረብ ማርች 8 በየዓመቱ እንዲከበር ያደረጉት ሴቶች ለመብታቸው ያደረጉትን አስታውጾ ለመዘከር ዓለም አቀፍ መድረክ ለማመቻቸት በመቻላቸው ስማቸው በአክብሮት ይነሳል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓሉን ያከበሩት ጀርመን፣አውስትራሊያ፣ሲውዘርላንድ እና ዴንማርክ ለመሆናቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
ከዚሁ የአንድነት ተምሳሌትነት በመነሳት በዓለማ አቀፍ ደረጃ ማርች 8 የሴቶች ቀን በማድረግ ዓለም አቀፍ ስያሜዎችን በመስጠት አገራችን ኢትዮጵያ ጨምሮ በተለያየ መልክ ሲከበር አመታትን እቆጥሯል፡፡ የዘንድሮዉም ማርች 8 አለም አቀፍ የሴቶች ቀን እስከ ዛሬ በአገራችን በተከታታይ የኢትዮጵያ ሴቶች ካከበሩት በዓላት የሚለየው ሁሌም የምኮራባቸው የሰማያዊ ፓርቲ ሠላማዊ ታጋይ ሴቶች የፈፀሙት ገድል ነው፡፡
በአገራችን ኢትዮጵያ የዜጎች መብት በእኩልነት ተጠብቆ በሴቶች ላይ አጥልቶ የኖረው የጾታ ጭቆና እስከዛሬ ምላሽ ያላገኘ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡በተለይ በወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት የስልጣን ዘመን የሴቶች ጭቆና እና የመብት እረገጣ በህግ ማቀፍ ውስጥ መሆኑ ይብልጥ አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡ ይህን ለማለት የሚያስደፍረው የህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ነው በሚባለው ህገመንግሰት የፆታን አድልዎ የሚቀርፍ እና የሴቶችን መብት የሚያመላክት ድንጋጌዎች በውስጡ አካቶ የያዘ ቢሆንም ተግባሪዊነቱ ፕ/ር መስፍን እንዳሉት ‹‹የተፃፈበትን ወረቀት ያህል ዋጋ የማያወጣ ነው››፡፡ ዋጋ አለው እንኳን ከተባለ የትርፉ ተካፋይ የሆኑት የገዥው መንግሰት አጨብጫቢዎች እና የጡት ልጆች ብቻ ናቸው፡፡

በአገራችን መከበር ከጀመረ ከሦት አስርታት በላይ ያስቆጠረው ማርች 8 ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ለሴቶች በሴትነታቸው ከሚደርስባቸው ጾታዊ በደል እና የሰብአዊ መብት ጥሰት ያስቀረላቸው አንድም ነገር የለም፡፡ በተለይ ከላይ እንደተገለፀው በወያኔ/ኢህአዴግ መንግሰት ሴቶች በህግ እና በመብት ጥላ ስር ከፍተኛ የሰብአዊና የዲሞክራሲ ጥሰት እየተፈፀመባቸው ይገኛል፡፡
እጅግ አስገራሚው ክስተት ደግሞ የኢህአዲግ ሴቶች ሊግ ፣ የሴቶች ፎረም ኢህአዲግ የሚያዘው እና አገዛዙ ያስተባበራቸው በርካታ የሴት ማህበራት ተጠሪነታቸው በቀጥታ ለወያኔ መንግስት ስርአት ነው፡፡ ስርአቱ ደግሞ የመላው ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ እና ይሁንታ ያላገኘ መሆኑ ነው፡፡ ነገሩን ይበልጥ አሳሳቢ የሚያደርገው ደግሞ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ከመንግስት ድጋፍ ውጪ በራሳቸው ፍቃድና አቅም አንድም የተደራጀ ማህብር የሌላቸው መሆኑ ነው፡፡ እርግጥ ነው የሴቶች የፅዋ እና የእድር እንዲሁም የዕቁብ ማህበራት በአገራችን ለቁጥር የሚታክቱ ነው፤ግን እነዚህ ማህበራት የሴቶችን ሁለንተናዊ ችግሮችን የሚቀርፉ አይደለም፡፡

ለመደራጀት ሳይሆን ለማደራጀት ትኩረት እና ድጋፍ የሚሰጠው መንግሰት በሴቶች ላይ ማላገጥን ስራዬ ብሎ ተያይዞታል፡፡ለዚህም እንደማሳያ ከታችኛው የቀበሌ ባለስልጣን ጀምሮ እስከላይኛው የአገር መሪ የሴቶች እኩልነት እና የመደራጀት መብት በህግ የተጠበቀ እንደሆነ ሳይታክቱ የሚገልፁት ነገር ነው፡፡ይሁን እንጂ የሴቶች እኩልነት እና የመደራጀት መብት ለኢህአዴግ አባልነት እና ቤት ለቤት ቡና እያጣጡ የተነገራቸው መልሰው ከማውራት ከቅያስ ወይም ከጎሮ ከድሬነት ያለፍ ተሳትፎ ከተደራጁበት ሳይሆን ከደራጃቸው አካል ያተረፉት ነገር የለም፡፡ ከላይ የተጠቀሰው አሳብ ለመረዳት እና ለመታዘብ ብዙ መራቅ አያስፈልግም በህገመንግስቱ መሰረት ተደራጅተዋል የተባሉ ማናቸውም እንዲሁም በየትኛውም ቦታ የሚገኙ የሴት ማህበራት ከመንግሰት ተፅኖ ውጪ ላለመሆናቸው ከማህበራቸው የስም አወጣጥ ጀምሮ ተግባራቸው በመመልከት በቀላሉ ማህበሩ እና ማህበርተኞችን እነማን እንደሆኑ ለመረዳት ይቻላል፡፡

ለዚህ ፁሑፍ መነሻ የሆነው አሳብ ዘንድሮ ተከብሮ ሳይሆን ተደፍሮ ለማለት በሚያስችል ሁኔታ ማርች 8 መሰረት ያደረግ ነው፡፡ እንደሚታወቀው የባለፈው እሁድ ማርች 8 አስመልክቶ የሴቶች 5 ሺህ ኪ.ሜ ሩጫ ውድድር ተካሂዶአል፡፡ በውድድሩ ላይ ቁጥራቸው የበዛ ሴቶች ተሳትፈዋል ፤ከተሳታፊዎቹ ብዛት ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ በአነስተኛ እና ጥቃቅን መንግስት ያደራጃቸው ሴቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ሴቶች አደባባይ ይዘው የወጡት አሳብ ጥቃቅን መሆኑ በእርግጥም ማህበርተኞቹ ምን ያህል አንድ ለአምስት ‹‹እደተጠረነፉ›› የሚያሳይ ነው፡፡ የጉዳዩ አሳሳቢነት የሚጀምረው እነኚህ ጢቂት ‹‹የተጠረነፉ›› ሴቶች በነፃነት ቀናቸው ነፃነት የተነፈጋቸው መሆኑ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ እሩጫው ላይ የተሳተፉት በራሳቸው ፍቃድ ሳይሆን በድረጅታቸው ትዕዛዝ ነው ሊያስብል የሚያስችል የተለያየ ‹‹ልማታዊ›› የሆነ መፈክሮችን ሲያሰሙ ተደምጠዋል፡፡በመንግሰት ልዩ ድጋፋ የተደረገላቸው እነኚህ ሴቶች ለሚደግፉት ሳይሆን ለተገደዱበት ዓላማ የመሰላቸውን መፈክር እና ቀረርቶ በማሰማት እንዲሁም የተለያዩ ፖስተሮችን በመያዝ በዕለቱ ሲንቀሳቀሱ ታይተዋል፡፡

ይሁን እንጂ ለመንግስት ደጋፊዎች የተፈቀደው ለሌሎች ለመንግሰት ተቃዎሚ ሴቶች ፖሊስ ያደረገው ክልከላ እና እስራት ክስተቱን አስገራሚ ብቻ ሳይሆን አሳሳቢያ ደርገዋል፡፡ እንደሚታወቀው ማርች 8 ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ነው፤ ይህ ቀን ሴቶች ተሰባስበው ከበሮ ይዘው የሚደልቁበት ቀን ሳይሆን ለነፃነታቸው ቀደምት ሴቶች ያደረጉትን ተጋድሎ በመዘከር ያሁኖቹ ሴቶች ለበለጠ እኩልነት እና ነፃነት በጋራ የሚቆሙበት የቃል ኪዳን ቀን ነው፡፡ ይህም እንደሆነ የተረዱ ሴቶች በነፃነት ቀናቸው ስለነፃነታቸው ከፍ ባለ ድምፅ ሲዘምሩ ማየት ምንኛ መታደል ነው ! ይህን በድፍረት ላደረጉት የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሴቶች አድናቆት ሊቸራቸው እና ድጋፍ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ሴቶች በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ በአደባባይ ታፍሰው ለእስር የበቁት በእኔ ዘመን ይህ የመጀመሪያ ነው ፡፡የኔ ዘመን ደግሞ 23 ዓመት ሙሉ የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ የበላው ጅብ አልጮው ብሎ ተቸግረን የከረምንበት ወቅት ነው፡፡ እርግጥ ነው ይህ የሆነበት ምክንያት ለማወቅ እና ለመዘርዘር ሰፊ ጥናት ያስፈልጋል፡፡ የችግሩ አሳሳቢነት እንደተጠበቀ ሆኖ እንቢ ለነፃነቴ በማላት አደባባይ በመውጣት የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሴቶች ‹‹ እኔ የጣይቱ ልጅ ነኝ ! እስክንድር ይፈታ ! እርዮት ትፈታ ! አብበከር ይፈታ ! አንዱአለም ይፈታ ! መብራት እና ውሃ ናፈቀን ! ፍትህ እንፈልጋለን ! ›› እና የመሳሰሉትን መፈክር በልበ ሙሉነት በማሰማት ያሳዩት ቆራጥነት ታሪክ መቼም የሚዘነጋው አይደለም፡፡ በይበልጥ ደግም በዚሁ የፖለቲካ አመለካከታቸው ምክንያት ብቻ ለእስር መዳረጋቸው የመንግስት ስርዓት ምን ያህል አምባገነን እና ጨቋኝ እንደሆን በግልፅ የሚያሳይ ነው፡፡

Sunday, March 16, 2014

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ተጨማሪ አራት ቀን እስር ቤት እንዲቆዩ ተደረገ

March 14, 2014

Semayawi Party- EthiopiaBlue Party’s executives and female members
ባለፈው ሰኞ ፖሊስ መረጃ ለማሰባሰብ በሚል ፍርድ ቤት የ14 ቀን ጊዜ ጠይቆ 5 ቀናት እንደተፈቀደለት ይታወቃል፡፡ ዛሬ መጋቢት 5 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የካ ምድብ ችሎት ቢቀርቡም ፖሊስ አሁንም ‹‹ምርምራውን አልጨረስኩም፣ ተጨማሪ የምይዛቸው ሰዎች አሉ፣ የተያዙትም ቢለቀቁ ሌላ ወንጀል ይሰራሉ›› በሚል ሰባት ተጨማሪ ቀናት እንዲሰጡት ጠይቋል፡፡
በአንጻሩ የታሳሪዎቹ ጠበቃ ሆነው የቀረቡት የጋዜጠኛ ርዕት አለሙ አባት አቶ አለሙ ጌደቦ በበኩላቸው ፖሊስ ተሰጥቶት የነበሩት ሰባት ቀናት መረጃ ለማሰባሰብም ሆነ ሌሎች የምይዛቸው ተጨማሪ ሰዎች አሉ ያላቸውን ቢኖሩ ኖሮ ለመያዝ በቂ እንደነበር አስረድተዋል፡፡ በተጨማሪም ታሳሪዎቹ በኃላፊነት ቦታ ላይ የሚሰሩና ቋሚ አድራሻ ያላቸው በመሆኑ በዋስ ተለቀው ጉዳያቸውን መከታተል ስለሚችሉ የዋስትና መብታቸው እንዲጠበቅላቸው ተከራክረዋል፡፡Semayawi party activist court show up
በሌላ በኩል ታሳሪዎቹ በምርመራ ወቅት በፖሊስና ‹በደህንነቶች› እየተፈጸመብን ነው ያሉትን በደል ለፍርድ ቤቱ አቅርበዋል፡፡ ‹‹የታሰርነው በያዝነው አስተሳሰባችን ምክንያት ነው›› ያለው የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ መታወቂያ ለማሳየት ፈቃደኛ ያልሆኑ ሲቪል የለበሱ ግለሰቦች ‹‹ሰማያዊ ከሚባል አሸባሪ ወጥታችሁ ከእኛ ጋር ካልሰራችሁ መቼ እንደምንገላችሁ አታውቁም፡፡›› በሚል እንዳስፈራሩዋቸው ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ ወንድ ፖሊሶች ሌሊት ሴቶች እስር ቤት ውስጥ በመግባት እንደሚያስፈራሩዋቸውም ተገልጻል፡፡ ሴቶቹ ታሳሪዎች ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ላይ ወንድ ፖሊሶች ከታሰሩበት እያስወጡ እንደሚያስፈራሩዋቸውም የየራሳቸውን አጋጣሚዎች ለፍርድ ቤት አቅርበዋል፡፡ ወጣት አቤል ‹‹ከእኛ ጋር ከሰራህ የተሻለ እንከፍልሃለን›› ብለውኝ አልፈልግም በማለቴ እንገልሃለን ብለውኛል በማለት ገልጹዋል፡፡
በተቃራኒው ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ሌሎች ታሳሪዎች ላይ ቅስቀሳ እያደረጉ መሆኑን፣ በጋራ እንደሚዘምሩ፣ ቃል ለመስጠት ፈቃደኛ እንደማይሆኑ በመግለጽ ተጨማሪ 7 ቀን እንዲሰጠው በድጋሜ ጠይቋል፡፡ ዛሬ ጠዋት ወደ ችሎት ሲመጡ የታላቁን ሩጫ ቲሸርት ካለበስን አንሄድም ማለታቸውንም ታሳሪዎቹ በቀጣይነትም ወንጀል ሊሰሩ ይችላሉ ለሚለው መከራከሪያው እንደ ማስረጃ አቅርቧል፡፡ ዳኛው ፖሊስ በታሳሪዎቹ ላይ እንዳደረሰው የተገለጸውንና ታሳሪዎቹ ሌሎች ታሳሪዎችን በማቀስቀስና በመረበሽ ያቀረበውን ክስ ላይ ምክር አዘል መልዕክት ካስተላለፈ በኋላ ተጨማሪ 4 ቀን የምርመራ ጊዜ ሰጥቷል፡፡
ችሎቱ መደበኛ ስራውን ይጀምራል ከተባለበት አንድ ሰዓት ዘግይቶ ሊጀምር ችሏል፡፡ በክርክሩ ወቅት መረዳት እንደተቻለውም ጠዋት ታሳሪዎቹ ወደ ፍርድ ቤት በሚመጡበት ጊዜ በሩጫው ዕለት ለብሰውት የነበረውን የታላቁን ሩጫ ቲሸርት መልበሳቸውን ፖሊስ በመቃወሙ በነበረው አለመግባባት መዘግየቱ እንደተከሰተ ታውቋል፡፡
ፖሊስ ሰኞ ዕለት ያስመዘገበው የክስ ጭብጥ እንደሚያመለክተው ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ያዋለው ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር ተንቀሳቅሰዋል፣ የጣይቱ ልጆች ነን፣ የምኒልክ ልጆች ነን፣ ዳቦ ራበን፣ ብለዋል በሚል ነው፡፡ በዛሬው የክርክር ሂደት እንደተስተዋለው ግን ፖሊስ የመጀመሪያዋን ጭብጥ ብቻ መዝዞ ተከራክሯል፡፡ መርማሪ ፖሊሱ በወቅቱ አሉኝ ያላቸውን የክርክር ነጥቦች በሚያስረዳበት ወቅት አለመረጋጋት ጎልቶ ይታይበት እንደነበር ተስተውሏል፡፡

Tuesday, March 11, 2014

በዴሞክራሲ” ስም የሚደረግ የመሬት ነጠቃና የዘር ማጥፋት ወንጀል በኢትዮጵያ

"በዚሁ ከቀጠለ አገሪቷ ወደ እርስበርስ ግጭት ማምራቷ አይቀሬ ነው"

                                 March 11, 2014
በአይነቱ የመጀመርያ የሆነ የውይይት መድረክ የካቲት 27 2006ዓም/March 6, 2014/ በኦስሎ፣ ኖርዌይ ከተማ ተደረገ። Frontline Club Oslo በተባለ ድርጅት አማካኝነት በኢትዮጵያ በዴሞክራሲ ስም እየተካሄደ ያለውን የመሬት ነጠቃ እና የዘር ማጥፋት ወንጀል በተመለከተ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን አካላት በመጥራት ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል። በስብሰባውም ላይም ከውጭ ጉዳይና ከሌሎች መስሪያ ቤቶች፣ ከዩኒቨርሲቲ፣ ከመንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ በኦስሎ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ለጉዳዩ ቅርበት ያላችው አካላት ተገኝተዋል።
ስብሰባውን የጠራው ድርጅት በመወከል ስብሰባውን በንግግር የከፈቱት ማርየስ ቮንዳርፈር እንደተናገሩት Fronline Club የተባለ ድርጅት በኦስሎ የተቋቋመው በያዝነው ዓመት ሲሆን አላማውም በዓለምአቀፍ ታዋቂ የፊልም እና የፎቶግራፍ ባለሙያዎችን፣ ጋዜጠኞችን፣ እና ምሁራንን በመጋበዝ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይቶች እና ዶክመንተሪ ፊልሞችን ማቅረብ መሆኑን ገልጸዋል። የዓመቱ ስራውንም የጀመረው በዚሁ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ እንደሆነ ተመልክቷል።
ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ በሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች አያያዝ ዙሪያ ጠንካራ ነቀፋና ተቃውሞ ያልተለየው መሆኑ ይታወቃል። የዚህም ውይይት ዋና አላማ በሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ዙሪያ የሚደርሰውን ችግር ትኩረት ለመስጠትና ተጽዕኖ ለማድረግ የሚያስችሉ አካላትን ጠርቶ ማወያየት ነው። በመሆኑም በውይይቱ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲሰፍንና የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ የምዕራባውያን መንግስታት በተለይም የኖርዌይ መንግስት ሚና ምን መሆን እንዳለበት በስፋት ትኩረት ተሰቶበታል። በውይይቱ ላይ አራት የተለያዩ አካላት ንግግር አድርገዋል።


የውይይቱ የመጀመሪያ ተናጋሪም አቶ አብዱላሂ ሁሴን ሲሆኑ እርሳቸውም የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ልዩ አማካሪና የኦጋዴን ቲቪ ቻናል ሃላፊ ሆነው ሰርተዋል። ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ሲሰሩ በነበሩበት ወቅት ያሰባሰቡትን መረጃ በቪድዮ የተደገፈ ዶክመንተሪ በዚህ ስብሰባ አቅርበዋል። የቀረበው ቪድዮ በክልሉ ፕሬዝዳንት እና በክልሉ ባለስልጣናት፣ ፖሊሶችና የጸጥታ አካላት መካከል የተደረጉ ምስጢራዊ ስብሰባዎችን አካቷል። በክልሉ እየተደረገ ያለውን ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ማሰርን፣ ማሰቃየትን፣ ግድያን እና በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት እና ስቃይ ራሳቸው የጸጥታ ኃይሎች የሰጡትን ምስክርነት ዶክመንተሪው አካቷል። በመንግሥት ወታደሮችና ፖሊሶች አማካኝነት በክልሉ እየደረሰ ያለውን አሰቃቂ ወንጀሎች ዶክመንተሪው በማስረጃነት የሚያሳይ በመሆኑ በቀጣይነት ሄግ ለሚገኘው አለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት እንደሚያቀርቡ አቶ አብዱላሂ አመልክተዋል።

በሶማሌ ክልል በሚሰሩበት ወቅት በተለያዩ ቦታዎች በህዝቡ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ችግር የተመለከቱ መሆኑን ከመጥቀሳቸው በተጨማሪ በአሰቃቂ ሁኔታ የሚካሄደው የዘር ማጥፋት ወንጀል ትኩረት እንዳልተሰጠው ተናግረዋል። ዓለምአቀፉ ማህበረሰብም ሆነ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን በመንግስት ባለስልጣናት እና የጸጥታ ኃይሎች እየደረሰ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በተመለከተ በቂ መረጃ እንደሌላቸው አቶ አብዱላሂ አመልክተዋል። ይህ የሆነበትን ምክንያት ለማስረዳት ተናጋሪው ሁለት ነጥቦች አንስተዋል። በመጀመሪያ ደረጃ ኢህአዴግ ጋዜጠኞችንና ዓለምአቀፍ ገለልተኛ ድርጅቶች ወደ ክልሉ እንዳይንቀሳቀሱ በመከልከሉ ሲሆን ይህም ድርጊት በተጨባጭ በክልሉ እየደረሰ ያለው እውነታ እንዳይሰማ፣ እንዳይታይ አድርጎታል። በሁለተኛ ደረጃ ኢህአዴግ ምዕራባዊያንን በውሸት የማሳመኑን ስልት የተካነበት በመሆኑ እስካሁን በክልሉ የሚደርሰውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በመሸፈኑ ተገቢውን ትኩረት እንዳያገኝ አድርጎታል ብለዋል። የሳቸውም አላማ ይህንን የሰበሰቡትን የቪዲዮ መረጃ ለዓለምአቀፉ ህብረተሰብ በማቅረብና በክልሉ የሚደርሰውን የዝር ማጥፋት ወንጀል በማስቆም ለዚህ ተጠያቂ የሚባሉ ባለስልጣናትና የጸጥታ ኃይሎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ መሆኑን ተናግረዋል።



በመቀጠል ንግግራቸውን ያደረጉት እውቁ የሰብአዊ መብት ተሟጋች እና ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዳይሬክተር የሆኑት የተከበሩ አቶ ኦባንግ ሜቶ ሲሆኑ የኖርዌይ ህዝብና መንግስት ለኢትዮጵያውያን ብሎም ለአጠቃላይ ሰብዓዊነት እያደረጉ ያለውን አስተዋጽዖ በማድነቅ ንግግራቸውን ጀምረዋል። በግጭትና በተለያዩ የፖለቲካ ቀውሶች ምክንያት በዓለማችን ተጠቂ ህዝቦች ካንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የመሰደዱ ሁኔታ የተለመደ መሆኑን በማመልከት ብዙ ስደተኞች ወደ ኖርዌይ የሚመጡበት ምክንያት አገሪቷ ሃብታም እና የበለጸገች ስለሆነች ብቻ ሳይሆን የአገሪቱ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ እና ለሰብዓዊነት ክብር ቅድሚያ በመስጠቷ መሆኑን አቶ ኦባንግ አመልክተዋል።

በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና የመሬት ነጠቃ ሁኔታ በመጥቀስ የኖርዌይ መንግስትና እርዳታ ሰጪዎች ሊወስዱ የሚገባቸውን እርምጃ በንግግራቸው ጠቁመዋል። በመቀጠልም ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ ሃብት የሚያሳይ ምስል በማቅረብ ምን ያህል አገሪቱ በተፈጥሮ የታደለች መሆኑንና ያገሪቱ ዋና ችግር የመልካም አስተዳደር እጦት እንደሆን አስረድተዋል። በስልጣን ያለው አገዛዝ በህዝቡ ላይ የሚያደርሰው ጭቆና አላንስ ብሎ የአገሪቱን መሬት ለህንድ፣ ለቻይና እና ለሳውዲ ኢንቨስተሮች በርካሽ እየሸጠ ይገኛል። በዚህም ምክንያት ከሚሸጠው መሬት የሚፈናቀሉ ዜጎች በአስከፊ የድህነት ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ በመጥቀስ የሚያፈናቀሉት ዜጎች ህይወት በመሬቱ ላይ የተመረኮዘ በመሆኑ ኢህአዴግ በኢንቨስትመንት ስም የሚደርገው ድርጊት የዜጎችን ኑሮ አናግቷል። ምዕራባዊያን አገሮችም በተለይም የኖርዌይ መንግስት ይህንን አስከፊ የህዝቡን ስቃይ እና ችግር እያዩ እንዳላዩ በመሆን ለአምባገነናዊ መንግስት የሚያደርጉትን ድጋፍ እና ድጎማ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ ይገኛሉ። ይህም የምዕራባዊ መንግስታት ዕርዳታ ህዝቡ እራሱን በራሱ ከአምባገነናዊ አገዛዝ ነጻ እንዳያወጣና ለማውጣት የሚያደርገውን ጥረት ላይ ትልቅ እንቅፋት እንደሆኑበት አቶ ኦባንግ ተናግረዋል።
ይህ ሁኔታም በዚሁ ከቀጠለም አገሪቷ ወደ እርስ በርስ ግጭት የማምራት ሁኔታ አይቀሬ መሆኑን በማመልከት ምዕራባዊ አገሮች በተለይ የኖርዌይ መንግስት ይህ ከመሆኑ በፊት የህዝቡ ስቃይ እና እንግልት የሚቆምበትን መንገድ በማፈላለግ እና በኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲያብብ ትልቅ ሚና መጫወት እንዳልባቸው አቶ ኦባንግ አሳስበዋል።
በሶስተኛ ደረጃ ንግግራቸውን ያደረጉት ዮሃን ሂላን የተባሉ የማህበራዊ ምሁር ሲሆኑ በሰሜን እና በምስራቅ አፍሪቃ በልማት ዘረፍ የማማከር እና የምርምር ስራ እየሰሩ እንደሚገኙ ከመድረኩ ተጠቅሷል። ባሁን ወቅትም በርገን በሚገኘው በክርስትያን ኤይድ ኢንስቲትዩት ውስጥ እየሰሩ ሲሆን ይህም ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር እንደሚሰራ ታውቋል። እኝህ ምሁር ከኢህአዴግ ጋር ያላቸውን ቀረቤታ እና ለአምባገነናዊው መንግስት ያላቸውን አወንታዊ አስተያየት በሚያመለክት መልኩ ንግግር አድርገዋል። በስልጣን ላይ ያለው "መንግሥት" ከጎረቤት አገሮች አንጻር የተሻለ መረጋጋትና የኢኮኖሚ ዕድገት የሚታይበትን መሆኑን ገልጸዋል። ነገር ግን እኝህ ምሁር ባቀረቡት አስተያየት ላይ ከመድረኩም ሆነ ከተሳታፊዎች ትችት ተሰንዝሮባቸዋል። ከውይይቱ ተሳታፊዎች እንደተገለጸው እንደ ዮሃን ሂላን የመሰሉ ምሁር ነን ባይ ግለሰቦች የኢትዮጵያ ህዝብ በምን ሁኔታ እንዳለ የማያውቁና በተጨባጭ እውነታውን የማያሳይና የተሳሳቱ መረጃዎችን በመጠቀም የምርምር ውጤቶችን የሚያቀርቡ ምሁራን እንዳሉ የተጠቆመ ሲሆን በዚህም የተሳሳተ የምርምር ድምዳሜ ምክንያት ምዕራባውያን መንግስታት የተወላገደ የፖሊሲ አቅጣጫ እንዲከተሉ አድርጓል።
በመጨረሻም በኖርዌይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊ ጥገኝነት ጠያቂወች ዙሪያ የሚያጠነጥን ዶክመንተሪ ቪድዮ ያቀረቡት አርቲስትና የሰብአዊ መብት ተማጋች የሆኑት ሶልቬይ ስይቨርሰን ናቸው። ይህንን ዓይነቱን ጥናት ለማድረግ ያነሳሳቸው ዋናው ምክንያት የኖርዌይ መንግስት እና የኢትዮጵያ "መንግስት" ስደተኞችን ለመመለስ ያደረጉትን ስምምነት አሳስቧቸው መሆኑን ተናግረዋል። በኖርዌይ የሚገኙ የኢትዮጵያውያን ስደተኞች በከፍተኛ ችግር ላይ እንደሚገኙ በመጥቀስ የኖርዌይ መንግስትም ተገቢውን ትኩረት በመስጠት የጉዳዩን ውስብስብነት እንዳልተመለከተው ጠቁመዋል። ያቀረቡትን ዶክመንተሪ ለሚመለከታቸው አካላት እንደሚያቀርቡና የተሻለ የጥገኝነት ፖሊሲ እንዲቀረጽ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
በመጨረሻም በተነሱ ጉዳዮች ዙሪያ አጭር ውይይት የተደረገ ሲሆን የተለያዩ አካላት ጥያቄና አሰተያየቶች ሰንዝረዋል። የስብሰባው አዘጋጆችም በጉዳዩ ዙሪያ ተከታታይ ውይይት እንደሚደረግ በመጠቆም የዕለቱን መረሃ ግብር አጠቃለዋል።

source:Golgul



Friday, March 7, 2014

በፓርስ ኢትዮጵያዊው ከጎዳና ተዳዳሪነት ያወጡትን እናትና ልጅ ገድሎ ተሰወረ!

ዘጋቢ፦ክንፉ አሰፋ (ጋዜጠኛ)

እናትና ህጻን ልጅዋን ገድሎ የተሰወረው ሰውዬ ትውልዱ ኢትዮጵያዊ ሲሆን በፈረንሳይ ፓሪስ ክርተማ የጎዳና ላይ ተዳዳሪ ነበር:: ሟች ወ/ሮ ክውን ገዳሙ ትባላለች:: ከቤትዋ ወደ ስራ ቦታ ሲመላለሱ ተጠርጣሪውን የዩታል:: በጎዳናው የተጎሳቆለውን ሰው(ጉዳዩ በህግ ስለተያዘ ስሙን እዚህ ላይ አንጠቅሰውም) ስለሚያሳዝናቸው ባለፉ ባገደሙ ቁጥር እጃቸውን ይዘረጉለት ነበር::

ከግዜ በኋላ ከክረምቱ ብርድ እንዲገላገል ሲሉ ይህንን የጎዳና ተዳዳሪ ለግዜው በቤታቸው አስጠጉት:: የአቅማቸውን እየረዱት አብረው ለወራት ኖሩ::
ባለፈው ሳምንት አንድ አስደንጋጭ ክስተት በቤተሰቡ ውስጥ ተፈጸመ:: በችግሩ ያስጠጉት ሰው ከተኙበት በጭካኔ ገድሏቸው አመለጠ::
ወ/ሮ ክውን ገዳሙ የሶስት ልጆች እናት ሲሆኑ በፈረንሳይ ፓሪስ ለረጅም ግዜ ኖረዋል:: የሶስት ልጆች እናትም ናቸው:: ያለአባት ከሚያሳድጓቸውን ሶስት ልጆች ውስጥ አንደኛዋና የሁሉም ታናሽ ከሆነችው ጋር ላይመለሱ ይህችን አለም ባለፈው ሳምንት ተሰናበቱ::
ገዳዩ ጭካኔ በተሞላበት መንገድ በጩቤ ሰነጣትቆ ነው እናትና ልጅን ለህልፈት የዳረገው- እንደ ፈረንሳይ የዜና ምንጭ:: ባጎረሱት እጅ ተነከሱ:: ደግ ባደረጉ ምላሹ ግድያ ሆነ: ለዚያውም አረመኔያዊ ግድያ::
ነብሰ ገዳዩ ለግዜው ተሰውሯል:: የፈረንሳይ ፖሊስ ከኢንተርፖል ጋር በመሆን ጉዳዩን በጥብቅ ይዞታል:: እኛም እየተከታተልን ጉዳዩ ምን እንደደረሰ እናቀርብላችኋላን::

Thursday, March 6, 2014

በመንግስት ታጣቂው በጥይት ተደብድበው የተገደሉት ባልና ሚስት ፎቶ ተገኘ



እብሪተኛ የመንግስት ታጣቂዎች ለሚቀጥፉት የሰው ህይወት መንግስት ተጠያቂ የሚሆነው መቼ ነው?ከዳዊት ሰለሞን
የመንግስት ታጣቂዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች ደማቸው በትንሽ በትልቁ እየፈላ ሲቪል ዜጎችን የሚጨርሱበት አጋጣሚ ከቀን ቀን እየጨመረ ነው፡፡
የባህር ዳሩን ዘግናኝ እልቂት ለጥቆ ቂርቆስ ቤ/ክ አካባቢ ሁለት ሰዎችን በጥይት በመምታት የወሲብ ደምበኛው እንደነበረች የተነገረላትን ሴት ሲገድል አብሯት የነበረውን ማቁሰሉ አይዘነጋም፡፡የታክሲ ሹፌሩ አልጭንህም ስላለው የታጠቀውን ሽጉጥ በመምዘዝ ለፍቶ አዳሪውን በአጭር አስቀርቶታል፣አራት ኪሎ ቤተ መንግስት አቅራቢያ በሚሄድ መኪና የተርከፈከፈ ጥይት ስንቱን እንዳስቀረ እግዜር ይወቀው ፡፡በየአካባቢው እንዲህ አይነት ዘግናኝ ዜናዎችን መስማት አዲስ አይደለም፡፡
ከትናንት በስቲያ በላፍቶ ክፍለ ከተማ አቦ ማዞሪያ አካባቢ በምስሉ የምትመለከቷቸውን የሶስት ልጆች ወላጆች እብሪተኛው ታጣቂ በጥይት በመደብደብ ገድሏቸዋል፡፡ ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡እሰየው ነው ፡፡ግን በቃ?እነዚያን ሶስት ህጻናት ማን ነው የሚያሳድጋቸው?ግለሰቡን አምኖ ክላሽ ያስታጠቀው አካል የማይጠየቀውስ እስከመቼ ነው?
መንግስት የመኪና አሽከርካሪዎች የሶስተኛ ወገን ኢንሹራንስ እንዲገቡ እያስገደደ መሆኑ በመኪኖቹ አደጋ ለሚደርስበት ሰው አንዳች ነገር ነውና ይበረታታል፡፡መንግስት በነካ እጁ የሚያስታጥቃቸው ሰዎች ለሚያደርሱት የመብት ጥሰት ኢንሹራንስ ይግባ!!!በእኔ እምነት ስለ ተገደሉት ወላጆችና ወላጅ አልባ ስለሆኑት ልጆች መጮህ የሁላችንም ግዴታ ነው።

Wednesday, March 5, 2014

በኢሕ አዴግ ውስጥ አለመተማመኑ በዝቷል፤ አንድነት በመዋቅሬ ውስጥ ገብቷል በሚል ግምገማ ሊጀምር ነው

 

Bahr dar 7
ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ እንደዘገበው፡
ኢህአዴግ የአንድነት ፓርቲ ኃይሎች በአደረጃጀቴ ሰርገው ገብተተዋል በሚል ግምገማ ለጀምር መሆኑ ታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ጽ/ቤት የአንድ-ለ-አምስት የአደረጃጀት አመራሮች በተለያዩ ክፍለ ከተማዎች የሚገኙ የአንድ-ለ-አምስት የአደረጃጀት አመራሮችን በመሰብሰብ “አንድነት ፓርቲ የአንድ-ለ-አምስት አደረጃጀታችን ውስጥ አስርጎ ያስገባቸው ኃይሎች በጊዜ በግምገማ ካልተራገፉ ቀጣዩ ምርጫ ከቁጥጥር ውጪ እንደማይሆን ማንም እርግጠኛ መሆን አይችልም፡፡” ማለታቸውን በስብሰባው ላይ የተሳተፉ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ተናግረዋል፡፡
eprdf UDJ ምንጮቹ ጨምረው እንደተናገሩት ኢህአዴግ የአንድ-ለ-አምስት አደረጃጀቱን የሚያስተባብሩ ከፍተኛ ካድሬዎችን አንድ-ለ-ሰላሳ ማደራጀት መጀመሩን ተከትሎ አንድነት ፓርቲ አስርጎ ያስገባቸው ኃይሎች አሉ በመባሉ ካድሬዎች እርስ በእርስ መሰላለል እና አለመተማመን ጀምረዋል፡፡ ይህ በካድሬዎቻቸው መካከል የተጠፈጠረው ትርምስ ያሰጋቸው የኢህአዴግ የአዲስ አበባ ጽ/ቤት አመራሮች ለክፍለ ከተማ አመራሮቻቸው አንድነት ሊይዝብን የሚችለው 30 በመቶ የሚሆነውን ህዝብ ነው የተቀረውን በኮንዶሚኒየም ፣ በአነስተኛ ጥቃቅንና በየአንድ-ለ-አምስት አደረጃጀት ይዘነዋል ብለዋቸዋል፡፡ ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ መረጃ የሰጡት የስብሰባው ተሳታፊዎች 750ሺ የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢ፣ 30ሺ የኮንዶሚኒየም እጣ ተጠባባቂዎች ኢህአዴግን ነው የሚመርጡት በሚል ከመድረክ የቀረበው መደምደሚያ እንዳላሳመናቸውም ተናግረዋል፡፡
ጉዳዩን በሚመለከት ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ከአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የደረሰው ዶክሜንት እንደሚያስረዳው ፓርቲው የአዲስ አበባ አደረጃጀቱን ኢህአዴግ በዘረጋው ልክ 138 ያደረሰ ሲሆን በአሁኑ ጊዜም የወረዳ ደረጃና የሴል አደረጃጀቶቹን በኢህአዴግ የአደረጃጀት ቁጥር ልክ የማድረግ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ያመለክታል፡፡

Source: Ze-Habesha